2014-11-26 17:48:13

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ፣


RealAudioMP3 ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ዛሬ ሮብ ረፋድ ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ምንም እንኳ ዝናምና ብርድ ቢኖርም በቦታው ለተገኙ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ም እመናንና ነጋድያን ስለ ቤተ ክርስትያን ማንነት የጀመሩትን ትምህርተ ክርስቶስ በመቀጠል የሚከተለውን አስተምህርቶ አቅርበዋል፣
ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ! ቀኑ ጥቂት የዳበነ ይመስላል ሆኖም ግን በብዛት እዚህ መገኘታችሁ ብርታታችሁን ስለሚያመለክት ሳመሰግን ዛሬ አብረን እንድንጸልይ ተስፋ አደርጋለውሁ፣
ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ስለቤተ ክርስትያን መረሳት የሌለበት አንድ መሠረታዊ እውነት ገለጠ፤ ይህም ቤተ ክርስትያን ቀዋሚ የማትንቀሳቀስና ለውጥ የማይካሄዳት ሳይሆን በታሪክ ውስጥ በተከታታይ እንድምትጓዝና የመጨረሻ ዓላማው የሆነውን መንግሥተ ሰማያት እስክትደርስ እንደጅማሬና እንደዘር እየታደሰችና እያደገች እንደምትገኝ ነው (ብርሃነ አሕዛብ 5 ተመልከት)፣ በዚሁ አድማስ መመልከት ስንጀምር ከህዋሳቶቻችን ባሻገር የሆነው አስደናቂውን ምሥጢር ሲገለጥልን አስተያየታችንና አቅማችን ሲቆም እናያለን፣ በኅልናችንም አንዳንድ ጥያቄዎች ይነሳሉ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ እውን ይሆናል? የመጨረሻ ዓላማው ወደሆነው መንግሥተሰማያት ላይ ስትደርስ ቤተ ክርስትያን እንዴት ትሆን ይሆናል? የሰውልጅ ፍጻሜስ ምን ይሆን? ተፈጥሮና አከባብያችንስ መጨረሻው እንዴት ይሆን? የሚሉ ጥያቄዎች ሊነሱ ይቻላል፤ ነገር ግን እነኚህ ጥያቄዎች የመጀመርያ አይደሉም ድሮ ሓዋርያት ከጌታ ጋር ኢየሱስ እያሉ “ይህ ሁሉ መቼ ይሆናል?መንፈስ ቅዱስ በተፈጥሮና በፍጥረት ላይ ሁሉ ድል የሚነሳው መቼ ይሆን” ብለው ጠይቀውት ነበር፣ ጥያቄዎቹ የሰው ልጅ ሁሉ ጥያቄ ሆነው ከጥንት የነበሩና አሁንም እኛ የምንጠይቃቸው ናቸው፣
ፍሥሓና ደስታ የሚለው የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ሰነድ ዘወትር በሰውልጅ ልጅ ውስጥ ለሚመላለሱ እነኚህን ጥያቄዎች በሚመለክት “መሬትና የሰው ልጅ መጨረሻን የሚመለከቱትን ጉዳዮች እንተዋቸው ዓለም መቼ እንደምትለወጥ አናውቅምና፣ በእርግጥ ይሄኛው በኃጢአት ደብዛው የጠፋው ዓለም እንደሚለወጥ እናውቃለን፣ እግዚአብሔር በገለጠለን ደግሞ እግዚአብሔ በፍትሕ የምንኖርበት አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እንደሚያዘጋጅ በዚህም በሰው ልጅ ውስጥ ያሉ ፍላጎቶችን ሁሉ የሚያሟላ ከሰላም ፍላቶች ሁሉ የላቀ ደስታ ሁሉንም እንደሚሞላ እናውቃለን” (ቍ 39) በማለት መልስ ይሰጣል፣ ቤተ ክርስትያን የምትጓዘውም ለዚህ ዓላማ ነው ቅዱስ መጽሓፍ እንደሚለውም “አዲስትዋ ኢየሩሳሌም” ወይንም “መንግሥተ ሰማያት” ይህ ነው፣ አንድ ቦታ ሳይሆን ሁኔታን ነፍሳችን የምትኖረው ሁኔታን ያመለከታል፤ ብውስጣችን ያሉ ጥልቅ ፍላጎቶች በተጣጠፈ መንገድ እውን ሊሆኑና እንደእግዚአብሔር ልጆች በሙላት የምንኖርበት ሁኔታ ነው፣ እንዲህ ባለሁኔታም በመጨረሻ የእግዚአብሔር ደስታ ሰላምና ፍቅርን በሙላት እንለብሰዋለን አለምንም ገደብም ከእግዚአብሔር ጋር ፊት ለፊት እንተያያለን (1ቆሮ 13፡12)፣ ይህንን ማሰብ ስለመንግሥተሰማይት ማሰብ ምኑን ያህል ደስ ያሰኛል፣ እኛ ሁላችን በዚህ እንገናኛለን፤ ይህ ደስ የሚያሰኝ አሳብ ለነፍሳችን ኃይል ይሰጣታል፣
በዚህ አመለካከት የዚህች በጉዞ ላይ የምትገኝ ምድራዊት ቤተ ክርስትያንና በሰማይ ላይ በምትገኘው ቤተ ክርስትያን መካከል ያለውን ጥልቅ ግኑኝነትና ቀጣይነት እንዳለ መገንዘብ እንዴት ደስ ያሰኛል፣ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተው በእግዚአብሔር እቅፍ ያሉ አባሎቻችን ሊደግፉንና ስለእኛ ሊያማልዱ ሊጸልዩ ይችላሉ፣ እኛም በበኩላችን ከእነዚሁ ነፍሳት ወደ መጨረሻ የሌለው ብፅዕና ለመግባት ገና በመጠባበቅ ያሉና በሥቃይ ስለሚገኙ እግዚአብሔር እንዲያቀልላቸው፤ መልካም ሥራ መሥራት መጸለይ መሥዋዕተ ቅዳሴ ማስቀደስ አለብን፣ ይህ የሚሆንበት ምክንያት ደግሞ በክርስትያኖች መካከል ያለው ልዩነት በሞተና ገና በሕይወት ባለ ሳይሆን ከጌታ ጋር አብሮ የሚጓዝና ከጌታ ኅብረት የሌለው ተብለው ስለሚከፈሉ ነው፣ ይህ ነጥብ ለደህንነታችንና ለደስታችን ወሳኝ ነው፣
በሌላ በኩል ደግሞ ቅዱስ መጽሓፍ የዚሁ አስደናቂ ዕቅድ ፍጻሜ እኛን ብቻ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ኃሳብና ልብ የወጣውና የተፈጠረው ከቦን ያለ ፍጥረት ሁሉን እንደሚያካትት ያስተምረናል፣ ሐዋርያ ጳውሎስ ይህንን ግልጽ በሆነ መንገድ ያረጋግጥልናል “ተስፋውም ፍጥረት ራሱ ደግሞ ከጥፋት ባርነት ነፃነት ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደሚሆን ክብር ነፃነት እንዲደርስ ነው። ጥረት ሁሉ እስከ አሁን ድረስ አብሮ በመቃተትና በምጥ መኖሩን እናውቃለንና።” (ሮሜ 8፡21-22) ይላል፣ ሌሎች ጽሑፎችም የአዲስ ሰማይና የአዲስ ምድር ምሳሌን ያቀርባሉ (2ጴጥ 3፡13 የዮሓ ራእ 21፡1) ይህ ማለትም ምድረሰማዩ ሁሉ ይታደሳል ለአንዴና ለመጨረሻ ከማንኛውም የክፋት ምልክት እንዲሁም ከሞትም ሳይቀር ነጻ ይወጣል፣ እኛ የምንጠባበቀውም ይህ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ የጀመረው ለውጥ በሁላችን እንዲደርስና አዲስ ፍጥረት እንድንሆን ነው፣ ስለዚህ የሁሉ ነገር መጥፋትና መውደም ሳይሆን እኛ የምንጠባበቀው የሁሉን ነገር መታደስ መለወጥና አዲስ ሙላት እውነትና መልክ መያዝን ነው፣ የቅድስት ሥላሴ የአብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ዕቅድም ከጥንት ጀምሮ ይህ ነው፣ ቀስ በቀስም እውን እየሆነ ነው፣
ውዶቼ! ስለእነዚሁ የሚጠባበቁን አስደናቂ ነገሮች ስናሰላስል የዚህ ተስፋና እቅድ ተሸላሚ የሆነች ቤተ ክርስትያን አባል መሆን ምንኛ ያህል ደስ እንደሚያሰኝ እንረዳለን፣ ስለዚህ የቤተ ክርስትያን እናት የሆነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በዚሁ ጉዞ አችን እንድትሸኘንና እንደ እርሷ ለወንድሞቻችን የመተማመንና የተስፋ ደስተኛ ምልክቶች እንድንሆን ትረዳን ዘንድ እንለምናት፣








All the contents on this site are copyrighted ©.