2015-03-16 17:11:00

ክርስቶስ ለምናበረክተውና ለምንሰጠው የፍቅር አገልግሎት የልባችን ማዕከልና ምንጭ እንዲሆን አሳሰቡ


ወንጌልን በድፍረት መመስከር የጠንካራ ክርስቲያን እምነት ምልክት ነው ሲሉ ቅዱስ አባታችን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ በትላንት ዕለት ተከተለኝ ተብሎ የሚጠራው የአለማዊያን ምዕመናዊያን ግብረ ሰናይ ማህበር 50 ዓመት ኽብረ በዓል ላይ አመለከቱ። ይህ የግብረ ሰናይ ማህበር በ11 ሃገሮች በመገኘት አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገለፀ።

በ2ኛ የቫቲካን ጉባኤ ላይ የዛሬ 50 ዓመት ቤተክርስቲያን ለአለማዊያን ምዕመኖችዋ በቤተክርስቲያን አገልግሎት በመስጠት እንዲስፋፉ በሮችዋን ስትከፍት ይሕም ወንጌል በቤተሰብ፤ በመስሪያ ቤትና፤ በማኅበራዊ ኑሮ ላይ እንዲስፋፋ ነበር። ዛሬ ከ 50 ዓመት በውሃላ ተከተለኝ ተብሎ የሚጠራው የግብረ ሰናይ ማህበር 400 ማኅበርተኞች እንዳሉትና በትላንት እለት በተካሄደው ስርዓተ ቅዳሴ ላይ ከግማሽ ማኅበርተኞች በላይ ከቅዱስ አባታችን ጋር በመገኘት ስርዓተ ቅዳሴው ላይ መሳተፋቸው ተገለፃል።

ቅዱስነታቸው ለተከተለኝ  ግብረ ሰናይ ማኅበር ተግባሩን ሳይሆን በቀዳምነት ክርስቶስን የሁሉም ማዕከል ምንጭ በማድረግ የሕይወት መመሪያ  ቃል  የሕይወታቸውና  የአግልግሎታቸው አስተዋጾ ተግባር መሆኑና ማየቱ በጣም ያማረና ደስ የሚያሰኝ መሆኑን በመጥቀስ ይህም በታማኝነት በወንጌል የተጻፈውን በተግባር ላይ በማዋል የተዘራው ፍሬ ፈርቶ  በተለያዩ የግብረ ሰናይ ማኅበራት የሚሰጠው አስተዋጾን ማየቱን እጅግ አመስግነዋል።  እውነተኛ ክርስቲያን ቀዳማዊ የሕይወቱ ማዕከል  ክርስቶስ መሆኑን በማስገንዘብ ከሁሉም በላይ የህይወታችንን  ልብ የሚቀይረው  መንፈስ ቅዱስ መሆኑን አሳስበዋል። ክርስቶስ በልባችን ገብቶ መስራት እንዲችል እንጋብዘው እንዲሁም ከክርስቶስ ጋር አብረን በሕብረት ጠንክረን  ከቆምን እንደ የተክል ስር ቅርንጫፎች ካካባቢያችን በመውጣት በአለም ዙሪያ በችግር የሚገኙትን ሄደን መርዳትና ክርስቶስን መመስከር የግብረ ሰናይ አገልግሎትም ለደከሙ ተስፋ መሆኑን በማብራራት  ሌሎችን መርዳት እንደሚቻል አመልክተዋል።

ቅዱስነታቸው በማያያዝ  የግብረሰናይ ማኅበርተኞች ዓለማዊያን ወንድሞችና እህቶች በትዳር የሚኙትንም ይሁን ነጠላ ቤተሰቦች በሕብረት ሆነው ለሚሰጡትና ለሚያደርጉት የሕብረት ተሞክሮ ሕይወት ያንዱን ባዶነት ሌላው እንደሚሞላው በመግለፅ ይህ የወንድሟሟችነት ሕብረትና ፍቅር ስጦታን ለማሳደግና የክርስትና የሕይወት ጉዛቸውን ነቅተው እንዲጠብቁና  ጠንቅቀው እንዲይዙ አደራ ሲሉ ይሕም ለሰብዓዊ እድገትና ደስታ ክርስቲያኖችን በሙሉ በሕብረት እንደሚያጠናክር በማሳሰብ እንዲሁም አንዱ ሌላውን እንዲረዳ አደራ ሲሉ ከራስ ወዳድነት በመውጣት ለ እውነተኛ ወንጌል ምስክርነት መዘጋጀት እንዳለብን አሳስበዋል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.