2015-02-04 16:41:16

ቤተ ክርስቲያን በጸረ ሰብአዊ ንግድ ትግል


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. የካቲት 8 ቀን በላቲን ሥርዓት የሚከበረው የቅድስት በኪታ ዓመታዊ በዓል ምክንያት የጸረ ሰብአዊ ንግድ የጸሎትና የአስተንትኖ ቀን ጋር ተያይዞ በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን እንዲከበር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የሰጡት ውሳኔ በሁሉም ሰበካዎችና ቁምስናዎች በተለያዩ የውፉያንና የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት ማኅበራት በተለያዩ የካቲሊካዊት ቤተ ክርስቲያን እንቅስቃሴዎች እግብር ላይ እንደሚውል የውፉያንና የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት ማኅበራ ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ብራዝ ደ አቪዝ በቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ሕንፃ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ የየስደተኞችና ተጓዦች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል አንቶኒዮ ማሪያ ቨሊዮ፣ የፍትህና ሰላም ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ፐተር ቱርክሶ ተሸኝተው እንዲሁም በዚህ ጸረ ሰብአዊ ተግባር ዓላማ ተጠምዶ አቢይ አገልግሎት የሚሰጠው ታሊታ ኩም የተሰየመው የደናግል ማኅበር አባላትና የተለያዩ ያንን በጸረ ሰብአዊ የተጠቁትን ዜጎች በመደገፍና በሰብአዊና መፍነሳዊ ተልእኮ ተሰማርተው አገልግሎት የሚሰጡ ማኅበራትና እንቅስቃሴዎችን የሚወክሉ በተገኙበት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ማሳወቃቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፍራንቸስካ ሳባቲነሊ ገለጡ።
በሰው ልጅ ላይ የሚፈጸመው እርሱም የአዲስ ባርነት ተግባር፣ ሰው ልጅ በመሸጥና በመለወጥ ለክብር ሰራዥ አደጋ የማጋለጡ ተግባር በዓለማችን እየተስፋፋ ያለው አሰቃዊው ጸረ ሰብአዊ ድርጊት ለመግታትና ጨርሶ ለማጥፋት የሚደረገው ጥረትና የሚሰጠው አገልግሎት ቅዱስት ቤተ ክርስቲያን በተለያየ ወቅትና መድረክ ቀዳሚ ሥፍራ የምትገኝና ይኽ አገልግሎት በጸሎትና በአስተንትኖ ብሎም በተለያዩ አውደ ጉባኤዎችና ጥናቶች አማካኝነት መላ ቤተ ክርስቲያን በማወሃድ አገልግሎቱ ከፍ በማድረግ፣ ሰው ልጅ ለማዳን የሚደረገው ማንኛውም ዓይነት ጥረት በጸሎት እንዲሸኝ መላ የኵላዊት ቤተ ክርስትያን ምእመናን በዚህ አንደኛው የጸረ ሰብአዊ ንግድ የጸሎትና የአስተንትኖ መንፍሳዊ መርሃ ግብር እንዲሳተፍ ብፁዕ ካርዲናል ብራዝ ደ አቪዝ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱ ሳባቲነሊ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.