2015-03-30 17:34:00

በጀርመንዊንግስ አደጋ ለተጐዱ ወገኖች በጸሎት ማሰብና እአአ በ2016 ዓም ስለሚካሄደው የወጣቶች ቀን


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ትናትና በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ከተገኙ ምእመናን ጋር እሁዳዊ መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ደግመዋል። ከመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ፍጻሜ በኃላ ፊታችን ዓመት 2016 እኤአ በፖላንድ ክርኾቭያ ከተማ ላይ እንዲከናወን የታቀደውን ዓለም አቀፍ የወጣች ግንኙነት አስታውሰው፤ ወጣቾች በየቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ሀገር በሆነችው ፖላንድ እግዚአብሔር ከወጣቶች ጋር በሰላም እንድያገናኘን እንጽልይ ብለዋል።

በዚሁ ትናትና በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የተመራ የሆሳእና ሥርዓተ ቅዳሴ እና እኩለ ቀን ላይ የተፈጸመው የመልአከ እግዚአብሔር እሁዳዊ ጸሎት በብዙ ሺ የሚገመቱ ወጣቶች ተገኝትረው ነበር። ዓለም አቀፍ የወጣቶች ግንኙነት በቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የተማሩ ብጹዓን ናቸው ምሕረት ያገኛሉ እና በሚል ስያሜ መጀመሩ የሚታወስ ነው። በቅርቡም ቤተ ክርስትያን ከፊታችን ታሕሳስ ወር ስምነት ቀን ጀምሮም እስከ ፊታችን ዓመት የሚቆይ የምሕረት ዓመት ማወጅዋም የሚታወስ ነው።

ትናትና የተጀመረውን ሳምንተ ሕማማት ኢየሱስ ክርስቶስ በእምነት እና ጠንክረን እንወጣው ዘንድ ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክን እናለምን በማለትም አሳስበዋል። ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በገባበት ግዜ እስዋ ማለት ቅድስት ድንግል ማርያም እዚያው መኖርዋ እና ለመስዋዕተነት ዝግጁ መኖርዋ አክለው ገልጠዋል።

በመጨረሻም ባለፈው ሰኞ ከእስጳኛ ወደ ጀርመን ይበር በነበረ ጀርመንዊንግስ አየር መንገድ በደቡባዊ ፈረንሳይ መከስከሱ እና 150 ሰዎች ለሕለፈት መዳረጋቸው አስታውሰው እግዝአብሔር ለሕለፈት ለተዳረጉት መንግስተ አማየቱ ለቤተ ሰቦቻቸው ጥናቱ እንዲሰጠቸው ቅድስነታቸው ከምእመናን ጋር ጸልየዋል። አደጋው የተከሰተው ረዳት አብራሪ ሆን ብለው አውሮፕላኑ እንዲከሰከስ ማድረጋቸው በጀርመን የዱሱልዶርፍ አቃብያነ ሕግ መግለጫ መስጠታቸው ታውቆዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.