2015-02-13 16:28:16

ኡጋንዳ፦ ብፁዕ ኣቡነጁዘፐ ፍራንዘሊ፣ ሕፃናት ከውትድርናው ዓለም እናድን


እ.ኤ.አ. የካቲት 12 ቀን 2015 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ የጸረ ሕፃናት በውትድርናው ዓለም ቀን ታስቦ መዋሉ ሲገለጥ፣ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ሕፃናት ለተለያዩ ግጭቶች መገልገያ መሣሪያ እንዲሆኑ ታልሞ በውትድርናው ዓለም የማካተቱ ተግባር ከፍ እያለ መምጣቱ የሚያትቱ የተቀረጹት የጥናት ሰነዶች በተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና በተለያዩ ዓለም አቀፍ መዋቅሮች መድረክ ለትርኢት ቀርቦ ሕፃናት ከዚህ አስከፊው ጸረ ሰብአዊ ተግባር ለማዳን የሚደረገው ርብርቦሽ እንዲያይል ጥሪ መተላለፉ የቫቲካ ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ዳቪደ ማጆረ ዕለቱን ምክንያት በማድረግ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
ገና ገዛ እራሳቸውን ለመከላከል ደረጃ ያልበቁት የኅብረተሰብ ክፍል አባላት በተለያየ ወቅትና በተደጋጋሚ በተለያዩ ወቅታዊ ግጭቶችና ውጊያዎች የጭካኔና የኢሰብአዊ ድርጊቶች መሣሪያ እንዲሆኑ ተገደው ብቻ ሳይሆን ይባስ በዚህ የጭካኔ ተግባር ጽንሰ ሃሳብ አእምሮአቸውን በማጠብ ቅትለት ጭካኔ ጸረ ሰብአዊ ተግባር የተገባ የሚያስመስል ለሚሰጣቸው ጸረ ሰብአዊ ጽንሰ ሃሳብ ተገዥ እንዲሆኑ በማድረግ፣ ለጸያፍ ተግባርና ለወሲብ ዓመጽ መሣሪያ እየሆኑ፣ የሚደርስባቸው ጸረ ሰብአዊ ግብረ ገባዊ ሥነ ልቦናዊ ጫና በእውነቱ እጅግ አሳሳቢ መሆኑ በኢራቅ በሶሪያ በደቡብ ሱዳን በአፍጋኒስታንና በማሊ ያለው ሁኔታ በመጥቀስ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ማጆረ ባጠናቀሩት ዘገባ በማብራራት፣ ሕፃናት የጦር መሣሪያ አንግበው እንዲገድሉ ተገደው የሌላው ሰው ሕይወት መቅጨት እንደ ተራ ተግባር እንዲመለከቱትና በዚህ አመለካከት ተመርተው እንዲያድጉ እየተገደዱ እሴት አልቦ ሕይወት ተመርተው እንዲያድርጉ ተደርገው መጻኢው ሕይወታቸው ተነጥቆባቸው በከፋ ሁኔታ ላይ የሚገኙ መሆናቸው ገልጠዋል።
ሕፃናት ሰብአዊ መብትና ክብር ተነፍጎአቸው ከሚኖሩበት ሁነትና ግጭቶችና ጦርነቶች አብቆቶለት አሊያም በተለያዩ የመንግሥታትና የሰውብአዊ ማኅበራት አማካኝነት ከዚህ ጸያፍ ተግባር ነጻ ከወጡ በኋላ ተከትሎአቸው የሚኖር ያለፈው ጸያፍ ተመክሮ በሚያሳድርባቸው ሥነ ልቦናዊ ግብረ ገባዊ ጫና ከማኅበርዊና ከሰብአዊ ችግሮች ሁሉ ለማላቀቅ የሚደረገው ጥረት ከባድና ትዕግስት ብዙ ወጪ የሚጠይቅ መሆኑ የዚህ ጉዳይ ምስክር በኡጋንዳ የሊራ ሰበካ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጁዘፐ ፍራንዘሊ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.