Home Archivio
2015-01-12 15:11:20
ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር፦ የምኅረት ጊዜ እየኖርን ነው
እ.ኤ.አ. ጥር 11 ቀን 2015 ዓ.ም. የላቲን ሥርዓት የምትከተል ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በዓለ ጥምቀት ዘእግዚእነ ባከበረችበት ሰንበት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እኩለ ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከተሰበሰቡት ከውጭና ከውስጥ የመጡት ምእመናን ጋር ሆነው ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር መርተው ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ
“የሰማያተ ሰማይ የመዘጋት ወቅት አብቅቶለታል”
በሚል ቀዉም ሃሳብ ላይ ያነጣጠረ አስተንትኖ መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሰርጆ ቸንቶፋንቲ አመለከቱ።
“ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በድኾች በታመምቱና በእስረኞች ዘንድ እንገናኘዋለን”
የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት ያ በሰው ልጅ ኃጢአት አማካኝነት በእግዚአብሔርና በሰው ዘር መካከል ተፈጥሮ የነበረው የመለያየት ምልክት የሆነው የሰማያተ ሰማይ መዘጋት እንዳገለለ ገልጠው፦
“ኃጢአት ከእግዚአብሔር እንድንርቅ ያደርገናል፣ በሰማይና በመሬት መካከል የነበረው ግኑኝነት ይገታል፣ ይኽ ሁኔታ ደግሞ የሕይወታችን ውድቀትና መከራን ወስነዋል፣ የሰምያተ ሰማይ መከፈት እግዚአብሔር ጸጋውን እንደሰጠን የሚያመለክት ነው፣ ስለዚህም እያንዳንዳችን ፍቅርንና ማለቂያ የሌለውን ምህረት ለማጣጣም ከእግዚአብሔር ልጅ ጋር ለመገናኘት አስችሎናል፣ በቅዱሳት ምስጢራት በተለይ ደግሞ በቅዱስ ቁርባን ከእርሱ ጋር ለመገናኘት እንችላለን፣ በወንድሞቻችን ሕይወት ለይተን እናውቀዋለን፣ በተለይ ደግሞ በእነዚያ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይ ተካፋዮችና እየዚያ የማይታየው እግዚአብሔር ተጨባጭ ኅላዌ የሆነው ጌታችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኅያው አካል በድኾች በታመሙት በታሰሩት በተፈናቀሉት በስደተኞች ዘንድ እንገናኘዋለን። ወቅቱ የእግዚአብሔር ምኅረት እጅግ የሚያስፈልግበት ጊዜ ነው፣ ስለዚህ ይኸንን የእግዚአብሔር ምኅረት መላ ቤተ ክርስቲያንና ዓለማውያን ምእመናን በመኖር ወደ ተለያየው የማኅበራዊ ገጽታ ለማድረስ ተጠርተዋል። ወደ ፊት እንበል አደራ የምኅረት ጊዜ ነው። የምኅረት ጊዜ እየኖርን ነው” እንዳሉ የገለጡት ልኡክ ጋዜጠኛ ቸንቶፋንቲ አክለው “መንፈስ ቅዱስ ወንጌል ወደ ሁሉ ዓለም ለማድረስ ያነቃቃል፣ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት ያ በጸሎታችን የምንዘነጋው ሆኖም የክርስትያን ኅልውና የሚመራው መንፈስ ቅዱስ ወርደዋል፣ ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና ተግባራችን በዚያ በምሥጢረ ጥምቀት አማካኝነት በተቀበልነው በመንፈስ ቅዱስ ሥራ ሥር እናኑር፣ ይኽ ደግሞ መልካም አታላይና ምቹ የሚመስለው በዓለማዊ መንፈስ ላለ መመራት ሐዋርያዊ ጽናት መልሶ ማግኘት ማለት ነው። አንድ ክርስቲያን አንድ ማኅበረ ክርስቲያን ለዚያ ወንጌል ወደ ሁሉ ዓለምና ህዝብ እንዲደርስ ለሚያደርገው ለመንፈስ ቅዱስ ድምጽ የተዘጋና የማይሰማ ጆር ያለው ሲሆን የማይናገርና ልሳኑ የተቆለፈ ኮልታፋ ክርስቲያንና ማኅበረ ክርስቲያን ይሆናል፣ የዚህ ዓይነቱ ማኅብረ ክርስቲያን አይናገርም ወንጌልንም እያደርስም አያስፋፉም”
ብለው እ.ኤ.አ. ጥር 12 ቀን 2015 ዓ.ም. ወደ ስሪ ላንካና ፊሊፒንስ የሚያካሄዱት ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ዑደት አስታውሰው ሁሉም በጸሎታቸው እንዲያስቡዋቸው አደራ ብለው ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር አሳርገው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው አስታውቀዋል።
ይኽ በእንዲህ እንዳለም ቅዱስ አባታችን በስሪ ላንካና ፊሊፒንስ የሚፈጽሙት ሐዋርያዊ ዑደት ለማርያም ለማማጠን እ.ኤ.አ. ጥር 11 ቀን 2015 ዓ.ም. ሮማ ወደ ሚገኘው ሳንታ ማርያ ማጆረ (ዓቢይ የቅድስት ማርያም) ጳጳሳዊ ባዚሊካ መፍነሳዊ ንገድ መፈጸማቸው ልኡክ ጋዜጠኛ ቸንቶፋንቲ ገለጡ።
All the contents on this site are copyrighted ©.