2015-03-24 13:02:00

በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ክርስትያን እየተሳደዱ እና ለስቃይ እየተዳረጉ መሆናቸው ተገለጠ


በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ክርስትያን እየተሳደዱ እና ለስቃይ እየተዳረጉ መሆናቸው በተለይ በመካለኛው ምስራቅ የሚገኙ ክርስትያን ማሕበረ ሰቦች በአሳሳቢ ሁኔታ እንደሚገኙ በጀና ስዊትጸላንድ በሚገኙ የተባበሩት መንግስታት ተቋሞች የቅድስት መንበር ቀዋሚ ታዛቢ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሲልቫኖ ማሪያ ቶማሲ ጀነቭ ላይ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ምክር ቤት ስብሰባ ተገኝተው መግለጣቸው ከቦታው የደረሰ ዜና አስታወቀዋል።

ዓለም አቀፍ ማሕበረ ሰብ በክርስትያኖች ላይ አየተፈጸመ ያለውን ማሳደድ እና ማሳቃየት ለመግታት ሁኔኛ ርምጃ የሚወስድበት ግዜ አሁን መሆኑ ሊቀ ጳጳሱ አጽንኦት ሰጥተው ማሳሰባቸው ዜናው አክሎ አመልክተዋል።

የተባበሩት መንግስታት ዓለም አቅፍ ድርጅት ሃይማኖትን ወይም ፖሊቲካ አሳበው በህዝቦች ላይ ዓመጽ የሚፈጽሙ ድርጅቶች ቡድኖች እና ግለ ሰቦች ለይቶ በማወቅ አስፈላጊው ርምጃ እንዲወስድ እና የዚሁ ዓመጽ ሰለባ ለሆኑ ሁሉ ተገን እንዲሰጥ በተባበሩት መንግስታት ተቋማት  የቅድስት መንበር ልዩ ታዛቢ ብፁዕ  አቡነ ሲልቫኖ ማሪያ ቶማሲ  ለስብሰባው መናገራቸው ዜናው  ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.