2015-02-06 15:40:08

ብፁዕ አቡነ ሮሶላቶስ፦ ለድኾች ቅርብ የሆንች ድኻይቱ ቤተ ክርስቲያን በግሪክ


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በግሪክ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳት በአገረ ቫቲካን ተቀብለው ማነጋገራቸው ሲገለጥ፣ በዚህ በተካሄደው ግኑኝነትም ቅዱስነታቸው ብፁዓን ጳጳሳቱና በግሪክ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ተስፋ የተሞላች በመጻኢ እማኔ በማኖር የጨለምተኝነትን ባህል ትቃወም” በሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ ያነጣጠረ ምዕዳን መለገሳቸው ሲገለጥ። በተካሄደው ግኑኝነት የተሳተፉት የአተኔ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሰቫቲኣኖስ ሮሶላቶስ ስለ ተካሄደው ግኑኝነትና እንዲሁም በግሪክ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የተደቀኑባት ተጋርጦዎች ውስጥ የምእመናን መበታተን የጥሪ ማነስና ስደት ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩም አጋጥሞ ያለው የኤኮኖሚ ቀውስ ብራሰልስ ግሪክ ልትከተለው ይገባል በማለት የወጠነው ድሎት የለሽ ጥብቅ የኤኮኖሚ ሥልት የአገሪቱ ዜጎች ወደ ድኽነትና ወደ መሠረታውያን አስፈላጊ ነገሮች እጦት እየዳረገ ያለው ሁነት ርእስ ሥር ከቫቲካን የቴሌቪዥን ማእከል ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ የገንዘብ ሃብት የነበራቸው አሁንም ያለውን የኤኮኖሚ ችግር እየተቋቋሙት ነው ሆኖም ግን ሠራተኞች በወር ደሞዝ የሚተዳደሩ ዜጎች በተከሰተው የኤኮኖሚ ችግርና ብራሰልስ የወጠነው የኤኮኖሚ መርሃ ግብር ለሥራ እጦት ተዳርገው በሥራ አጥነት ብቻ ሳይሆን በተመጣጠነ የሕይወት ደረጃ ከመተዳዳር ወደ ድኽነት እንዲያዘግም በማድረጉ ምክንያት በግሪክ በአሁኑ ሰዓት አንድም ሠራተኛ አባል የሌላቸው ቤተሰቦች ብዛት እጅግ ከፍ እንዲል ማድረጉንም ገልጠው፣ በንግድ ኤኮኖሚ ይተዳደሩ የነበሩት የአነስተኛ ድርጅቶች ባለ ሃብቶች የንድግድ ድርጅታቸውን እንዲዘጉ በማስገደዱም ምክንያት ሠራተኞቻቸውን ለማሰናበት ተገደው ባጠቃላይ አምራች ኤኮኖሚው እጅግ ተጎድቶ ድኽነት እየተስፋፋ ነው። በሕዝቡ አብራክ ዘንድ የምትገኘው ድኻይቱ ቤተ ክርስቲያን ባለው ሁኔታ እጅግ መጠቃቷ ገልጠው አሁንም ከሕዝቡ ጋር ለሕዝብ በተለያየ መስክ እያገለገለች ነው ብለዋል።
በካሪታስ ለሚጠራው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማኅበር ቅርንጫፍ በግሪክ በሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት በሕክምና ረገድ አቢይ አገልግሎት እየሰጠች ነው፣ የእናቴ ብፅዕት ተረዛ ደናግል ማኅበር አባላት በድኽነት የተጠቁት የጎዳና ተዳዳሪዎች የአደንዛዥ እጸዋት ጥገኞች ለብቻቸው የተተዉት ሴት ልጆች ዘርፈ ብዙ አገልግሎት በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፣ የቤት ኪራይ ለመክፈት የመብራት የውሃ አገልግሎት መስጫ ዋጋ መክፈል የሚሳነው የአገሪቱ ሕዝብ ብዛት እጅግ ከቀን ወደ ቀን እያደገ ነው። ስለዚህ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እንደ ሚያስተምሩትም ተክስቶ ካለው የኤኮኖሚ ቀውስ ለመላቀቅ የኤኮኖሚው ሥልት አለማዊነት ትሥሥር ሰው ማእከል የሚያደርግ መሆን አለበት በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.