2015-03-30 16:59:00

ትህትና የእግዚአብሔር መንገድ


ትናትና እሁድ መጋቢት ወር 29 ቀን በሥርዓተ አምልኮ ላቲን ሆሳዕና ከፍ ባለ ድምቀት ተከብሮ የዋለ ሲሆን፤ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ምእመናን በተገኙበት በካርዲናላት ጳጵሳት እና ካህናት ተሸኝተው መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገዋል።

ቅድስነታቸው በዚሁ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት ትህትና የእግዚአብሔር መንገድ መሆኑ ጠቁመው ካለ ውርደት ትህትና እንደማይኖር አስገንዝበዋል። መድኅን ክርስቶስ ከህዝቡ ጋር ለመጓዝ መዋረዱ ጠቅሰው ዛሬ ሳምንተ ሕማማት ኢየሱስ ክርስቶስ የሚጀመርበት ዕለት መሆኑ ምእመናንን አስታውሰዋል። ለመጽሐፍ ቅዱስ ታማኝ በመሆናቸው የተዋረዱ እና የሚዋረዱ በርካታ መሆናቸውንም አመልክተዋል። እንግዲህ የመድኅን ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስን ሕማማት ለመከተል ዝግጁ መሆን ይጠበቅብናል ያሉት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ትህትና የኢየሱስ ክርስቶስ ስልት መሆኑ በማስገንዘብ ትህትና ቀውስ ላይ የሚጥል መሆኑ ጠቅሰው የትሁት እግዚአብሔርን ስልት መከተል በቀላሉ ላይለመድ ይችላል ብለዋል።

በሳምንተ ሕማማት ጌታችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሱ ላይ የወረደ ስድብ እና ውርደት የተቃጣበት ስቃይ የማናስተነትንበት ግዜ መሆኑ እጽንኦት ሰጥተው አስገንዝበዋል። በሌላ በኩልም የኢየሱስ ክርስቶስ ትህትና እንመለከታለን ውርደት አላባ ትህትና ሊኖር እንደማይችል ግን ግልጽ መሆን አለበት ይሉና ትህትና ማለት አገልግሎት ትህትና ማለት ሁለንትናህ ለእግዚአብሔር ቦታ መስጠት መሆኑ አመልክተዋል።  የእግዚአብሔርን መንገድ የሚጻረር መንገድ መጓዝ ማለት ዓለማዊ መንገድ መሆኑ እሱን ማሳዘን በየዲያብሎስ ፈተናዎች መሸነፍ መሆኑ ኢየሱስ ክርስቶስ በምድረ በዳ ለርባ ቀናት በነበበረበት ግዜ ፈተና እንደገጠመው እና ወድያውኑ ውድቅ እንዳደረገው አስታውሰዋል። በየኢየሱስ ክርስቶስ ምሕረት እና እገዛ ከዓለማውነት ከእብሪት እና ከንቱነት መገላገል እንችላለን በማለት ስብከዋል።

የመድኅን ኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ለመከተል መጠራጠር የለብንም እሱን እንከተለው እንውደደው እናመስግነው እንስገድለት ምክንያቱም ሁሉ የሚቻለው ፈጠሪ ነው እና ብለው ያሉት ቅድስነታቸው እሱ ሐጢአታችን ሁሉ ተሸክሞ እናን ለማዳን ተሰቅይቶ ተገርፎ የሞተ እና የተነሳ ነው እና በማለት አስገንዝበዋል።

በማያያዝም በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በእምነታቸው የተነሳ ለሚሳደዱ እና ለሚንገላቱ ሁሉ እንጸልያላቸው እናስባቸው ለእምነታቸው በሰማዕትነት የሚያልፉም እንዳሉ እና ቤተ ክርስትያን ሁኔታቸው እንደሚያሳስባት ጠቅሰው እነሱ መጽሐፍ ቅዱስን ለመመስከር ሕይወታቸው እየሰጡ መሆናቸው አስታውቀዋል። የእግዚአብሔር ፍቅር ኀይል ይሰጠናል ትክክለኛውን መንገድ ይመራናል እና መንገዱ እንከተል መልካም ሶሙነ ሕማማት ለሁላችን በማለት ስብከታቸውን አጠቃልለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.