2015-01-21 14:48:34

ብፁዕ ካርዲናል ፊሎኒ፦ ህያው ቤተ ክርስቲያን በቪየትናም


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ጥር 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ባጠናቀቁት ዓለም ዓቀፋዊ ሐዋርያዊ ዑደት የሸኙዋቸው የአስፍሆተ ወንጌል ለአሕዛብ ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ፈርናንዶ ፊሎኒ የቪየትናም ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ባቀረቡላቸው ጥሪ መሠረት በቪየትናም በሚከበረው ዝክረ 400ኛው ዓመት ክርስትና ለመሳተፍ እ.ኤ.አ. ከጥር 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ቪየትናም እንደሚገኙ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ እ.ኤ.አ. ጥር 20 ቀን 2015 ዓ.ም. በሃኖይ ከቪየትናም ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤትና ቀጥለውም ከአገሪቱ ውሉደ ክህነት አባላት ጋር መገናኘታቸው ያመለክታል።
በቪየትናም ለቤተ ክርስቲያንና ለአገር እድገት የዓለማውያን ምእመናን አስተዋፅዖ ወሳኝ መሆኑ ሲገለጥ ከጠቅላላ የአገሪቱ የካቶሊክ እምነት የሚከተል ሕዝብ ብዛት ውስጥ ከ 80 እስከ 93% የሚሸፍን ነው። በዕለት ሰንበት ብቻ ሳይሆን በተራ ቀን እምነቱ የሚኖር መሆኑ ሲገለጥ፣ ዓለማውያን ምእመናን በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ያለው ሱታፌ እጅግ ከፍ ያለና ለቃለ እግዚአብሔርና እንዲሁም የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ ትምህርት በሕይወቱ አቢይ ሥፍራ የሚሰጥ ለአገርና ለቤተ ክርስቲያን እድገት ዋና ተወናያን መሆኑ ሲገለጥ፣ ብፁዕ ካርዲናል ፊሎኒ ባካሄዱት ግኑኝነት ይኸንን ሃሳብ እንዳሰመሩበት የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ ብፁዕነታቸው ወንጌላዊ ኃሴት ለአስፍሆተ ወንጌል ኃይል መሆኑ ባስደመጡት ንግግር አበክረው፣ የአገሪቱ በፁዓን ጳጳሳት ወንጌላዊ ኃሴት የተሰየመው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሐዋርያዊ ምዕዳን በበለጠ ትኵረት ሰጥተውበት የቤተ ክርስቲያን መርሃ ግብርና ራእይ ምን መሆን እንዳለበት የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ቅዱስ አባታችን ያኖሩት ሃሳብ መከተል አስፈላጊ ነው። ይኽ ደግሞ የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን መርሃ ግብር ነው። ወንጌላዊ ኃሴት ለአስፍሆተ ወንጌል መሠረት ነው። ወንጌላዊ ኃሴት የሚመነጨው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የሚደረገው ሕይወትንና ወንጌላዊ ተልእኮ የሚለውጥና የሚያድስ ግኑኝነት መሆኑ ቅዱስ አባታችን ገልጠዉታል፣ ስለዚህ ወንጌላዊ ኃሴት ከኢየሱስ ጋር ከመገናኘት የሚመነጭ ለአስፍሆተ ወንጌል መሠረት ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።
የዛሬ 400 ዓመት በፊት ክርስትናን ወደ ቪየትናም ያስገቡት ያንን 50ኛው ዓመቱን ያካበረው ወደ አሕዛብ የተሰየመው የሁለተኛው ቫቲካን ጉባኤ ውሳኔ ያስታውሰናል፣ እነርሱ የዛሬ 400 ዓመት በፊት የኖሩት እውነትም ነው። የመጀመሪያው የክርስትናው እምነት ዘር ወደ ቪየትናም ያስገቡት የኢየሱሳውያን ማኅበር አባላት መሆናቸውም አስታውሰው፣ እ.ኤ.አ. በ 2010 ዓ.ም. በቪየትናም የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በቪየትናም በሐዋርያዊ መስተናብርነት የቆሙት የመጀመሪያዎች ሁለት ሰበካዎች 350ኛው ዓመት መሥረታዎችና እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ሥልጣን ቅዋሜው 50ኛው ዓመት መከበሩ አስታውሰው፣ የአገሪቱ ካህናትና የምድር ጨውና ብርሃን እንዲሆኑ መጠራታቸው አሳስበው ክህነት ጥሪ አገልግሎትና ክርስቶስን መምሰልን የሚጠይቅ ገዛ እራስ ለእግዚአብሔር ማቅረብ እንጂ ሥልጣን ማለት አይደለም ብለው መላ ሕይወት ለመላ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት አነሆኝ የሚባልበት ሕይወትን ስለ ፍቅር የሰዋው የጌታችን ኢየሱስ ፍቅር የሚወልደው የፍቅር ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መርኖ ያስፈልጋል፣ ስለዚህ ድኾች የተናቁት የተነጠሉት ማእከል የሚያደርግ ቅድሚይ የሚሰጥ የከተሞቻችንና የሕልውናችን ጥጋ ጥግ ክልሎችን የሚያስቀድም ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎና ሐዋርያዊ አገልግሎት የሚል ማለት ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያመልክታል።
የቪየትናም ክርስትና 400ኛው ዓመት ማስቆጠሩና በአሁኑ ወቅት በቪየትና የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤት ክርስቲያን እጅግ በደማቅ ሁኔታ እያከበረችው ያለ ዓቢይ በዓል ሲሆን፣ የዛሬ አራት መቶ ዓመት በፊት ቀደምት ሰባክያንና ወደ ቪየትናም ክርስትና ያስገበቡት የኢየሱሳውያን ልኡካነ ወንጌል ማኅበር አባላት መሆናቸው ሚስና የዜና አገልግሎት ጠቅሶ ብፁዕ አቡነ ሶስማ ሆአንግ ቫ ዳት የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል በቱ ዱክ በሚገኘው የኢየሱሳውያን ቤት 210 የማኅበር አባላት 3 ሺሕ ምእመናን የተሳተፉበት መሥዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው አስታወቀ። ክርስትና በተቀበሉት በአንዳንድ የጃፓን ዜጎች ተሸውኘው ክርስትና ለመጀመሪያ ጊዜ የዛሬ አራት መቶ ዓመት በፊት ወደ ቪየትናም ያስገቡት ሁለት የኢጣሊያ ዜጎችና ሁለት የፖርቱጋል ተወላጆች የኢየሱሳውያን ማኅበር አባላት መሆናቸው ያስታወሰው ሚስና የዜና አገልግሎት፣ ቪየትናም የገቡት የኢየሱሳውያን ማኅበር በቪየትናም ከ 158 ዓመት በኋላ በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ተገደው እቋርጠው ከተመለሱ በኋላ እ.ኤ.አ. በ 1975 ዓ.ም. ዳግም ተመልሰው የቪየትናም ጦርነት አብቅቶለት በአገሪቱ በቆመው የኮሙኒስት መንግሥት እዛው የነበሩት 41 ኢየሱሳውያን የውጭ አገር ዜጎችን ሲያባርር የተቀሩት 26 ቬትናማውያን የኢየሱሳውያን ማኅበር አባላት እንዲቀሩ ፈቅዶ ግማሾቹ ለእስር የተቀሩትንም ደግሞ በጉልበት ሥራ እንዲሰማሩ ማድረጉ ያስታወሰው ሚስና የዜና አገልግሎት በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ 140 የኢየሱሳውያን ማኅበር የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ያካተተ በጠቅላላ 210 የኢየሱሳውያን ማኅበር አባላት እንዳሉ ይጠቁማል።







All the contents on this site are copyrighted ©.