2015-04-01 16:10:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የኢዮበሊዮ አዋጅ ድንጋጌ (Bulla Papalis)


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያወጁት እ.ኤ.አ. ታህሳስ 8 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚጀመረው የምኅረት ዓመት እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 11 ቀን 2015 ዓ.ም. በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በኋላ ልክ አምስት ሰዓት ተኩል የኢዮቤልዮ አዋጅ ሰነድ የኅትመት በዓል በይፋ እንደሚጀመር የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

የአከባበሩ ሊጡርጊያዊ ሥነ ሥርዓት

የኢዮበልዮ አዋጅ ሰነድ ድንጋጌ ክብረ በዓል በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ባለው ቅዱስ በር ፊት ተኩኖ አንዳንድ በውሳኔው የአዋጅ ሰነድ ዓውደ ካለው ጽሑፍ በተወሰዱት በአንዳንድ ምንባባ ተሸኝቶ፣ ቀጥሎም በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሠራኢነት በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ የሰንበት ዘምኅረቱ አንደኛው ጸሎተ ዘሠርክ ያወጁት ልዩ የቅዱስ ዓመት ዋና ርእስ ሥር እርሱም “የእግዚአብሔር ምኅረት”  ላይ በማተኮር ይፈጸማል።

ግጻዌ፣ ጊዜያትና ተስፋ የተኖረባቸው ፍሬዎችየኢዮበልዮ ዓመት አዋጅ፦ የታወጀው ልዩ ቅዱስ ዓመት ሰነድ በይፋ የሚከፈትበት ቀን የሂደቶቹ ግጻዌ የመዝጊያ ቀን፣ ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩም ቅዱስ አባታችን ቅዱስ ዓመት ያወጁበት ምክንያት፣ የአበይት ክንዋኔዎቹ ምን ተምስሎ፣ የቅዱስ ዓመት እሳቤዎችና ተስፋ የተኖረባቸው ፍሬዎች ያካተተ መሆኑም የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.