2015-03-25 16:03:00

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍርናቸስኮስ ዛሬ ሮብ ረፋድ ላይ የተለመደውን ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምርተ ክርስቶስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከማቅረባቸው በፊት በተለያዩ በሽታዎች ለታመሙ በጳውሎስ ስድስተኛ አደራሽ ተቀብለው አነጋገሩ፣ ዛሬ ዕለት በሮም ዝናም ስለነበረ በአደባባዩ የነበሩ ዣንጥላ ይዘው ሲከታተልዋቸው ሕመምተኞቹ ደግሞ በቪድዮ በአደራሹ ሆነው ትምህርቱን ተከታተሉ፣

ስለቤተ ሰብ የጀመሩትን ትምህርት በመቀጠልም የዛሬው ትምህርት ልዩ ትኵረት የሚሰጠው በቤተሰብ ዙርያ ሊካሄድ እየተሠራበት ስላለው ሲኖዶስ ለመጸለይ እንደሆነ አመልክተዋል፣ በላቲኑ ሥርዓተ አምልኮ ዛሬ ከቤተ ክርስትያን ትላልቅ በዓሎች አንዱ የሆነ በዓለ ትስብእቱ ነው፣ ይህም ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ወልደ እግዚአብሔርን እንደምትጸንስና እንደምትወልድ ያበሠራት የሚታወስበት ነው፣ እግዚአብሔር በዚሁ ብሥራት የእመቤታችን ድንግል ማርያም እምነትን እንደአበራና እንደአበረታታ ያመለከቱ ቅዱስነታቸው ለእርሷ ብቻ ሳይሆን እጮኛዋ ወደ ነበረው ቅዱስ ዮሴፍም እንደተላከና ጌ.መ.ኢ.ክ ደንበኛ ቤተሰብ እንዲኖረው ዝግጅት ማድረጉን ገልጠዋል፣

ይህም የሚያመለከተው ወልደ እግዚአብሔር ብምሥጢረ ሥጋዌ መጸነስና መወለድ ብቻ ሳይሆን በደምብ የሚቀበለው ቤተሰብም እንዳሰፈለገው ነው፣ በዛሬው ዕለት ትምህርታችን አብረን ስለዚሁ አስደናቂና ደስ የሚያሰኝ የእግዚአብሔር ዕቅድና ውሳኔ ልናሰላስል እወዳለሁ፣ አብረንም ሰላመ ቅዱስ ገብርኤል መልአክ በመድገም መል አኩ ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ያወረበውን ሰላምታ አብረን እንጸልይ ሲሉ በቦታው ከተገኙና በመገናኛ ብዙኃን አማክኝነት ይከታተልዋቸው ከነበሩ ሁሉ በአንድነት በሰላመ ቅዱስ ገብ ር ኤል ደግመዋል፣

ቅዱስነታቸው በማያያዝ ሌላው በዚሁ ቀን የሚታወስ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሕይወት ቀን መሆኑን አመልክተው በተለይ ከሃያ ዓመታት በፊት ልክ በዚሁ ዕለት ር.ሊ.ጳ ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ኢቫንጀሉም ቪተ የሕይወት ወንጌል የሚለው ሓዋርያዊ መልእክታቸውን ፈርመው በይፋ ያቀረቡበት ዕለትም ነው፣ ይህንን ለማስታወስ ደግሞ በዚሁ አጋጣሚም ሕይወትን ለመከላከል የሚንቀሳቀስ ድርጅት ብዙ አባሎች በአደባባዩ ይገኛሉ፣ የሕይወት ወንጌል ዋና ይዘትና አንኳር ቤተሰብ ነው ምክንያቱም ቤተ ሰብ የሰው ልጅ ሕይወት ማኅጸን ነውና፣ ይህንን በተመለከተ ከኔ በፊት የነበሩ ስመጥርና ልሂቅ ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ የተናገሩት ቃላትም ሚስትና ባል እግዚአብሔር ከመጀመርያው ጀምረው የፍቅርና የሕይወት ማኅበር በማቆም የሰው ልጅ ዘር እንዲቀጥል ባርካቸው፣ እንድናስታውስ ያስፈልጋል፣ ክርስትያኖች በምሥጢረ ተክሊል ይህንን ቡራኬ ለመቀበልና በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ በሞት እስኪለያዩ ድረስ እንዲጠብቁት ዝግጁነታቸውን ይገልጣሉ፣ ቤተ ክርስትያንም በበኩልዋ የሚወለደውን ቤተሰብ እግዚአብሔር ለሕይወት የሚሰጠው ጸጋ መሆኑን በመገንዘብ በደስታ እንድትቀበለውና እንድትንከባከበው በሚመችም ይሁን በማይመች ጊዜ እስከመጨረሻ እንድትረዳው ዝግጁ መሆን አለባት፣ ይህ መተሳሰር ቅዱስና የማይሻር ነው፣ ቤተ ክርስትያን እንደእናት ቤተሰብን በምንም ምክንያት አትተዋትም፤ ችግር ቢያጋጥምም ይሁን ቆስላ በምትገኝበት በምንም ምክንያት አትተዋትም፣ በኃጢአት የወደቀች ብትሆንም ከቤተ ክርስትያን የራቀችም ቤተሰብ ሳይቀር መተው የለባትም፣ የተቻላችን ያህል በማድረግ መንከባከብና መፈወስ ከእግዚአብሔር ጋር ሊመለሱና ሊታረቁ መታገል አለባት፣ ይህንን ተልእኮ በድምብ ለመወጣት ቤተ ክርስትያን ምንኛ ያህል ጸሎት እንደሚያስፈልጋት ግልጽ ስለሆነ በቤተሰብንና በሕይወት ፍቅር የሞላ ጸሎት ያስፈልጋል፣ ከሚደሰት ጋር የሚደሰት ከሚሰቃይ ጋር የሚሰቃይ ጸሎት ያስፈልጋል፣ ስለሆነም ከአማካሪዎችየ ጋር በመሆን በቤተሰብ ዙርያ ለሚካሄደው ሲኖዶስ እንድንጸልይ አስበናል፣ ይህንን ጸሎት እስከ እፊታችን የጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ ሳናቋርጥ እንድናሳርገው፣ ይህ ጸሎት በተለያዩ ምክንያቶች ደክመው የሚገኙ እረኛ እንደሌላቸው በጎች ጠፍተው ላሉ ቤተሰቦች የመልካሙ እረኛ እንክብካቤ የሚያስገኝ እንዲሆን ባለ ብዙ ተስፋ ነኝ፣ እንዲህ በማድረጋችን ደግሞ ቤተ ክርስትያን በእግዚአብሔር ጸጋ ተደግፋና ብርሃነ መንፈስ ቅዱስ አግኝታ እግዚአብሔር ለማንኛውም ቤተሰብ ማንንም ሳያገለልል በበረት ውስጥም ያሉ ይሁኑ ከበረት ውጭ ላሉ ቤተሰቦች ያለውን ፍቅርና ርኅራኄ እውነት ለመመስከር ትችላለች፣ ጸሎት እንዳይጐድል አደራ እላለሁ፣ ይህ አደራ ለሁላችን ነው፤ ለር.ሊ.ጳ ካርዲናሎች ጳጳሳት ካህናት መነኮሳን መነኮሳትና ምእመናን ሁላችን ለሲኖዶስ እንድንጸልይ እንጠራለን፣ ሲሉ ከተማጠኑ በኋላ የተዘጋጀውን ጸሎት በአደባባዩ ከተገኙ ጋር በኅብረት ደገመዋል፣ የጸሎቱ ይዘትም ይህ ነበር፣

“ኢየሱስ ማርያምና የሴፍ በእናንተ የእውነተኛ ፍቅር ብርሃንን እናያለን! በመተማመንም በእናንተ እንማጠናለ፣ የናዝሬቲቱ ቅድስት ቤተሰብ ሆይ! ቤተሰቦቻችን እውነተኛ የወንጌልትምህርትና ትናንሽ የቤት ቤተክርስትያኖች በመሆን የውህደት ቦታዎችና የጸሎት ጽርሓ ጽዮን እንዲሆኑ እርዱን፣ የናዝሬቲቱ ቅድስት ቤተሰብ ሆይ! በቤተሰቦቻችን መከፋፈል ዓመጽና መገለል አውግዱልን! የቆሰለና የተጉዳ እንዳለ ወዲያውኑ መጽናናትና መዳን እንዲያገኝ ይሁን፣ የናዝሬቲቱ ቅድስት ቤተሰብ ሆይ! መጪው የጳጳሳት ሲኖዶስ በእያንዳንዱ ያ የቤተሰብ ቅዱስና የማይሻር መለያ የሆነው በእግዚአብሔር ዕቅድ ውስጥ ያለው ውበት ግንዛቤ ያሳድር፣ ኢየሱስ ማርያምና ዮሴፍ ልመናችንን ስሙን ተቀበሉን አሜን፣








All the contents on this site are copyrighted ©.