2015-04-15 19:37:00

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ፤


 

ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ! የዛሬው ዕለት ትምህርተ ክርስቶሳችን የቤተሰብ አንኳር በሆነው እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሰጣቸው ጸጋዎች ታላቁ የሆነው ውንድና ሴት አድርጎ መፍጠሩና በምሥጢረ ተክሊል ተሳስረው እንዲኖሩ ማድረጉን እንመለከታለን፣ የዛሬው ዕለትና በሚቀጥለው ሳምንት የምሰጣቸው ትምህርቶች ይህን ይመለከታሉ፣ ዛሬ  በወንድና በሴት መካከል ስላለው ልዩነትና መሟላት ስንመለከት በሚቀጥሉት ደግሞ ስለሰርግና ሌሎች ጉዳዮች እንመለከታለን፣

በኦሪት ዘፍጥረት ላይ “እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው” (1፤27) በማለት ስለ የሰው ልጅ አፈጣጠር በሚመለከተው እንጀምራለን፣ ከጠቅስነው ቍጥር በፊት ያለው እግዚአብሔር ዓለምንና በውስጡ ያለውን ሁሉ ከፈጠረ በኋላ ከፍጥረቶቹ ሁሉ አስደናቂውን ማለት የሰው ልጅን በመልኩ እንደፈጠረ እንረዳለን፣

እኛ ሁላችንም እንደምናውቀው ጾታዊ ልዩነት በተለያዩ ሕያው ፍጡራን ከታናሹ እስከ ታላቁ እንዳለ ነው፣ ነገር ግን በሰው ልጅ ብቻ ነው የእግዚአብሔር መልክና ምስል የሚገለጠው፣ ይህንን ነገር ቅዱስ መጽሓፍ ሶስት ጊዜ ይደጋግመዋል፣ የሰው ልጆች ሴትና ወንድ የእግዚአብሔር መልክና ምስል ናቸው፣ በዚህም የሚገልጽልን የሰው ልጅ ውንዱ ብቻውን ወይንም ሴቲቱ ብቻዋን ሳይሆን እንደ ጥንድ ሁሉቱም በአንድነት የእግዚአብሔር መልክ እንዳላቸው ነው፣ በሰው ልጆች በሴትና በወንድ ያለው ልዩነት ለውድድር ወይንም አንዱ ሌላውን ሊጮቅን ሳይሆን ለኅብረትና ዘር ለማቆም ሁሌም  በእግዚአብሔር መልክና ምስል እንዲሆን ነው፣

ተመክሮ እንደሚያስተምረን ጥሩ አድርጎ ለመተዋወቅና የሰው ልጅ ባህርይን በኅብረት ለማሳደግ አንዱ ሌላውን መደገፍ እንዳለበት ነው፣ ይህ መሠረታዊ በሴት ልጅና ወንድ ልጅ መካከል መኖር ያለበት መተባበር የሌለ እንደሆነ ውጤቱም ወዲያው ይታያል፣ የተፈጠርነው አንዱ ሌላውን ለማዳመጥና ለመርዳት ነው፣ አንዱ ሌላውን በኃሳብ በተግባር በፍቅር እና በሥራ በእምነትም ሳይቀር ያልረዳና ያላበለጸገ እንደሆነ ውጤቱ ግልጽ ነው፤ ሌላው ቀርቶ ሴት መሆንና ወንድ መሆን ምን ትርጉም እንዳለው ሁለቱም ሊረዱት አይችሉም፣

የተያዝነው ዘመናዊ ባህል ይህንን ልዩነት ለማስረትዳ ብሎም በጥልቅ ለማቀራረብ ብዙ አዳዲስ ሁኔታዎችና ነጻነቶች ያቀርባል፣ ነገር ግን ጾታን በሚመለከት ብዙ ጥርጣሬዎችና ልዩነቶችም አስከትለዋል፣ ለምሳሌ ያህል እኔ የምጠይቀው ይህ ነው፤ ምንም እንኳ የመሰልቸትና ተስፋ የመቍረጥ መግለጫም አይሁን ግን የሚቀርበው ጾታዊ ሥነ ኃሳብ ሊረዳው ስላልቻለ ጾታዊ ልዩነትን ለመደምሰስ ለምን ይጥራል? እስቲ ወደኋላ መለስ ብለን እንመልከት፤ ጾታዊ ልዩነትን መደምሰስ ችግር እንጂ መፍትሔ ሊሆን አይችልም፣ ባልና ሚስት የትዳር ፈተናዎችና ችግሮችን  መፍትሔ ለማግኘት ጠልቀው መነጋገርና መወያየት መደማመጥ በበለጠ መተዋወቅና መፈቃቀር አለባቸው፣ አንዱ ሌላውን በአክብሮትና በጓደኝነት መተባበር አለባቸው፣ በዚሁ ሃሳብና በእግዚአብሔር ጸጋ እርዳታ ቤተሰብ ለመመስረትና ለማቆም ቃል ኪዳን ማሰርና እስከ ለሞት የሚያደርስ ማቀድ ይቻላል፣ ቃል ኪዳን ማሰርና ቤተሰብ ማቆም አብይ ቁምነገር ነው ይህም ለአማኞች ብቻ ሳይሆን ለማያምኑም ጭምር ነው፣ ሊቃውንት ይህንን ነገር ቸል እንዳይሉትና ነጻና ፍትሓዊ ማኅበረሰብ ለማቆም በአንደኛ ደረጃ እንጂ በሁለተኛ ደረጃ የሚመለከት ጉዳይ አይደለም፣

እግዚአብሔር ዓለምን ለሰው ልጆች ለሴትና ወንድ ልጆቹ   ኪዳን አደራ ሰጣት! የዚህ ኪዳን መበተን ዓለምን ከፍቅር ያደርቃል የተስፋ ሰማይንዋን ያጨልማል፣ ምልክቶቹ እጅግ የሚያስጨንቁ ናቸው እናያቸዋለምም፣ ከእነዚህ መካከል ሁለት ነጥቦች መጥቀስ እወዳለሁ በአስቸኳይም መሥራት ያስፈልጋል፣

የመጀመርያው በሴቶችና በወንዶች መካከል ያለውን መተባበርና መረዳዳት ለማበረታታት ሴት ልጆችን በሚመለከት ብዙ መሥራት እንዳለብን የማይካድ ሐቅ ነው፣ የሴቶችን አስተያየት መደመጥ ብቻ ሳይሆን የሚሰጡትንም ሃሳብ ተቀብሎ ተግባር ላይ ማዋልና የሃላፊነትን ቦታ በሕብረተሰቡና በቤተክርስቲያን እንዲሰጥም ያስፈልጋል። በመጽሐፍ ቅዱስ እየሱስ ለሴቶች ከፍተኛ ቦታን እንደሰጣቸው እንመለከታለን። በመጽሐፍ ቅዱስ ከተመለከትን በዛን ግዜ ከኛው ቢለይም በዛን ግዜ ሴቶች በሕብረተሰቡ በ2 ደረጃ ነበር የሚያስቀምጣቸው የሚመለከታቸው። አየሱስ ግን ሴትን የሚመለከታት የመንገዱን ርቀት የምታሳይ እንደ ቦግ ያለ መብራት ሲሆን እኛ ግን የተራመድነው መንገድ ትንሽ ነው። እኛ ገና የሴትን እውቀትና በሴት ዓይን ለሕብረተሰቡና ለኛ ወንዶች መስጠት የምትችለውን ገና አልተረዳነውም። ይህንን ለመረዳት ከዘልማድ አስተሳሰብና መውጣትና ድፍረት ያስፈልጋል።

ትኩረት እንዲሰጠው የምፈልገው ሁለተኛው ነጥብ ደግሞ “ሴትና ወንድ ልጆቹን በእግዚአብሔር መልክ እንደተፈጠሩ” የሚያመለክተውን ነው። እኔ የምለው የዘመኑ በእግዚብሔር የመታመን ቀውስ እጅግ እንደሚጐዳን እንዲሁም ላለመታመንና ለመጠራጠር እንድንገዛ የሚያደርገን በባልና ሚስት መካከል መኖር ያለበት ኪዳን ቀውስ ሳቢያ እንዳይሆን ማስተንተን ያስፈልጋል! በእርግጥ በመጽሓፍ ቅዱስ ታሪክ ምድራዊ ገነትንና የአባታችን አዳም ሐጢአት በሚያስደንቅ ሁኔታ ሲተርክልን ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት የሚያንጸባርቀው በሁለት ሰዎች ጥምረት ያለው ግንኙነት ሲሆን ተስፋ መቁረጡንም የሚያሳየን የሁለቱ ሰዎች ጥምረት መበላሸትና በሰማያዊ አባታችን እምነት ማጕደል መከፋፈል እንዲሁም በባልና ሚስት መካከል ግጭት ያስከትላል፣

የቤተክርስቲያን ታላቅ የኅላፊነት ድርሻ ለምእመናኖችዋ በቅድሚያ ለቤተሰቦች እዚህ ላይ ነው። ምእመናን የእግዚብሔርን ውበትና የእቅዱን ዓላማ በመጽሃፍ ቅዱስ አንደተጻፈው በአምሳሉ መፈጠራችንና የሴትና ወንድ ልጆቹን ሕብረት አስቀድሞ ማወቁ እስፈላጊ ነው። ምድር ሐሴት የምታደርገው ወንድና ሴት ልጆቿ በፍቅርና በሕብረት ተስማምተው ሲኖሩ ነው። ይህም ሴቶችና ወንዶች በአንድነት በመስማማት ከአምላካቸው ጋር በመተባበር ሰላምን ከፈለጉ ያለ ጥርጥር ያገኛቷል።  ክርስቶስ የሚያበረታታን በግልፅ የምንመሰክረው ውበቱ በእግዚአብሔር መልክ መፈጠራችንን ነው።








All the contents on this site are copyrighted ©.