2015-03-23 14:56:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ የወንጀል ቡድኖችና ወንጀለኞች ተለወጡ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በናፖሊ ከተማ በሚገኘው በፕለቢሺቶ አደባባይ በብዙ ሺሕ የሚገመት የካምፓኒያ ክፍለ ሃገር ነዋሪ ሕዝብ የተሳተፈበት መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው “ልብን ለቃለ ወንጌል መክፈት ሲጀመር ሁሉ በኅዳሴና በለውጥ ጎዳና መራመድ ይጀምራል።

ሰብአዊነት ይፈልቃል፣ ዳግም ይነሣል፣ የኢየሱስ ቃል በሁላችን ልብ ሊደርስ ይፈልጋል፣ በተለይ ደግሞ በእነዚያ በከተሞቻችን ጥጋ ጥግ ክፍለ ከተማ ብኅልውና ዳርጃ በሚገኙት ልብ ውስጥ ማረፊያ ለማግኘት ይፈልጋል፣ ናፖሊ የላቀ መንፈሳዊ ባህላዊ ሰብአዊ እምቅ ኃይል የተካነች ከተማ ነች፣ በተለይ ደግሞ ሰብአዊ ፍቅር የተካነች ከተማ ነች፣ በዓለማችን የሚታዩት ከተሞች ተምሳል ነች፣ ሁሉም ያው ነው፣ መለወጥና መታደስ አይቻልም ብሎ ተስፋ ቆርጦ እጅን አጣምሮ መቀመጥ አያስፈልግም። ብሩህና የበለጠ መጻኢ ለመገንባት ለብሩህ መጻኢ ታማኝ በመሆኑ ገዛ እራስ መክፈት፣ ለቀቢጸ ተስፋነት እጅ አለ መስጠተ” የሚል ሃሳብ ያሰመሩበት ስብከት መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አመደዮ ሎሞናኮ ገለጡ”

“ውዶቼ ተስፋ እንዲሰረቅባቸሁ አትፍቀዱ። ባቋራጭ መንገድ ሃብት ለማካበት በሚያስችል የጥፋት መንገድ አትማረኩ። በዚህ ባቋራጭ መንገድ የሚገኘው ዕለታዊ እንጀራ፣ የነገውን እርሃብ ያረገዘ ሁነት ነው። የነገ እርሃብ ይሆናል፣ በጸና የብዝበዛ ሥልት፣ ወጣቶችን ድኾችን ለስቃይ የሚዳርግ ሥልት ሁሉ ተቃወሙ። መጻኢ ሕይወት ከወዲሁ ለሚቀጩ የሴሴኝነት የሙስና የወንጀል ቡድን አባል ከመሆን ተግባር ተቆጠቡ፣ እኔም ቤተ ክርስቲያንም ደጋግመን የወንጀል ቡድኖች ተለወጡ፣ ከጥፋት መንገድ ራቁ ወደ ፍቅር ወደ ፍትህ ተለወጡ በማለት ጥሪ እናቀርባለን” እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሎሞናኮ አያይዘው፦ “ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉን በተለይ ደግሞ የጠፉትን ኃጢአተኞችን ይፈልጋል። በእግዚአብሔር ምኅረት ትገኙና ትማረኩም ዘንድ ገዛ እራሳችሁ ፍቀዱ። ያለፈው ሕይወታችንን የማይመለከት አምላክ ነው ያለን። ኢየሱስ ይፈልገናል፣ ዘወትር ይምረናል፣ ሐጢአታችን ሁሉ ይምራል፣ እናንተ የወንጀል ቡድኖች ከዚያ ከቅድስት እናት ማርያም እንባ ጋር የተቀላቀለው የናፖሊ እናቶች እንባ ከጥፋት መንገድ ተመለሱ ተለወጡ ይላል፣ ይኽ እንባ የደነደነው ልባችሁ ያረስርስ ወደ መልካም ጎደና ይምራችሁ” እንዳሉ አስታወቁ።

“የኢየሱስ ቃል ዓለምን ይለውጣል፣ የልብ ቁስሎቻችን ይፈውሳል፣ ቃሉ ኃያል ነው። የዓለም ኃይል ሳይሆን የእግዚአብሔር ኃይል የተሞላ ቃል ነው። የእግዚአብሔር ኃይል። ድንበር የለሽ ሁሉን የሚያፈቅር ሌሎችን ለማፍቅር የሚያበቃን ፍቅር ነው። ኃይሉም ይኽ ነው። የኢየሱስ ቃል፣ ድኾች የዋሆች ዓመጽ የማይከተሉ፣ የሰላምና የፍትህ አገልጋዮች ናቸው በማለት ብፁዓን ይላቸዋል፣ ይኽ ነው ዓለምን የሚለውጥ ኃይል። ከጠባቡ ቅጥር ግቢ ወጣ ብሎ ሌላውን ድኻውን ማስተናገድ፣ ከገዛ እራስ መውጣትና መሄድ የቤተ ክርስቲያን የልብ ትርታዎች ናቸው፣ ወደ ሁሉ መሄድ የእግዚአብሔር ምኅረት ፍቅር የዋህይነት ጓደኝነት ማወጅ፣ ቁምስናዎች ሁሉ እግዚአብአብሔርን ለሚፈልጉ ድኾች አረጋውያን በጠና ችግር ለሚገኙት ሁሉ ቤተ መቅደስ ሆነው መገኘት ይኖርባቸዋል፣ የናፖሊ ከተማ ከዚያ ሁሉን ነገር አዲስ ከሚያደረገው ከኢየሱስ ክርስቶስ ምኅረት በተስፋ ወደ ፊት ለማለት የሚያነቃቃ ኃይል ታግኝ። ተስፋ ማድረግ የክፋት መንፈስና የክፋት መንገድ እንቢ ለማለት የመጀመሪያ እርምጃ ነው። ዓለምን በእግዚአብሔር ዓይንና ልብ መመልከት ማለት ነው። ተስፋ ማድረግ በእግዚአብሔር ምኅረት እማኔ ማኖር ማለት ነው” ያሉት ቅዱስ አባታችን “የደስታችንና የተስፋችን ምንጭ የሆነው እግዚአብሔር በከተሞቻችን ይኖራል፣ እግዚአብሔር በናፖሊ ይኖራል” በማለት የለገሱት ስብከት እንዳጠቃለሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አመደዮ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.