2015-03-13 18:54:00

እግዚአብሔር የማይምረው ኃጢአት የለም፤


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍርናቸስኮስ ትናንትና በሮም ምሥጢረ ንስሓን ለመረዳትና በተገቢ መንገድ እንዲሠሩት ለመማር ተሰብስበው ለሰነበቱት አዳዲስ ካህናት ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት “ምሥጢረ ኑዛዜ ከባድ የወንጀል ምርመራ ወይንም የሚያሰቃይ ጥያቄ ሳይሆን የእግዚአብሔር ወደር የለሽ ምሕረትና ይቅር ባይነት የሚገለጥበት ምሥጢር ነው” ሲሉ አሳስበዋል፣

ሶሙኑን ለአዳዲስ ካህናት ሲያተምሩ የነበሩ አባቶች እና በግንኝቱ የተገኙ ለቅዱስነታቸው ታላቅ ጭብጨባ በማቅረብ ሰላምታ ባቀረቡበት ወቅት አጋጣሚውን በመጠቀም ቅዱስነታቸው ገዳም ገበተው የመጀመርያ ማኃላ ካደረጉ ትናንትና 57ኛ ዓመታቸው መሆኑንም በታላቅ ደስታ ገልጠዋል፣

ቅዱስነታቸው ደጋግመው እንደገለጡት ቅዱሳት ምሥጢራት እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ያለውን ፍቅር የሚገልጡና ደካማዎችና ኃጢአተኞች በመሆናችንስ ይሁን እጅግ የተወሰንን በመሆናችን ሳያፍር እግዚአብሔር በተጨባጭ ሊያቅፈንና ፍቅሩን ሊገልጥልን የለገሰልን የጸጋ ምንጭ መሆናቸውን ካሳሰቡ በኋላ በተለይ ምሥጢረ ንስሓ የእግዚአብሔር ርኅራኄና ይቅር ባይነት ልዩ በሆነ መንገድ በመካከላችን እውን ያደርገዋል ብለዋል፣

ለሁላችን አደራ ለማለት የፈለጉት ደግሞ የሚናዘዝም ይሁን የሚያናዝዝ ማስታወስ ያለበት እግዚአብሔር ይቅር የማይለው ኅጢአት እንደሌለ ነው፣ ጌታ እንዳለው ይህንን ምሕረት አልቀበልም ብሎ ገዛ ራሱን ያገለለ ልክ ከጸሓይ ራሱን ያገለለ ሊሞቅና ሊበራለት እንደማይቻል ሁሉ ከምሕረት ራሱ ያገለለ ብቻ ነው ምሕረት ሊቀበል የማይችለው፣ ምእመናን ከመንበረ ኑዛዜ ሲመለሱ ምሕረት ተቀብለው ልባቸው በደስታ እንዲሞላ ይሁን፣ ይህንን ለማድረግ የንስሓ አባቶች ማድረግ ያለባቸው ሶስት ነገሮች እንዲህ ሲሉ ዘርዝረዋል፣ በመጀመርያ ምሥጢረ ኑዛዜ ለመለኮታዊ ምሕረት እንደሚያዘጋጅ ትምህርት ሊጠቀሙት ያስፈልጋል፤ ይህ ማለትም ውለደ ንስሓን ወይንም ምእመናንን የእግዚአብሔር ሰላምንና ርኅራኄን በሰብአዊ መንገድና በክርስትያናዊ መንገድ እንዲያጣጥሙት ሊረድዋቸው አደራ ብለዋል፣ በሁለተኛ ደረጃ ኑዛዜ አስፈሪ አሳፋሪ ሥቃይ ውስጥ የሚከት መሆን የለበትም ነገር ግን ከመንበረ ኑዛዜ የሚመለሱ ሁላቸው በተስፋ ያሸብረቀ ገጽታና በደስታ የሞላ ልብ ይዘው መመለስ አለባቸው፣ በወንጌል ደስታ የሚለው ሓዋርያዊ ምዕዳን ቍ 44 ላይ እንደተመለከተውም በንስሓና ለውጥ እምባ እንዲሁም ከዚህ ምሥጢር በሚገኘው ደስታ መሞላት አለባቸው፣ እንጂ እንደ አንድ የፖሊስ ምርመራ ማእከል ከባድ ቃለ መጠይቅና አድካሚ ምርመራ የሚደረግበት ቦታ እንዳይሆን አደራ ብለዋል፣ በዚሁ አንጻር የምሥጢረ ንስሓ ግኑኝነት ነጻነት የሚያለብስና ሰብአውነት የሞላበት ሆኖ የተቻለውን ያህል የተፈጸመውን ጥፋት ለማካካስ የሚጣርበት ሲሆን ምእመኑ ተመላልሶ ለመናዘዝም አይቸገርም፣ ጥሪ እንደቀረበለት ዓይነት ሆኖም ይሰማዋል፣ እንዲህ በማድረጉ አበነፍሱም ደስ ይለዋል፣ አለበለዚያ ቸልተኛ አናዛዥም ይሁን ጨካኝና ደረቅ አናዛዥ የምሕረት መሳርያ ሊሆኑ አይችሉም፣ ስለዚህ በመካነ ኑዛዜ ለለውጥና ለምሕረት የሚያዘጋጅ ንግግርና መደማመጥ መዘውተር ያስፈልጋል፣ የመልካሙ እረኛና የጠፋች በግ ምሳሌ ማስታወስ ያስፈልጋል፣ አበነፍሶች በመንፈስ ገንቢ የሆኑ ኑዛዜዎችም ሊያጋጥምዋቸው ስለሚችሉ ይህንንም መጠቀም እንዳለባቸው አሳስበዋል፣ በሌላ በኩል ደግሞ በወንጌሉ ተመልክቶ እንዳለው የታናሹ ልጅ ምሳሌ ለብዙ ጊዜ ጠፍተው የነበሩ እንደገና ወደ አባታቸው ቤት ወደ ምሥጢረ ኑዛዜ ሲመለሱም እንመለከታለን፣ እንዲህ ዓይነት ሰዎች ስንቀበልም ይሁን ብዙ መንፈሳውያን ሰዎች ስናናዝዝ ካህናትም የኅልና መርመራ ማድረግ አለብን፣ ሲሉ ምሥጢረ ኑዛዜ ለሁሉም መንፈሳዊ ፈውስ መሆኑ ገልጠዋል፣

በሶስተኛ ደረጃም በአበ ነፍስና በውሉደ ንስሓ ያለው ግኑኝነት እጅግ ብርቱ በመሆኑ ሁሉ ስለሰማያዊ ነገር ማሰብ ማንም ሰው በምሥጢረ ኑዛዜ በብቃቱና በችሎታው እንዳልቆመ በመረዳት የሌሎችን የሕይወት ኑሮ ድንበር በምንነካበት ጊዜ ቅዱስ ነገር ስለሆነ ልክ ሙሴ በሲና ጫማው እንዳወለቀው በዚህም ጉዳይ በታላቅ ትሕትናና መንፈሳውነት ልናደርገው እንደሚገባ አሳስበዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.