2015-04-01 16:20:00

የሃይማኖት መሪዎች፦ ሊባኖስ የመከፋፈል ስውር ዓላማ ያለ እንደሚመስል ገለጡ


እ.ኤ.አ. መጋቢት 30 ቀን 2015 ዓ.ም. በሊባኖስ የሚገኙት የሁሉም ሃይማኖት የበላይ መንፍሳዊ መሪዎች ብከርከ ሰበካ የማሮናዊ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ሕንፃ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ ባካሄዱት የጋራ ውይይት፦ ለሊባኖስ መከላከያ ኃይል ሰብአዊ ድጋፍ ገልጠው፣ በአገሪቱ ማለቂያ የሌለው ጊዚያዊ ርእሰ ብሔር ስያሜ እንዲወገድና ሃይማኖት ተገን በማድረግ የሚሰበከው አሸባሪነትና ግብረ ሽበራ ማውገዛቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የሃይማኖት መሪዎች የዚህ ዓይነቱ ቀጣይ የጋራው ግኑኝነት ፈር በያዘ መልኩ መካሄድ እንዳለበትም በመስማማት፣ በአገሪቱ የሚታየው ቋሚ የርእሰ ብሔር መጓደል የአገሪቱ ሉአላዊነት ደህንነትና ጸጥታ አደጋ መሆኑ አብራርተው፣ ያ በአገሪቱ የሚገኙት ሃይማኖቶች በጋራ ሰላማዊ ኑሮ ለመኖርና ለመከባበር ብሎም በፖለቲካዊ መድረክ የመሳተፍ መብትና እኩልነት የሚያረጋገጠውን የሊባኖስ ሕገ መንግሥት ቅርጽ የሚያዛባ ሁነት የሚፈጥር እንደሚሆንም ገልጠው፣ አገሪቱ እ.ኤ.አ. ከግንቦት 25 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምራ ቋሚ ርእሰ ብሔር የሌላት በመሆንዋና ይኽ ደግሞ አገሪቱ ለአደጋ የሚያጋልጥ ጉዳይ ሆኖ ላለው ማኅበራዊ ሃይማኖታዊ ሰላማዊ የጋራው ኑሮ ለአደጋ ከማጋለጡ በፊት የፖለቲካ አካላት ተገቢ መፍትሔ ለማረጋገጥ የማያወላውል መልካም ፈቃድ ሊኖራቸው ይገባል እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት ገለጠ።

የሃይማኖት መሪዎች አክለው በመካከለኛው ምስራቅ ባለው ውጥረት ሳቢያ ሊቦኖስ የሚገኙት የሶሪያና የኢራቅ ተፈናቃይ ዜጎች ሊቦኖስ አጋጥሟት ያለው ኤክኖሚያው ችግር አቢይ ግምት የሰጠ የዓለም አቀፍ ማኅበርሰብና የተለያዩ የበጎ ፈቃድ ማኅበራት የተሟላ ሰብአዊ ትብብር ያለው አስፈላጊነት ገልጠው፣ ሁሉም ድጋፍ በማቅረቡ ረገድ እንዲተጋ አደራ ማለታቸውን የገለጠው ፊደስ የዜና አገልግሎት አክሎ፦ ሃይማኖት ተገን ያደረገ እየተስፋፋ ያለው ሽበራና የሽበራ ድርጊት በማውገዝ፣ ይኽ ሃይማኖት ከለላ በማድረግ እየተስፋፋ ያለው የሽበራ ተግባር በመካከለኛው ምስራቅ እየተዛመተ የተቀረው የዓለም ለአደጋ እያጋለጠ መሆኑና፣ የመካከለኛው ምስራቅ ማኅበረ ክርስቲያን የሌሎች አናሳ ሃይማኖት አባላት ጭምር ለስደትና ለመፈናቀል አደጋ በመዳርግ፣ የመካከለኛው ምስራቅ ከሁሉ ኃይማኖት በፊት በክልሉ ያለው ጥንታዊው የክርስትናው ባህል ለማጥፋት ያቀና ስውር ዓላማ ያለው መሆኑም አብራርተው፣ የዚህ ዓይነቱ ማለትም የሊባኖስ የሁሉም ሃይማኖቶች መንፈሳውያን የበላይ መሪዎች ጉባኤ በየሦስት ወር አንዴ እንዲካሄድ የሚል የጋራ ስምምነት ማድረጋቸውም ባወጡት የጉባኤው የፍጻሜ ሰነድ ላይ እንዳመለከቱም አስታውቀዋል።  








All the contents on this site are copyrighted ©.