2015-04-17 16:01:00

ቤተ ክርስትያን ሀብት ማካበት የለባትም ያላትን መለገስ አለባት


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በየዕለቱ ጥዋት በቅድስት ማርታ በሚገኘው ቤተ ጸሎት ውሉደ ከህነት እና ምእመናን የሚሳተፉት መስዋዕተ ቅዳሴ እንደሚያሳርጉ የሚታወስ ነው። ትናትና ጥዋት እንደተለመደው መስዋዕተ ቅዳሴ ያሳረጉ ሲሆን በዚሁ መስዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት ቤተ ክርስትያን ሀብት ማካበት የለባትም ያላትን መለገስ አለባት ክርስትያኖችም በየጌታችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ይመሩ የነበሩ ቀደምት ክርስትያን ማሕበረ ሰቦች ያደርጉት እንደነበረ ሀብታቸው ከተቸገሩ ህዝቦች ጋር መካፈል ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

የመጀመርያዋ የክርስትያን ማሕበረ ሰብ ስትወለድ ክፍት በመሆን ማለት ማቻቻል እና ፍጹም ከስስት በመራቅ እንደሆነ በማመልከት ሀርሞኒ  ውህውበት መግባባት የሚሰጥ መንፈስ ቅዱስ ብቻ መሆኑ ጠቁመው ይህ ሕብረት የሚፈጥር ነው። መንፈስ ቅዱስ ለአንድ ማሕበረ ሰብ የሚሰጠው ፍሬ የመቻቻል የመፈቃቀድ እና የአንድነት ተግባር መሆኑ እና መንፈስ ቅዱስን ተላብሶ የሚኖር ማሕበረ ሰብ በመልካምነቱ እና ለጋስነቱ ይታወቃል ብለዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በቅድስት ማርታ ቤተ ጸሎት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ እና ባሰሙት ስብከት መጽሐፍ ቅዱስ ተተንተርሰው በማያያዝ አንዳንድ ማሕበረ ሰቦች እና ግለ ሰቦች ቤተ ክርስትያንን እንረዳለን ብለው ቀርበው የራሳቸውን ጥቅም የሚያሳድዱም አልጠፉም ብለዋል።

ይሁን እና አንድ ማሕበረ ሰብ ትዕግስት እንዲኖረው ያሻል በችግር ግዜ በሐዘን ግዜ በሕማም ግዜ በቃይ ግዜ ትዕግስት ጸሎልት እና ጥልቅ አስተንትኖ ያስፈልጋል ያሉት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በሁለተኛ የትንሳኤ ሳምንት መሆኑ በማስታወስም የትንሳኤ ሚስጢር የምናከብርበት እና የምናስተነትንበት ግዜ ነው የሃገረ ስብከቶች የቁምስናዎች እና የቤት ሰቦች መልካምነት እንዲኖር የበኩላችን አስተዋጽኦ የምናበረክትበት ግዜ መሆኑ ጠንቅቀን መረዳት ይጠበቅብናል ብለዋል።

እንድግዲህ ቀደም ሲል እንዳልኩት ለጋሶች እና ለማህበረ ሰቦች መልካምነት መቆም እንዳለብን በተለይ በችግር ላይ ለሚገኙ ህዝበ ክርስትያን ማሰብ መለገስ እና ሞራል መስጠት ይገባናል በማለት ስብከታቸውን አጠናቅቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.