2015-04-03 16:21:00

ብፁዕ ካርዲናል ሩዊኒ፦ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ርህሩህ አቢይ የእግዚአብሔር ሰው


ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የሮማ ጳጳስ ሆነው በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነት ሥልጣን ኵላዊት ቤተ ክርስቲያንን በመሩበት ረዥም ዓመታት የሮማ ሰበካ ኅየንተ በመሆን ያገለገሉት ብፁዕ ካርዲናል ካሚሎ ሩዊኒ የዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ዝክረ 10ኛው ዓመት በሰማያዊ ቤት መወለድ ምክንያት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦

ስለ ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ የግል ትውስቴ ይላሉ የእሳቸው ዜና እረፍት እንደተነገረ ከምኖርበት ቅዱስ ዮሓንስ ዘላተራኖ ሕንፃ ወደ ቫቲካን በመሄድ እዛው ያዩት የሃዘን መንፈስ የሚገርመው ሰላም የተሞላው መሆኑ ነበር። የሐዘን መንፈስ ሰላም የተሞላው ነበር ብሎ መናገር ያዳግታል ሆኖም ግን የመንፈስ ሰላም ሰፍኖ ነበር። የእሳቸው ሥልጣናዊ ምዕዳን ሓዋርያዊ መልእክቶች፣ ስብከቶች ዓዋዲ መልእክቶቻቸው በጠቅላላ ቃላቸው ኅያውና ወቅታዊ ነው። አቢይ የለውጥ ታሪክ ያመጡ እንደ እሳቸውም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ያወጁት የምህረት ዓመት በእውነቱ ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ያስታውሰናል፣ ሁሉም እንደሚያስታውሰውም ቅዱስ ዎይትይላ መለኮታዊ ምኅረት በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ዓዋዲ መልእክት የሚያስተጋባ ቅዱስ ዓመት ነው።  ስለ መለኮታዊ ምኅረት በተለያየ ወቅት ያስደመጡት ስብከት ምዕዳን በእውነቱ እግዚአብሔር ምኅረት መሆኑ  የሚያረጋግጥ ነው። የክፋት መንፈስ ውስንነት የእግዚአብሔር ምኅረት የማይሻር ወይንም የማይሸነፍ መሆኑ ነው በማለት ያሰመሩበት ጥልቅ ቲዮሎጊያዊ መጽሓፍ ቅዱሳዊ እሳቤ በእውነት እምነታችን የሚገልጥ የእግዚአብሔር ማንነት የሚያበክር ነው ብለዋል።

ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የደረሱት የመጀመሪያ ሐዋርያዊ መልእክታቸው ቤተሰብ ርእስ ዙሪያ ነበር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮም የጠሩት የመጀመሪያው ሲኖዶስ ቤተሰብ ዙሪያ የመከረ ነው ይኽ ደግሞ በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አማካኝነት በቤተ ክርስቲያ ለሚኖር ኅዳሴና ቀጣይነት ምስክር ነው ብለዋል። ስለ ሰብአዊ ፍቅር ያቀረቡት ምዕዳን ስብከት በጠቅላላ ወቅታዊነቱ የማይሻር ነው። ስለ ሚሥጢረ ተክሊል የቤተሰብ ሚና ቤተሰብ ትዳር በተመለከተ የተለያዩ መንግሥታት ያጸድቁት ያስተጋቡት የነበረ ውሳኔና ሃሳብ በጥበብ መልስ የሰጡ የሕይወት ባህል ያስፋፉ ናቸው ለዚህ ሁሉ ወንጌላዊ ሕይወት በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ዓዋዲ መልእክት ማስታወሱ ይበቃል።

በአሲዚ የሁሉም ሃይማኖቶች የጋራ ውይይት ያስጀመሩት በጸሎት ዙሪያ ተገናኝቶ መወያየት ያነቃቁ ያንን በአንቀጸ እምነት ላይ የነበራቸው ጽኑ ታማኝነትና እምነት አቅበው ከሁሉም ጋር በመወያየት የተከተሉት ጥበብ የሚደነቅ ነው በዚህ አጋጣሚም ይኽ መንፈስ በቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛና በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እየተመሰከረ ነው። ክርስትና የሕይወት የፍቅር የሰላም የፍትህ ባህል መሆኑ የመሰከሩ ይኽ ደግሞ ክርስትና እምነት መሆኑ ያበከረ ጥበብ ያስተማሩ መሆናቸው ገልጠው፣ ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር ለጎረቤታችን ባለን ፍቅር መመስከሩ ግድ የሚል ጥበብ ያነቃቁ ናቸው። ስለዚህ ሁሉም ሃይማኖቶች ውይይት ፍቅር ሰላም ፍትህ ወንድማማችነት የሚያነቃቁ መሆናቸው ያስገነዘቡ፣ የፍልስፍና የቲዮሎጊያ የስነ ጽሑፍ የቤተ ክርስቲያንና የዓለም ታሪክ የመጽሓፍ ቅዱስ ሊቅ ናቸው።

ኤወሮጳ በፖለቲካና በኤኮኖሚ አንጻር አንድ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ባህል መሠረት ካላደረገ ዘላቂነት የሌለው ባዶ መሠረት የለሽ ፍላጎት ወይንም እቅድ መሆኑ ያመለከቱ፣ ዓለም የሚለወጠውና የሚታደሰው ለወጣት ትውልድ በሚሰጠው ሕንጸት አማካኝነት መሆኑ እንዳስተማሩና እ.ኤ.አ. በ 1991 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በማነቃቃት በዚያች እጅግ በሚያከብሯት አማላጅ የክዘስቶኮዋ ማርያም አማላጅነት ጥበቃ ሥር በማኖር ይኸው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ቀጣይነቱ ተረጋግጠዋል።

የዮሐንስ ጳውሎስ የቀርብ ተባባሪ ሆነው ያገለገሉበተ ዓመታት አስታውሰው ከትውስቶቻቸው አንዱ ለመጀመሪያ ጊዜ ገና በኢጣሊያ የረጆ ኤሚሊያ ጳጳስና የሎሬቶ ጉባኤ አዛጋጅ ኮሚቴ ሊቀ መንበር እያሉ በ 1984 ዓ.ም. ከሳቸው ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ለእራት ታድመው በሐዋርያዊ መንበር እንደተገናኙዋቸውና በእራት ማእድ የዮሓንስ ጳውሎስ የግል ጸሓፊ የአሁኑ የክራኮቪያ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ስታንስላው፣ ብፁዕ ካርዲናል ረ አብረው መገኘታቸው ዘክረው ብዙ የሃሳብ ልውውጥ የተደረገበት አጋጣሚ ነበር ብለው። ከዚያ ሰዓትና ቀን ጀምሮ በሳችው ግልጽነት አርቆ አሳቢነት እምነትና ጥበብ መደነቃቸው ገልጠው፣ በእውነቱ ቅዱስ አባት ናቸው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.