2015-02-06 15:42:33

የሁሉም አቢያተ ትምህርት ዓለም አቀፋዊ ድራዊ ማኅበር አራተኛ ጉባኤ


RealAudioMP3 ዓለም አቀፍ የመላ አቢያተ ትምህርት ተማሪዎች ድራዊ ግኑኝነት ማኅበር እ.ኤ.አ. ከ የካቲት 2 ቀን እስከ የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን በሲኖዶስ አዳራሽ ያካሄደው ይፋዊ አራተኛው ዓለም አቀፍ ዓውደ ጉባኤ በጳውሎስ ስድስተስኛ የጉባኤ አዳራሽ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ ለተጋባእያኑ ባስደመጡት ሥልጣንዊ ምዕዳን አማክኝነት መጠቃለሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ፓውሎ ኦንዳርዛ አስታወቁ።
ይኽ ዓለም አቀፍ የመላ አቢያተ ትምህርት ተማሪዎች ድራዊ ግኑኝነት ማኅበር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአርጀንቲና የቦነስ አይረስ ሊቀ ጳጳሳት እያሉ ሁሉም አቢያተ ትምህርት አለ ሃይማኖትና አገር ልዩነት የሚያቅፍ የመላ ዓለም ተማሪዎች እንዲገናኙ በማድረግ እሴቶች ለመዝራትና የሰው ልጅ ትምህርት የማግኘት ሰብአዊ መብቱና ክብሩ እንዲከበር ለማነቃቃት ብሎም ተማሪዎች የሕይወት ተመክሯቸውና በተለያዩ አገሮች የተደረሰው እደ ጥበባዊ ምንጣቄና መልካም ባህሎች ለማገናኘትና ለማስፋፋት የሚል በሰው ልጅ በኑባሬ ያለው ሰላም ፈላጊነት ባህርዩ እንዲረጋገጥ ማድረግ የሚል ዓላማ ያነገበ መሆኑ የዚህ ዓለም አቀፍ የመላ አቢያተ ትምህርት ተማሪዎች ድራዊ ግኑኝነት ማኅበር ዋና አስተዳዳሪ ኾሰ ማሪያ ደል ኮራል ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ ቅዱስ አባታችን ከሩቅ አመታት ገና ካህን ከዛም ሊቀ ጳጳሳት እያሉ የግኑኝነት ባህል ላይ ያተኵረ እርሱም የባህሎች ግኑኝነት ተጨባጭ ለማድረግ ትምህርት ቤቶች ማገናኘት ወሳኝ መሆኑ በማስተማር የግኑኝነት ባህል እንዲስፋፋ ያነቃቁት ዓለም አቀፍ የመላ አቢያተ ትምህርት ተማሪዎች ድራዊ ግኑኝነት ማኅበር በአሁኑ ወቅት በጠቅላላ ከአምስት ክፍለ ዓለማት የተወጣጡ አራት ሺሕ ትምህርት ቤቶች የሚያቅፍ ሲሆን፣ በአባላት ትምህርት ቤቶችና ተማሪዎች ብዛትም እጅግ ከፍ እያለ መምጣቱንም እንዳመለከቱም የሚታወስ ሲሆን፣ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በበኩላቸውም፦ ይኽ ቅዱስ አባታችን ያቋቋሙት ዓለም አቀፍ የመላ አቢያተ ትምህርት ተማሪዎች ድራዊ ግኑኝነት ማኅበር በዓለማችን ዙሪያ ለያይ አጥሪ ጨርሶ እንዳይኖር የሚያነቃቃ የግኑኝነት ባህል የሚያስፋፋ መሆኑ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አብራራተዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.