2015-02-02 16:02:17

ኣባ ስፕሪያኖ፦ ወህኒ ቤቶች በብቸኝነት የሚኖሩ ሰዎች ስብስብ


RealAudioMP3 በዚህ እ.ኤ.አ. በተገባው የካቲት ወር በመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ስለ እስረኞች የሚጸለይበት ወር መሆኑ ሲገለጥ፣ በተለይ ደግሞ ወጣት እስረኞች መጻኢ ሕይወታቸው ለመገንባት የሚያግዛቸው ክብረኛው ድጋፍና ሕንጸት የሚያገኙበት እንዲሆን የሚል የጸሎት ሃሳብ ማእከል በማድረግ ስለ እሰረኞችና ቤተሰቦቻቸው በማሰብ ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ስለ እነርሱ በመጸለይ ሁሉም በወህኒ ቤቶች ለሚገኙት ዜጎች ትብብር ድጋፍና ቅርበት እንዲኖር በተለይ ደግሞ ምእመናን ለዚህ ለተቀደሰ ዓላማ የምታነቃቃበት ወቅት ሲሆን፣ ይኸንን የጸሎት ሃሳብ በማስደገፍ ሮማ በሚገኘው ረቢቢያ ወህኒ ቤት ቆሞስና አበ ነፍስ አባ ሳንድሮ ስፕሪያኖ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ በወህኒ ቤት የሚገኙት ወጣት ዜጎች በእስር የሚቆዩበት ወሮችና ዓመታት የባከነ ጊዜ እንዳይሆንና መጻኢያቸው የተሻሻለና በተለይ ደግሞ ታርመውና ገዛ እራሳቸውን በመቻል ብቃት ታንጸው ከኅብረተሰብ ጋር ተቀላቅለው በሰላም ለመኖር የሚደረገው ጥረት ብዙ ይቀረዋል። በወህኒ ቤቶች ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በተለያዩ ቆሞሶችዋ መንፈሳዊ ማኅበራትና የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የበጎ አድራጎት አባላት አማካኝነት ቅርብ በመሆኑ በዚህ ዘርፍ አቢይ አስተዋጽዖ እየሰጠች መሆንዋ ገልጠው፣ ወህኒ ቤት በእስረኞች የተጨናነቁ ሆነው እያሉ ነገር ግን እያንዳንዱ እስረኛ ለገዛ እራሱ ደሴት በመሆን በእውነቱ ማኅበራዊ ብቸኝነት የሚኖርባቸው ክፍለ ከተማ ሆነው ይገኛሉ።ከኅብረተሰብ ተነጥሎ ብቻ ሳይሆን በሚገኙበት ወህኒ ቤት ጭምር እርስ በእርስ መገናኘትን አግለው በከፋ ብቸኝነት ሲኖሩ ይታያል። ቀርቦ ከእነርሱ ጋር መወያየት ልብንና ጆሮን ሰጥቶ በማዳመጥ ቀርቦ መደገፍ ያስፈልጋል። ካልሆነ የተበየነባቸው ዓመታት አስቆጥረው ከወጡ በኋላ ምንም ዓይነት ለውጥ ሳያሳዩ ቢገኙም የመላ ኅብረተሰብ ውድቀት ይሆናል ብለዋል።
ወህኒ ቤት የብቀላ ሥፍራ ሳይሆን የሕንጸት ቤት መሆን አለበት፣ የተሳሳተ እንዲጸጸት የሚያታገዝበት ሥፍራ መሆን ይጠበቅበታል፣ በወህኒ ቤተ የሚያገለግሉ ካህናት ተቀዳሚ ሐዋርያዊ ተልእኮአቸው ተስፋን መዝራት ነው። ስለ እስረኞች መጸለይና ስለ እነርሱ ማሰብ በእውነቱ ብቻቸው እንዳልሆኑ የሚመሰክር መንፈሳዊ ሰብአዊ ተግባር ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.