2015-03-02 15:06:48

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ገንዘብ ለሰው ልጅ አገልግሎት


RealAudioMP3 እ.ኢ.አ. የካቲት 28 ቀን 2015 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በጠቅላላ ከሰባት ሺህ በላይ የሚገመቱት የኢጣሊያ የትብብር ፈደራላዊ ማኅበራት አባላት በአገረ ቫቲካን በሚገኘው ጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ ተቀብለው መሪ ቃል መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጃዳ አኵይላኒ አስታወቁ።
“ገንዘብ እንደ ጣዖት ሲመለክና ሰውን የሚያዝ ከሆነ የውድቀት ምክንያት ይሆናል፣ ስለዚህ ዛሬ የሚያስፈልገው ለሰውን ልጅ በሙላት እድገት ለማጎናጸፍ የሚያበቃ አዲስ የኤኮኖሚ ሥልት ነው። ለሰው ልጅ ምሉእ እድገት የሚደግፍ በቂ ገቢ ያስፈልጋል፣ ነገር ግን ገቢ ለብቻው በቂ ሊሆን አይችልም” በማለት ያብራሩት ቅዱስ አባታችን እ.ኤ.አ. በ 1800 ዓመታት የገበሬዎች ማኅበራት የድጋፍና የእድገት ደጋፍያን ማህበራት ብሎም የአበዳሪ ማኅብራት በካህናት በቆሞሶች ለሕብረተሰብ ለጋራ ጥቅምና የመደጋፈ ባህል መስፋፋት ይኽም አንድም ለብቻው ሳይተው ሁሉም ወደ እድገት ጎዳና እንዲያቀና ታልሞ ለመቋቋም የጀመረ መሆኑ አስታውሰው፣ ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ “ትርፍ እንደ ጣዖት ሳይሆን የንግድ፣ የኤኮኖሚ አውታሮችንና ድርጅቶች ሂደትና ተግባር መለክያ ብሶል መሆን ይገባዋል፣ ይኽ ደግሞ ኤኮኖሚ ጸጋ መሆኑ ያረጋግጥልናል” ያሉትን ሃሳብ የጠቀሱት ቅዱስ አባታችን ገንዘብ ጣዖት ከሆነና የሰውን ልጅ ምርጫዎች የሚያዝ ከሆነ ለሰው ልጅ ጉዳትና ወደ ውድቀትም በመምራት ተገዥ ያደርገዋል፣ ገንዘብ በርግጥ በቅንነትና በትክክል የተጠቀምንበት ከሆን ለሕይወት የሚያስፈልግ መገልገያ መሣሪያ ይሆናል፣ ይኸንን ስንገንዘብ ምጣኔ ኃብት ለሰው ልጅ እንጂ፣ የሰው ልጅ ለምጣኔ ኃብት አለ መሆኑ እንደምንረዳም አብራርተው፣ በአሁኑ ሰዓት በዓለማችን ክልል የሚታየው የጥቁር ሥራ እርሱም የሠራተኛ መብትና ክብር የማይጠብቅ ሰውን የማያከበር፣ አሠሪዎችና ባለ ሃብቶች ኃብት ለማካበት የሚገለገሉበት ሕገ ወጥ ተግባር መሆኑና፣ ለጥሮታ አበል የሚከፈለው ገንዘብ ለገዛ እራስ ጥቅም በማዋል የሠረተኛው መጻኢ የሚቀጭ የከፋ የኃጢአት ተግባር ነው፣ የሥራ አጥነት ችግር ተገን በማድረግ ሥራ ፈላጊው አለ መብትና ክብር መቅጠር የተለመደው ጸረ ሰብአዊ ተግባር በዓለም ዙሪያ ተስፋፍቶ እንደሚገኝ ገልጠው፣ ቅዱስ ባሲሊዮስ ዘቄሳሪያና ቅዱስ ፍራንቸስኮስንም ጠቅሰው ገንዘብ በቀላሉ የዲያብሎስ መገልገያ ሊሆን ይችላል፣ እንዲህ በመሆኑም የሰው ልጅ ለባርነት እንዳይሆን የሰው ልጅ የሚገለገልበት መሣሪያ ለተሟላ እድገት የሚበጅ ማንም በማይነጥል ደምብ መተዳደር ይኖርበታል፣ የገንዘብ ሃብት ለማካበት ያቀና የዓለማዊነት ትሥሥር ማረጋገጥ ሳይሆን ትብብርና መደጋገፍ የሚል በእሴቶች ላይ የጸና ዓለማዊነት ትሥሥር ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ማብራራታቸው አኵይላኒ ገለጡ።
“የኤኮኖሚ ማእከል ሰው እንጂ የገንዘብ ሃብት መሆን የለበትም” ፦ የጤና ጥበቃ የድጎማ ኤኮኖሚ ሂደት በአሁኑ ወቅት የሚታየው ሰውን ማእከል ያላደረገ የኤኮኖሚ ሂደት የሚገለገልበት ሥልት የሰው ልጅ ለአደጋ ተጋልጦ፣ መብትና ክብር ሳይሆን የገንዘብ ሃብት ማካባት ፍላጎት አመዝኖ ይታያል፣ ር.ሊ.ጳ. ሊዮነ አስራ ሦስተኛ፦ ክርስትና የሚያስደንቅ ሰብአዊ ሃብት ነው በማለት የገለጡት ሃሳብ ቅዱስነታቸው አስታውሰው፣ ሃብት የኤኮኖሚ ሥልት የሚያስተካክል መሆን አለበት እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አኵይላኒ አክለው፦ የኤኮኖሚ ሥልት የሰው ልጅ መሠረታዊ አስፈላጊ ነገሮችን ለሟሟላት የሚደግፍ መሆን አለበት፣ የጤና ጥበቃ፣ ትምህርት፣ ሥራ፣ የተሟላ እድገት የማግኘት መብት የሚያረጋግጥ መሣሪያ መሆን ይገባዋል፣ ለቤተሰብ ድጋፍ የሚል የሠራተኛው የተገባና የተስተካከለ የደሞዝ ክፍያ የሚል በግብረ ገብና በሥነ ምግባር የተካነ ቅን ኤኮኖሚ እንዲረጋገጥ ቅዱስ አባታችን አደራ ብለው የትብብርና የድጋፍ ድርጅቶች ሰው ልጅ ማእከል ያደረገ የኤኮኖሚ ሂደት መተባበርና በመደጋገፍ ቅን ኤኮኖሚ ለማረጋገጥ የሚበጁ እሴቶች በመከተል ቅን ኅብረተሰብ ለማነጽ በሚደረገው ጥረተ አቢይ ኃላፊነት እንዳለባቸውና የትብብርና የመደጋገፍ ተጨባጭ ምስክር ሆነው እንድገኙ አሳስበው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.