2015-01-16 15:43:19

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ኢየሱስን መምሰል


RealAudioMP3 “ትወደኛለህን?...በጐቼን ጠብቅ (አሰማራ)” (ዮሓ. 21.15.16) የዕለቱ ወንጌል ኢየሱስ ለጴጥሮስ የተናገረውን ቃል ዛሬ ለእናንተ ለተወደዳችሁ ብፁዓን ጳጳሳትና ካህናት ገዳማውያን የዘርአ ክህነት ተማሪዎች የማቀርበው ይሆናል። ኢየሱስ የተናገረው ቃል መሠረታዊ የሆነውን ነገር ያስታውሰናል፣ ማንኛውም የግብረ ሐዋርያት አገልግሎት ጥሪ ከፍቅር የሚወለድ ነው። እያንዳንዱ ውፉይ ከአስታራቂው የኢየሱስ ፍቅር የሚወለድ ነው፣ እንደ ቅድስት ተረዛ ዘሕጻነ ኢየሱስ፣ በቤተ ክርስቲያን የፍቅር ምልክት እንሆን ዘንድ በተለያዩ ጥሪያዎች አማካኝነት ተጠርተዋል።
ፍቅር በተካነው መንፈስ ለሁላችሁ ሰላምታየን አቀርባለሁኝ ለሁሉም ለወንድሞቻችሁ ለእህቶቻችሁ ለአረጋውያን ለህሙማን በዚህ ሰዓት በተለያየ ምክንያት እዚህ ለመገኘት ላልቻሉት ሁሉ ፍቅር የተሞላው ሰላምታዮን ታደርሱ ዘንድ አደራ….በዚህች አገር ወንጌልን ለማበሰር መላ ኃይላቸውን የሰዉ ቤተ ክርስቲያንን በማነጽ ያለፉት ብፁዓን ጳጳሳት ካህናት ደግነት፣ በዚህ ተልእኮ ብቻ ሳይታጠሩ ወንጌላዊ ፍቅር ምህረት ለጋራ ጥቅም ያቀና ትብብር በሚለው የተነቃቃ እንዲሆን ይኸ መንፈስ በሕብረተሰብ ውስጥ እንዲታተም አድርገዋል። እንዳለፉት ሁሉ እናንተም አገናኝ ድልድይ እንድትገነቡና የክርስቶስ መንጋ እንድታሰማሩ በእስያ ለአዲስ ብሩህ ዘመን ብቃት ያለው ወንጌላዊ መንገድ ታቀኑ ዘንድ የተጠራችሁ ናችሁ።
“የክርስቶስ ፍቅር የራሱ አድርጎናል” (2ቆር. 5 14) በአንደኛው ምንባብ ቅዱስ ጳውሎስ ያ የጠራን የስቁል መድኅን የሆነው አስታራቂው ፍቅር በልብና ከልብ ለመስበክ የተጠራን መሆናችን ይገልጥልናል። ልኡካነ ክርስቶስ ለመሆን የተጠራን ነን (2ቆሮ. 5, 20)፣ ተልእኳችን የእርቅ ነው፣ ያንን የምህረትና ምሉእ የእግዚአብሔር ፍቅር የሆነውን የፍቅር አዲስ ብሥራት ለማወጅ ነው። ወንጌል የእግዚአብሔር ጸጋና ቃል ኪዳን በመሆኑም ለታመመው ዓለማችን ምልአትና መዳንን የሚሰጥ እርሱ ብቻ ነው። ወንጌል ለአንድ ቅንና የዳነ ኅብረተሰብ ሥርዓት ለመገንባት የሚያነቃቃ ይሆናል።
የክርስቶስ ልኡካን መሆን ማለት እያንዳንዱ ሰው ከጌታ ኢየሱስ ጋር የታደሰ ግኑኝነት እንዲኖረው የሚጋብዝ ነው (ወንጌላዊ ኃሴት ቍ. 3 ተመልከት) ። ከእርሱ ጋር ያለን የግል ግኑኝነት። ይኽ ግብዣ በፊሊፒንስ ወንጌል የገባበት 500ኛው ዓመት ምክንያት ለምንፈጽመው ዝክረ በዓል ማእከል መሆን አለበት። ወንጌል በግልም በጋራም ደረጃ የለውጥና የህሊና መርመራ የማድረግ ጥሪም ነው። የፊሊፒንስ ብፁዓን ጳጳሳት እንደሚያስተምሩንም በአገሪቱ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ያንን ሥር የሰደደው የፊሊፒንስ ኅብረተሰብ ገጽ የሚበክለው ከክርስቶስ ትምህርት ጋር የሚጻረረው የኢፍትኃዊነትና የእኩልነት አልቦ መነሾ የሆነውን ለመለየትና ለመዋጋት የተጠራች ነች። ወንጌል እያንዳንዱ ክርስቲያን ቅነኛ ሙሉ ለጋራ ጥቅም እጅግ የሚተጋ ሕይወት እንዲኖር ይጠራል፣ ማኅበረ ክርስቲያንም የሚኖርበት ኅብረሰተስብ በሚሰጠው የቃልና የሕይወት ምስክርነት አማካኝነት የለውጥና የድጋፍ ቅነኞች ማኅበራት እርሱም የትብብር የመደጋገፍ የግኑኝነት መሥገርት ይፈጥር ዘንድ ይጠራል።
“ድኾች። ድኾች የወንጌል ማእከል ናቸው፣ የወንጌል ልብ ናቸው፣ ድኾችን ከወንጌል ያገለልን እንደሆን የኢየሱስ ክርስቶስ መልእክት በተአመር ለመረዳት አይቻለንም” እንደ ልኡካነ ክርስቶስ እኛ ብፁዓን ጳጳሳት ካህናት ገዳማውያን በቅድሚያ ያንን የእርሱ የዕርቅ ጸጋ በልባችን መቀበል ማሳደር ይጠበቅብናል፣ ይኽ ደግሞ ምን ማለት መሆኑ ቅዱስ ጳውሎስ የዓለማዊነት አስተያየት መካድ ሁሉ ነገር በክርስቶስ ብርሃን መመልከት ማለት መሆኑ ገልጦልናል። ስለዚህ በቅድሚያ ኅሊናችን ልንመረምር ይገባናል፣ ውድቀታችን ድካማነታችን ስህተታችንን ለይተንና አውቀን ዳግም በቀጣይ ኅዳሴና ለውጥ አማካኝነት በዕለታዊ መለወጥ መገኘት እንዳለብን ነው የሚገልጠው። ትዕቢተኛነታችን ለለውጥ ያለን ፍርሃት ለዚህ ዓለም አስተሳስብ ሰጥባይነት የምንከተለው የዓለማዊነት መንፈስ ለሚያናጋው የእግዚአብሔር ቃል ገዛ እራሳችንን ካልሰጠን እንዴት ብለን ነው ለሌሎች ነጻ አውጪው የመስቀል ኃይል ልናበሥር የምንችለው? (ወንጌላዊ ኃሴት ቍ. 93 ተመልከት)።
ለእኛ ካህናትና ውፉያን ሰዎች በወንጌላዊ ኅዳሴ ለመለወጥ ዕለት በዕለት በጸሎት ከጌታ ጋር መገናኘትን ይጠበቅብናል። ቅዱሳኖች የሐዋርያዊ ቀናተኛነት ምንጭ በጸሎት ከጌታ ጋር መገናኘት መሆኑ ያስተምሩናል፣ ለገዳማውያን ወንጌላዊ ኅዳሴ መኖር ማለት በፍጹም ፍቅር አማካኘንት ከጌታ ጋር ሱታፌ እንዲኖር በሚያበቃ አዲስ ሕይወትና በማህበራዊ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መገኘት ማለት ነው። የዚያ የመላ ሕይወቱ ትርጉም የእግዚአብሔር ፈቃድ መኖርና መፈጸምና ሌሎችን ማገልገል የሚለው የክርስቶስ ድኽነት እንዲስተነተን የሚያበቃ ሕይወት መኖር ማለት ነው። ሆኖም ለዚህ ዓይነቱ ሕይወት ሥጋት ያንን የምናቀርበው ብሥራት ለገበያዊነት ግልግልና ለዚህ ዓይነት መንፈስ ሰጥለበጥ እንዲልና ወደ ዓለማዊ ግኡዝነት ማዘንበል የሚለው ፈተና ነው። ድኾች በመሆን ብቻ ነው ከራስ ወዳድነት ለእራስ ጥቅም ከማድላት ተገሎ የመጨረሻ ከሆኑት ከተናቁት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን መስሎ መኖር የሚቻለው። እንዲህ ሲኮንም ሁሉን ነገር በአዲስ መንፈስ መመልከት እንጀምራለን፣ በዚህ መንገድ አማካኝነትም ሌላውን ነጥሎ መኖር መቦደን እኩልነት አልቦ መኖር በተላመደው ዓለም በቅንነትና በሙላት ሥር ነቀላዊ ወንጌል በማበሠር ለሚያጋጥም ተጋርጦ ሁሉ ምላሽ ለመስጠት የሚቻላቸው እንሆናለን።
በድኽነት በምግባረ ብልሽት ተስፋ ቆርጦ ሁሉን ነገር የትምህርት ገበታ ጭምር ሳይቀር ትቶ እጁን ሰጥቶ ለሚኖረው ሕዝብ ቅርብ ሁኑ፣ በዚያ ስለ ጾታዊ ስሜት በሚሰጠው ዓለማዊ ትምህርት በተደናገረው ኅብረተሰብ ዘንድ ክርስቲያናዊ ቃል ኪዳን ያለው ውበትና እውነት መስክሩ…የፊሊፒንስ ባህል ከእምነት በሚነቃቃ የፈጠራ ብቃት የተቀረጸ ነው፣ በሁሉም ሥፍራና ቦታ ፊሊፒናውያን ለእግዚአብሔር ባላቸው ፍቅር የሚታወቁ ናቸው…ለእግዚአብሔር ባላቸው ፍቅር ያላቸው ሕዝባዊ መንፈሳዊነት የሞቀውና ልባዊ ለማርያምና መቍጸሪያ ባላችሁ ፍቅር የምትታወቁ ናችሁ። የፊሊፒንስ ሕዝብ ባህሉን በወንጌል ሰብከዋል፣ አሁንም ወንጌላዊ ቃል በቀጣይነትና በታደሰ መንፈስ እያስተናገደ ነው። የፊሊፒንስ አስፍሆተ ወንጌል 500ኛው ዓመት ዝክረ በዓል በዚህ መሠረት ላይ የጸና አድርጉ።
ኢየሱስ “ስለ ሆሉ ሞተ። እንግዲያስ ሁሉ ሞቱ፣ በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው አንደማይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ” (2ቆር. 5.15) ውድ ወንድሞቼ ብፁዓን ጳጳሳት ካህናትና ገዳማውያን በእናንተ ውስጥ ጌታ ለእርሱ እነሆንኝ ብሎ ገዛ እራስ ለማቅረብና በእርሱ እጅ ገዛ እራሳችሁ በመተው ወንድሞችንና እህቶችን ገዛ እራስ ክዶ ለማገልግል የሚያበቃ ቀናተኛው ኃይል ይሰጣችሁ ዘንድ በቤተ ክርስቲያን እናት በሆነችው ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት እጸልያለሁ፣ በዚህ ዓይነት መንገድ የክርስቶስ አስታራቂው ፍቅር በእናንተ አማካኝነት በፊሊፒንስ ኅብረተሰብና ወደ ዓለም ዳርጃ ሁሉ ይሰርጻል። አሜን







All the contents on this site are copyrighted ©.