2014-11-21 16:23:44

የመላ ካቶሊካውያን ማኅበራትና እንቅስቃሴዎች በጋራ ለበሰለው ቤተ ክርስቲያናዊነት መንፈስ


RealAudioMP3 የዓለማውያን ምእመናን ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያዘጋቸው “ወንጌል ኃሴት የወንጌላዊ ልኡክነት ኃሴት ነው” በሚል ቃል የተመራው ሦስትሰኛው ዓለም አቀፍ የመላ ካቶሊካውያን ማኅበራትና እንቅስቃሴዎች ዓውደ ጉባኤ እ.ኤ.አ. ህዳር 20 ቀን 2014 ዓ.ም. በጳጳሳዊ የቤተ ክርስቲያን እናት ቅድስት ማርያም መንበረ ጥበብ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ የዓለማውያን ምእመናን ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ስታኒስላው ርይልኮ ባሰሙት ንግግር በይፋ መጀመሩ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሮበርታ ጂሶቲ ገለጡ።
ይኽ እ.ኤ.አ. እስከ ህዳር 23 ቀን 2014 ዓ.ም. የሚዘለቀው ዓውደ ጉባኤ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ወንጌላዊ ኃሴት በተሰየመው ሐዋርያዊ መልእክት አማካኝነት ደጋግመው ያሳሰቡት ወንጌላዊ ኃሴት በማጤን ወንጌልን በኃሴት ማበሰር በአሁኑ ወቅት የሚጋረጠው መሰናክል ሁሉ ለመለየት የሚመክር መሆኑ የገለጡት ልእክት ጋዜጠኛ ጂሶቲ አያይዘው፣ በዚህ ጉባኤ በብዙ መቶዎች ከሚቆጠጡሩ ከተለያዩ ካቶሊካውያን ማኅበራትና እንቅስቃሴዎች የተወጣጡ አምስቱን ክፍለ ዓለም የሚወክሉ በጠቅላላ 300 ልኡካን እየተሳተፉ ሲሆን፣ ብፁዕ ካርዲናል ርይልኮ ዓውደ ጉባኤውን በንንግር ለመክፈት ባሰሙት ንግግር፦ “ካቶሊካውያን እንቅስቃሴዎችና ማኅበራት ካቶሊክ የሚያስብላቸውን የኵላዊነት አድማስ የሚያስተጋቡና የሚኖሩ መሆን አለባቸው። በርን ከፍቶ መውጣት፣ ሌላው ጋር ለመገናኘት ከገዛ እራስ መውጣት ማለት ነው” ይኽ ደግሞ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያሰመሩበት ሥልጣናዊ ትምህርት መሆኑ ለተጋባእያኑ ማስታወሳቸው ገልጠዋል።
በጉባኤው በመሳተፍ ላይ የሚገኙት ዓለም አቀፍ የካቲሊካዊ የተኃድሶ ማኅበር ኃላፊ ማተዮ ካሊስቲ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃል ምልልስ፦ የወንጌል ኃሴት መኖርና በቃልና በሕይወት በኃሴት መመስከር የሚለው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሥልጣናዊ ትምህርት እንዴት መኖር ይቻላል? እንዴት በወንጌላዊ ልኡክነት ለመኖር ይቻላል? ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊም ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛም ከዚህ በፊት እንዳሉት ካቶሊካውያን ማኅበራትና እንቅስቃሴዎች ልኡካነ ወንጌል ናቸው ይኽ ደግሞ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በማስተጋባት ሆኖም ምስክርነት በኃሴት መሆን እንዳለበት ያሰምሩበታል። እነዚህ ማኅበራት በእውነቱ ይኽ ከገዛ እራስ መዘጋት ተላቆ ወደ ጥጋ ጥግ የከተሞቻችን ክልሎችና ወደ የህልውና ጥጋ ጥግ እንዲንወጣ ቅዱስነታቸው ላቀረቡት አደራ ተቀብሎ አወንታዊ ምላሽ ለመስጠት የሚያግዘው መንገድ በጋራ ለመቀየስ የሚካሄድ ዓውደ ጥናት መሆኑ ገልጠዋል።
ወንጌላዊነት ከአንድ ርእዮት ወይንም ሃሳብ ጋር ሳይሆን ከአንድ አካል ኃያው ከሆነው ከጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ጋር ከሚጸናው ግላዊና ማኅበራዊ ግኑኝነት የሚመነጭ ነው። አለዚህ ግላዊ ግኑኝነት ወንጌላዊነት ሳይሆን ገዛ እራስ ወንጌል አድርጎ ማቅረብ ነው የሚሆነው። ወንጌሉ እኛ ሳንሆን የተገናኘነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። የወንጌላዊነት ትርጉሙም ይኽ ነው። ወንጌላዊነት ሌላ ትርጉም የለውም።
ካቶሊካውያን ማኅበራትና እንቅስቃሴዎች ከመንፈስ ቅዱስ በሚታደሉት መንፈሳዊ መርሆ አማካኝነት በቤተ ክርስቲያን ፈቃድ ተቀባይነታቸው ተረጋግጦላቸው የሚመሠረቱ ናቸው፣ ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ካቶሊካዊ ማኅበርና እንቅስቃሴ ሊኖሩ አይችልም፣ በቅድሚያ ይኽ መገንዘብ ይኖርብናል፣ የተለያየ የቅዱስ መንፈስ ስጦታ የአንዲት ቤተ ክርስቲያን ውህደትና አንድነት ማረጋገጫ ነው። ይኽ ደግሞ የዛሬ 50 ዓመት በፊት ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ መለስ ብሎ በማስታወስ ውሳኔዎችንና ሰነዳቱን ማንበብ ያለው አስፈላጊነት የሚያመልክት ነው፣ ካቶሊካውያን ማኅበራትና እንቅስቃሴዎች የተቀበሉት መንፈሳዊ መርሆና የቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ሥልጣን ተገናኝተው ቤተ ክርስቲያናዊነት እንዲኖርና ይኸንን መኖር በኃሴት በመኖር በኃሴት ለመመስከር ከቤተ ክርስቲያን መርህ ቃል የሚቀበል ጉባኤ ነው ብለው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.