2015-04-13 15:40:00

ቅዱስ አባታችን፦ ለድኻው ትሪፍራፊ መተው ሳይሆን ፍትህና ሰላም መስጠት


እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 10 ቀን 2015 ዓ.ም. በፓናማ የተጀመረው የመላ የደቡብና ሰሜን አመሪካ አገሮች መርሔ መንግሥታት ይፋዊ ሰባተኛው ጉባኤ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 11 ቀን 2015 ዓ.ም. መጠናቀቁ የሚታወስ ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለጉባኤ ያስተላለፉት መልእክት በጉባኤ በተገኙት በቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን መነበቡ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ገለጡ።

በዚያ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ርእሰ ብሔር ባራክ ኦባማና አቻቸው ራዉል ካስትሮ መካከል ታሪካዊ ተብሎ የሚነገርለት የግማሽ ዘመን መራራቅ እንዲያከትምለት የሚያግዘው የእጅ መጨባበጥ ሁነት በታየበት መድረክ ተገኝተው  የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መልእክት ያነበቡት ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን፦ “ለድኾች ትራፊ ሳይሆን ፍትህና ሰላም መስጠት። ድኻው የኅብረተሰብ ክፍል ከሃብታሙ መአድ ውዳቂ እንዲሰበስብ የሚያደርግ ተስፋ ሳይሆን ፍትህና ሰላም ሊረጋገጥለት ያስፈልጋል፣ ሰብአዊ መብቱና የሁሉም ግዴታም ነው። በዓለማችን የኤኮኖሚ እድገት በሚኖርበት በአሁኑ ወቅት በድኽነት የሚኖሩ ዜጎች አሁንም እጅግ ወደ ባሰውና ወደ ከፋው ድኽነት ሲያምሩ ይታያል፣ አንድ እድገት እውነተኛ እድገት የሚያስብለው ሁሉም የሰው ዘር የልማቱ ተጠቃሚ ሲያደርግ ብቻ ነው። በመሆኑም በድኽነት ጫንቃ ሥር ለሚገኙትና በድኽነት ለሚሰቃዩት በቀጥታ የሚያስብ የኤኮኖሚ እቅድ ተቀዳሚው የልማት መርሃ ግብር መሆን አለበት” እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ፦ “ፍትህና ሰላም ላይ የጸና ለተስተካከለ ሁሉም የሚያስተናግድ እኩልነት ወንድማማችነት የሚያረጋገጥ አዲስ የዓለም ደንብ ማረጋገጥ” አስፈላጊ መሆኑ እንዳሰመሩበት ገልጠዋል።

“ስደተኞች እንክብካቤና ከለላ እንጂ ለአዲስ ባርነት አደጋ እንዲጋለጡ መተው አደገኛ ጸረ ሰብአዊ ተግባር መፈጸም ማለት ነው። ብዙውን ጊዜ በተለያየ ዘርፈ ብዙ ችግር ተገፋፍተው ቤትና ንብረት ጥለው ለስደት የሚዳረጉት ዜጎች ለተለያዩ የወንጀል ቡድኖች ወጥመድና ለባርነት አደጋ ተጋልጠው ማየቱ መቼም ቢሆን እንዳይለመድና ተቀባይነት ያለው የሚያስመስለው ፈተና ሁሉ በጋራ መዋጋት የሁሉም መንግሥታት ኃላፊነት ነው” የሚል ሃሳብ የተሰመረበት ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን ለመላ የላቲንና የሰሜና አመሪካ መሪዎች ጉባኤ የቅዱስ አባታችን መልእክት ያነበቡት አክለው “የሰው ልጅ መብትና ክብር ለማስጠበቅ ሕግ ለብቻው በቂ አይደለም፣ ስለዚህ አሳቢነት ተቆርቋሪንት ፍትህና ሰላም በሚል እሴት ላይ የጸና ሕግ እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል፣ እንዲህ ባለ ሁኔታ ዘረኝነት ብሔርተኝነት የመሳሰሉት የአንድ አገር ሉኣላዊነት ለአደጋ የሚያጋልጥ ችግር ለመቀርፍ ብቻ ሳይሆን፣ ሁሉም ተከባብሮና ተግባብቶ ለመኖር እንዲችል የሚያበቃ አቢይ ድጋፍ ማቅረብ ይሆናል” እንዳሉ ጂሶቲ አመለከቱ።

“እኩልነት መጓደልና ኢፍትሃዊነት የተካነው የተፈጥሮ ሃብት ያጠቃቀም ስልት በሕዝቦች መካከል የግጭት የውጥረት መሠረት ይሆናል፣ የሁሉም አመሪካዎች መሪዎች ዓለማዊ ትሥሥር ግድ የለሽነት ላይ ሳይሆን ትብብርና ወንድማማችነት ላይ የጸና በማድረግ ፍትህ እኩልነት እንዲጸና አበክረው እንዲሠሩ አደራ” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.