2015-03-17 16:41:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንሲስ በፓኪስታን ላሆር ላይ በክርስትያኖች የተፈጸመው ጥቃት በእጅጉ እንዳሳዘናቸው


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ፍራንሲስ ወትሮ እንደ ሚያደርጉት ሁሉ ትናትና በቅዱ ጰጥሮስ አደባባይ ከተገኙ ምእመናን እና ሀገር ጐብኝዎች ጋር እኩለ ቀን ላይ እሁዳዊ መልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ደግመዋል።

ቅድስነታቸው ከመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ፍጻሜ በኃላ በፓኪስታን ላሆር ላይ በክርስትያኖች የተፈጸመው ጥቃት በእጅጉ እንዳሳዘናቸው አጽንኦት ሰጥተው ገልጠዋል።

ዓለም በክርስትያኖች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ማሳደድ እንደሚደብቅ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጠቅሰው ጥቃቱ እና ማሳደዱ እንዲገታ አሳስበዋል።

ጀምዓት ኡል/አሕራር የተባለ ቡድን በፓኪስታን ላሆር ከተማ ላይ በአንድ ካቶሊካዊ እና ፕሮተስታንት አብያተ ክርስትያናት ጥቃት ፈጽሞ ቢያንስ 14 ክርስትያኖች መግደሉ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኀን አስታውቀዋል። አክራሪ ቡድኑ ለተፈጸመው ጥቃት ሐላፊነት መወስዱ መገናኛ ብዙኀኑ አስገንበዋል።

ይሁን እና ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በፓኪስታን ላሆር ላይ በክርስትያኖች ላይ የተፈጸመው ጥቃት እና ያስከተለው የሰው ሕይወት ጥፋት በማስመልከት

በፓኪስታን ላሆር ላይ በክርስትያኖች ላይ ጥቃት መፈጸሙ እንደተረዳሁ ጥልቅ ሐዘን ተሰምቶኛል፡ ጥቃቱ ለሰዎች ሕልፈት እና ቁስል አዳርገዋል።

ክርስትያኖች እየተሳደዱ ይገኛሉ፡ ክርስትያን በመሆናቸው ብቻ ደማቸው እየፈሰሰ ነው ለሕልፈት ለተዳረጉ እና ለቤተ ሰቦቻቸው እግዚአብሔር ጥናቱ እንዲሰጠጣቸው እጸልያለሁ እንድዲሁም ፓኪስታን ላይ ሰለም እንዲወርድ እንጸልይ በማለት ምእመናን ጠይቀዋል።

ኤስያ ኒውስ የተባለ የዜና አገልግሎት ዳይረክተር አባ በርናርዶ ቸርቨለራ በፓኪስታን በክርስትያኖች ላይ የተቃጣው ጥቃት ትኩረት በመስጠት ሲገልጡ፡ ዜናው አስደንጋጭ ነው ሁለት ጣሊባኖች ኀይል ተጠቅመው አብያተ ክርስትያናቱ ውስጥ ለመግባት ሲሞክሩ ከፖሊስ ጋር እንደተጋጩ መረጃ እንዳላቸው እና  ውስጥ ገብተው ቢሆኑ ኖሮ ሁኔታው የከፋ በሆነ ነበር ብለዋል።

በአብያተ ክርስትያናቱ አቅራብያ የነበሩ በርካታ ፓሊስ የክሪከት ጨወታ በተለቪዥን መስኮት ለመከታተል ወደ አንድ ባር በመሄዳቸው የጸጥታ ክፍተት በመኖሩ አሸባሪዎቹ 14 ሰባት ለመግደል መቻላቸውም አክለው ገልጠዋል።

የፓንጃብ ክፍለ ሀገር ፖሊስ ለክርስትያኖች ጥበቃ እንዲሰጥ የክርስትያን ማሕበረ ሰቦች ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዳቸው ጣሊባኖች በዚሁ ክልል በክርስትያኖች ላይ ቀጣይ ጥቃት እንደሚፈጽሙ የኤስያ ኒውስ ዜና አገልግሎት ዳይረክተር አመልክተዋል።

በሰሜናዊ ፓኪስታን የመሽገው የጣልባን ቡድን በክርስትያኖች ብቻ ሳይሆን በሺዒቲ ማሕበረ ሰብም ተመሳሳይ ጥቃት እንደሚፈጽምዳይረክተሩ ጠቅሰው የፓኪስታን መንግስት አሸባሪዎችን ለመግታት ሁነኛ ርምጃ ከመውሰድ የተቁጠበ እንደሚመስላቸውም አክለው አስገንዝበዋል።

በአጠቃላይ በኤስያ ክፍለ ዓለም የክርስትያኖች ሁኔታ ከግዜ ወደ ግዜ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱም የኤስያ ኒውስ ዜና አገልግሎት ዳይረክተር ይናገራሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.