2014-11-03 15:17:02

በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ከቤተሰብ ጋር


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ከህዳር 11 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በኢጣሊያ ካምፓኒያ ክፍለ ሃገር ርእሰ ሰበካ ካፑዋ በምትገኘው በቅድስት ማርያም ዘካፗ ቨተረ ቁምስ የሰበካው የቤተሰብ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሚከታተለው ቢሮ ያዘጋጀው በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ከቤተሰብ ጋር በሚል ዓላማ የተነቃቃ የሕንጸት መርሃ ግብር እንደሚጀመር የካፑዋ ርእሰ ሰበካ ያሰራጨው መግለጫ ይጠቁማል።
በዚህ የሕንጸት መርሃ ግብር የቲዮሎጊያ የቤተሰብ ቲዮሎጊያ የሥነ ቤተሰብ ሊቃውንት አስተምህሮ በማካፈል የሚሳተፉ ሲሆን፣ የሚሥጢረ ተክሊል ቲዮሎጊያዊ ሥነ ቤተ ክርስቲያናዊ መጽሓፍ ቅዱሳዊ ትርጉሙና መሠረቱ ጋብቻና ፍቅር ስለ ጾታዊ ስሜት በወላጅና ልጅ መካከል የሚኖረው ግኑኝነት በባልና በሚስት መካከል ስለ ሚፈጠረው ግኑኘንት ርእስ ዙሪያ ሕንጸት የሚስጥበት መሆኑ የገለጠው የካፑዋ ርእሰ ሰበካ መግለጫ አክሎ በዚህ በምንኖርበት ዓለም የሚታየው የጾታዊ ስሜት መዛባትና መደናገር ሚሥጢረ ተክሊልና ታማኝነት በተሰኘው ርእስ ዙሪያ ሰፊ አስተምህሮ የሚቀርብና ቤተሰብ የኅብረተሰብ ማእከል ከመሆኑ እንጻር ጤናማ ቤተሰብ ለጤናማ ኅብረተሰብ መሠረት በመሆኑም ቤተሰብን በመንከባከብ ኅብረተሰብና አገርን መገንባት ምን መደረግ አለበት ለሚለው መሠረታዊ ጥያቄ በሥነ ማሕበራዊ ሥነ ልቦናዊ በመሳሰሉት የምርምር ጥናቶች የተደገፈ መልስ የሚሰጥበት የሕንጸት መደብ እንደሚሆን አስታውቀዋል።
በቤተሰብ መሃል ለሚፈጠረው አለ መግባባት ለመፍታት ላለመግባባት ምክንያት የሆነው እንዴት መለየትና መፍትሔ እንዲያገኝ ማድረግ፣ በወላጅና ልጅ መካከል የሚፈጠረው አለ መግባባት ጭምር ከዚህ ጋር በማያያዝም ቤተሰብ የጸሎት የክርስትና ሕይወት የሚኖርበት እንዲሆን ማነጽና የዚያች ቅድስት ቤተሰብ አብነት ላይ ባነጣጠረ ሥነ ሕንጸት አማካኝነት ቤተሰብ ጥልቅ ትርጉም እንዲከተል ለማድረግ ቤተሰብ የመጀመሪያ ቁምስና መሆንዋ በጥልቀት እንዲስተዋል የሚደግፍ የሕንጸት መርሃ ግብር መሆኑ የካፑዋ ርእሰ ሰበካ መግለጫ ያመለክታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.