2015-03-23 16:11:00

በስዊድን የሕብረት ጸሎት በስደት ለሚገኙ ክርስቲያኖች እንደሚካሄድ ተገለፀ


የስዊድን ክርስቲያኖች ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ኻሪን ዊብሮን ጸሎት የመጀመሪያው የሃይል ምንጭ ለክርስቲያኖች መሆኑን በማሳሰብ እንዲሁም ፊታችን እሁድ በሚከበረው የሆሳዕና በዓል ላይ የተለያዩ የክርስቲያን ሃይማኖቶች አንድነት በሕብረት በመካከለኛው ምስራቅ በስደት ላይ ለሚገኙ ክርስቲያኖች የሕብረት ጸሎት እንዲደረግ አሳስበዋል::

እንዲሁም የቀድሞዋን የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያን ምዕመናን ወገኖቻቸው ለሚገኙበትና ለደረሰባቸው ችግር ስጋታቸውን ገልጠዋል። ጸሎት ሁሉንም መቀየር እንደሚችልና በስዊድን የሚገኙ  አብያተ ክርስቲያናትና የተለያዩ ማኅበረሰቦች በሕብረት ጸሎት ቢፈጸም በእርግጠኝነት የጸሎቱን መልስ እንደሚያገኙ አመልክተዋል።  

ብዙዎች የስዊድን አብያተ ክርስቲያን ምዕመናን በመካከለኛው ምስራቅ በመገኘት በጦርነቱና በስደቱ የተጎሳቁሉትን በመርዳት እንደሚገኙ ሲያመልክቱ ይሁን እንጂ በቦታው ተገኝቶ የሚገባውን እርዳታ መስጠትም አስቸጋሪ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በመጨረሻም የስዊድን አብያተ ክርስቲያን ለከፍተኛ  ባለስልጣኖች በሕብረተሰባችን የሓይማኖት ነፃነት  ሰላምና ፍትህ እንዲከበር የአደራ ጥሪን ሲያቀርቡ እንዲሁም በቅርቡ ከስዊዲን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በመገናኘትና በመመካከር የሃማኖት ነፃነት በሌሎች አገሮችም እንዲከበር ቅስቀሳ እንዲደረግ አበረታተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.