2015-03-17 16:27:00

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ልዩ የምሕረት ዓመት ኢዮቤልዩ አውጀዋል።


 

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ልዩ የምሕረት ዓመት ኢዮቤልዩ  አውጀዋል። ቅድስነታቸው ይህንን ያወጁ በቅዱስ ጰጥሮስ ባሲሊክ የንሥሐ መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉበት ግዜ ነው።በዚሁ የንስሐ መስዋዕተ ቅዳሴ የተሳተፉ ውሉደ ክህነት እና ምእመናን ዓዋጁ በጭብጨባ እና በደስታ ተቀብለውታል።

የእግዚአብሔር ምሕረት ተወዳዳሪ የሌለው እሴት መሆኑ እና ኢየሱስ ክርስቶስ በዓቢይ ፍቅር እንደሚመለከተን ሐጢአተኛ ልባችን እንደሚፈውስ ቅድስነታቸው አስገንዝበዋል።

የእግዚአብሔር ምሕረት ማእከል ያደረገ ልዩ እዮቤልዩ ለማወጅ ወሰንኩኝ ያሉት ቅድስነታቸው የምሕረት ቅዱስ ዓመት ይሆናል በማለት ገልጠውታል ።

እንደ እግዚአብሔት መሀሪዎች ሁኑ ያለውን ክርስቶስ ተንተርሰን ዓመተ ምሕረት ኢዮቤልዩ በደስታ እናሳልፈዋለን ያልይ ቅድስነታቸው ኤዮበልዩ ፊታችን ታሕሳስ ወር ስምንት ቀን ጎርጎርዮሳዊ አቁጣጠር በሚውለው የቅድስት ንጽህት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ክብረ  በዓል ተጀምሮ በ20016 ሕዳር ወር  ሀያ ቀን  እሁድ የእግዚአብሔር ምሕረት አንጸባራቂ የሆነውን የአድማስ  ሁሉ ንጉስ ኢየስሱስ ክርቶስ በዓል እንድፈሚጠቃለል  አስታውቀዋል።

የምሕረት ኢዮቤልዩ የቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የምስክርነት ተልእኮ በበለጠ ገሀድ የሚያደርግ ኢዮቤልዩ እንደሆነም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አመልክተዋል።

የዚሁ ኢዮቤልዩ አዘጋጅ የአዲስ ቅዱስ ወንጌል ስብከት ጳጳሳዊ ምክር ቤት ኢዮቤልዩ እንደ አዲስ የቤተ ክርስትያን ምዕራፍ በመመልከት የቅዱስ ወንጌል ምሕረት ለሁሉም እንዲዳረስ ያደርግ ዘንድ በመጠየቅ ቤተ ክርስትያንም ራስዋ እና ሁላችን ሐጢአተኞች ምሕረቱ የምንጠይቅበት ኢዮቤልዩ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በቅዱስ ጰጥሮስ ባሲሊክ የንስሐ መስዋዕተ ቅዳሴ ባሳረጉበት ግዜ ያሰሙት ስብከት በሙሉ የምሕረት ኢዮቤልዩ ትኩረት የሰጠ የነበረ ሲሆን ፡ ቅዱስ መጽሐፍ የተስፋ ጉዞ ይከፍትልናል ብለው ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ ጠቅሰው እግዚአብሔር በዘመናት ሁሉ ምሕረቱ ከመስጠት ፍጹም እንደማይቆጠብ በማስታወስ እና ቅዱስ መጽሐፍን ተንተርሰው ስብከታቸውን በማያያዝ፡ አንድ ሴት የኢየሱስ ክርስቶስን እግሮች በማጠብ እና በጠግርዋ በማደረቅ እግሩን ስማ ሽቶ እንደቀባችው የቤቱ ባለቤት ስምዖን ሴትዮውን ሐጢአተና መሆንዋ መፍረዱ በማስታወስ ፍቅርና ፍርድ ሲሉ ሰብከዋል።

ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሴትየዋ የምሕረት መጠየቅ ዝንባሌ ተመልክቶ የእግዚአብሔር ምሕረት አሳያት ሰጣት ፍቅርና ምሕረት ከፍትሕ በላይ መሆኑ ለመገንዝብ እንችላለን በማለት ስብከዋል ቅድስነታቸው።

በማያያዝም ፋሪሰይ ስሞዖን የፍቅር መንገድ ስቶ ፍትሕ ብቻ ጠየቀ በሰትዮ ላይ የነበረውን አመለካከት ከሐቅ እንዲርቅ አደረገው ልቡን አላዳም አጠም ማንም ሰው ክእግዚአብሔር ምሕረት ውጭ ሊሆን እንደማይችል እንገነዘባለን ቃል ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት  ፍራንሲስ። ቤተ ክርስትያን  የሁሉ ፍጥረ ሰው ቤት መሆንዋ እና በሮችዋ ለሁሉ ክፍት መሆኑ  የምሕረት ጠያቂዎች ቤት በመሆን የጌታን መድኀኒታችን ሚስጢራት ለመስጠት ዝግጁ መሆንዋ በማምልከት ፉታችን ታሕሳስ ወር ስምንት ቀን እኤአ የቅዱስ ጰጥሮስ ካተድራል ቅዱስ በር ክፍት እንደሚሆን አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.