2014-11-21 16:20:45

የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የዓንቀጸ እምነት ማኅበራዊ ትምህርት በዓል


RealAudioMP3 የቶኒዮሎ ማኅበር በየዓመት የሚያዘጋጀው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን መሠረታዊ የዓነቀጸ እምነት ማኅበራዊ ትምህርት በዓውደ ጥናት የሚሸኘው በዓል በመቀጠል እ.ኤ.አ. ህዳር 19 ቀን 2014 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በማኅበራዊ ጉዳይ ላይ ያነጣጠረ ባስተላለፉት የድምጸ ምስል ሥልጣናዊ መልእክት አማካኝነት በይፋ መጀመሩ ሲገለጥ ቅዱስ አባታችን ወንጌላዊ ኃሴት በሚል ርእስ ሥር ከደረሱት ሐዋርያዊ ምዕዳን የተወሰደ ሃሳብ እርሱም “ጊዜ ከስፋት የላቀ ነው” በሚል ቃል የተመራ ሲሆን፣ ይኽ የኢጣሊያ የሥራና ሠራተኛ ጉዳይ ሚን. ጁሊያኖ ፖለቲ በማሳተፍ የሚካሄደው የዘንድሮው እራተኛው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የዓንቀጸ እምነት ማኅበራዊ ትምህርት በዓል በማስመልከትም የፍትህና ሰላም ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ማሪዮ ቶሶ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ከወንጌላዊ ኃሴት ሐዋርያዊ መልእክት የተወሰደው የዓውደ ጉባኤው ርእስ በእውነቱ ሕብረተሰብ በሰላም በፍትህና በወንድማማችነት መንፈስ ማነጽ ያለው አስፈላጊነት የሚያሳስብና ይኸንን ክብር መሠረት የሚገነባው ሕብረተሰብ በእውነቱ በአሁኑ ሰዓት እጅግ አንገብጋቢ ነው። ስለዚህ የፖለቲካ አካላት በጠቅላላ በኃላፊነት የተቀመጡት ሁሉ የግል ጥቅም ላይ ማተኰር ሳይሆን ይኸንን በማስተዋል በሁሉም መርሃ ግብርና ተግባር የጋራ ጥቅም ቅድሚያ መስጠት ይኖርባቸዋል፣ በአሁኑ ወቅት ተከስቶ ያለው የኤኮኖሚ የሰብአዊ የማኅበራዊ ቀውስ መንስኤ መዘጋት ሳይሆን በእውነቱ በተከሰተው ቀውስ እጅግ ለተጠቃው ድኻውና ወጣት የኅበረተሰብ ክፍል በማሰብ ከዚህ ቀውስ ለመላቀቅም የተከረታተፈ፣ ካንተ የተለየውን በጥርጣሬ የመመልከትና አንዱ በሌላው ላይ የመነሳት አዝማሚያ የሚታይበት ኅብረተሰብ አያንዳንዱ የሁሉም ሁሉም የአንዱ ክፍል መሆናቸው የሚያስገነዝብ ሕንጸት ያለው አስፈላጊነት በመጠቆም ለዚህ ዓይነቱ ሕንጸት መንገዱን የሚያመለክት ነው። ስለዚህ የሁሉም የተበታተነው ሰብአዊ ሁነት የሚታይበት ኅብረተሰብ የተባባሪነትና የአሳቢነት ባህርይ ያለው እምቁ ኃይል ተጠቃሚ ማድረግ የሚል ነው።
ቤተ ክርስቲያን ባላት ክርስቶሳዊ ገጠመኝ እርሱም ሰው ሆኖ የመጣው ክርስቶስ አማካኝነት በሁሉም ሥፍራና በሁሉም ማኅበረሰብ ሥጋዌ በመሆን ኵላዊ ወንድማማችነት መሠረታዊ መመሪያ እንዲሆን ታንጻለች። ይኽ ደግሞ መልካም ፈቃድ ያላቸው ሁሉ ይኸንን እውነተኛውና ኩላዊ የሆነው መልካምነት-እግዚአብሔርን እንዲሻ ትመራለች፣ ይኽ ደግሞ ለኵላዊ ወድማማችነት መሠረት ነው ብለዋል።
ቤተ ክርስቲያን የዚያ በክርስቶስ የተለገሰው ጸጋ የሆነው እውነት በሙሉ ፍቅር በቃልና በሕይወት የምታስተምር የዚሁ ክርስቶሳዊነት ጽማሬ ነች፣ የእምነትና የአስፍሆተ ወንጌል ማኅበራዊ ገጽታው ቤተ ክርስቲያን ክፍለ አንቀጸ እምነት በማድረግ ፍቅር እጅግ በድኽነት ለተጠቃው ማለት መሆኑ ታስገነዝባለች፣ ድኽነታችንን ያየው እግዚአብሔር ሥጋችንን ልብሶ ወደ እኛ ለመምጣት ከገዛ እርሱ እንደ ወጣ ሁሉ፣ ቤተ ክርስቲያን ከገዛ እራሷ በመውጣት ምእመናንን ማኅበረ ክርስቲያንን በማነቃቃት ክርስቶስ በሁሉም በእያንዳንዱ ሰው ዘንድ እንደሚገኝና ሁሉም ይኽንን በእያናንዳንዱ ለሚገለጠው ክርስቶስ እንዲጠመድ በቃልና በሕይወት ታስተምራለች። የቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ ትምህርት ትስብእት ዳግም መኖር ማለት ነው።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ካለ መታከት ለምሁራን ለሊቃውንት ለሕክምና ባለ ሙያዎች ለመንግሥታት ለሁሉም ካለ መታከት ዴሞክራሲ ዙሪያ የሚሰጡት ምዕዳን የዴሞክራሲ የላቀው ክብሩና ትርጉሙን የሚያስተጋባ ነው። እርሱም የዴሞክራሲ ማኅበራዊ አድማሱንና የሕዝብ ተሳትፎ የሚለው ክብሩን የሚያብራራ ነው። የሁሉም ሰው ዘር መሠረታዊ አስፈላጊ የሆነው ቤት መጠለያ ምግብ ትምህርት ሕንጸት ሥራ የሕክምና አገልግሎት ፍትሃዊ የፍር ቤቶች አሰራር የሚያንጽ እንጂ የሰው ልጅ ክብር የሚሰርዝ እንዳይሆንና ሰብአዊ መብቱና ክብሩ አለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲረጋገጥለት የኤኮኖሚ አውታሮች ባለ ሃብቶም መንግሥታት ለዚህ የላቀው ክብር አገልግሎት የተጥሩ መሆናቸውና የሰው ልጅ ሰብአዊ ክብርና መብት እንዲሁም የሁሉም የጋራው ጥቅም የሚያረጋግጥ መሆን እንዳለበት የሚያስገነዘብ ሥልጣናዊ ትምህርት ነው። የቤተ ክርስቲያን የአንቀጸ እምነት ማኅበራዊ ትምህርት እግሮችና እጆች እኛ ነን፣ የቤተሰብ መሆናዊ ውበቱና ውህበቱ የኅብረተሰብ ማእከል እንደሆነም የሚያረጋግጥ መሆኑ ገልጠው፣ ቅዱስ አባታችን ለበዓሉ ባስተላለፉት መልእክት፦ “ጦርነት ለማቀጣጠል የጦር መሣሪያ ለማካበት ለጦር መሣሪያ ግዥ የገንዘብ ሃብት ይገኛል ድኽነት እርሃብ ለመቅረፍ ግን የገንዘብ ሃብት እንዴት እንደማይገኝ ይገርማል። ስለዚህ ችግሩ ገንዘብ ሳይሆን ሰው ነው። ማለትም አመለካከት ማደስ ሰብአዊነት ማስቀደም ያስፈልጋል” ያሉትን ጠቅሰው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.