2014-10-27 15:39:20

ጸላይ ሕይወት


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ጥቅምት 22 ቀን 2014 ዓ.ም. በላቲን ሥርዓት ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ቅድስና ካወጀችላቸው ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ የሚዘከሩበት ዕለት ማክበሯ ሲገለጥ፣ ስለ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ መንፈሳዊ ሕይወት በማስመልከት የቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ትውልድ አገር ዜጋ የሥነ ቫቲካን ሊቅ ውሎድዚማየርዝ ረድዚዮች ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ጸላይ የተመስጦ ሕይወትና የሰቂለ ህሊና ሕይወት ጥልቅ የጸሎት መንፈስ መስካሪ በማለት ገልጠው ከሳቸው ጎን በመሆን የኖሩት ዓመታት የጸጋ ዓመታትና ካንድ ቅዱስ ጎን የተኖረ ሕይወት ሲሉ መስክረዋል።
አለ ጸሎት ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ለመረዳት የሚቻል አይደለም፣ የኖሩት የተመስጦ ሕይወት ምንኛ ኢየሱስ ክርስቶሳዊ ሕይወት ይኖሩ እንደነበር የሚገልጥ ጧት በሳቸው የግል ቤተ ጸሎት በተለያየ ምክንያት በተገኙበት ዕለት ይላሉ፣ ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ መስዋዕተ ቅዳሴ ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ ተንበርክከው ሲጸልዩ በሁለመናቸው የሚጸልዩ ሕይወታቸው ጸሎት እንደነበር ቀርበው ለመረዳት እንደቻሉ ገልጠው፣ አንዳንዴም ተንበርክከው በተመስጦ ጾሎት ላይ እያሉ አንገታቸውን ቀና በማድረግ ወደ ላይ ሲመለከቱ ስታይ ልክ ከአንድ ሰው ጋር የሚወያዩ የኢየሱስ ህላዌ የሚኖሩና እንዲሁም ብዙ ሰዎች እንዲጸልዩላቸው የሚያቀርቡት የጸሎት ሃሳብ የተኖረበት የማስታወሻ ወረቀት እፊታቸው አስቀምጠው ስለ ሁሉም ይጸልዩ እንደበነር ገልጠዋል።
የቅርብ ተባባሪዎቻቸው ስም የተኖርበት ወረቀት እፊታቸው በማስቀመጥ ስለ እነርሱ አንድ በአንድ ሁሌ ይጸልዩ እንደነበር በቅርብ የተመለቱት ተመክሮ መሆኑ ገልጠው፣ ዮሓንስ ጳውሎስ የተወለዱባት ቤተ ሰብ በቁሳዊ ድኽነት የተጠቃች ከዛም እሳቸው ካህን ሆነው በድኽነት መኖር ያፈቀሩ ምንም ዓይነት ቁሳዊ ሃብት ማካበት የሚል ፍላጎት ያላጠቃቸው ባገለገሉበት ሰበካ በክራኮቪያ የሰበካ ሕንጻ ከዛም በሰበኻው መስተዳድር ሕንጻ ይኖሩ በነበሩበት ወቅት እዛው ያገኙት ንብረት የሚጠቀሙ እንጂ ይዘዉት የሚመጡትና ይዘዉት የሚሄዱ ምንም አይነት ንብረት እንዳልነበራቸው ገልጠዋል።
ዮሓንስ ጳውሎ ዳግማዊ የተመስጦ ሕይወት ይኖሩት የነበሩ በቅዱስ ቁርባን ፊት ተንበርክከው መጸለይ ካለ ማቋረጥ የሚያዘወትሩ በእውነቱ ስለ እሳቸው የተመስጦ ሕይወት ለመናገር እጅግ ያዳግታል፣ ምክንያቱም የአንድ ጸላይ የተመስጦ ጥልቅ ሕይወት የሚያውቀው ገዛ እራሱ ነው። ስለዚህ ይኸንን እሳቸው የሚኖሩት የተመስጦ ጸላይ ሕይወት ለመረዳት በጥልቅ ለመገንዘብ እሳቸው ይደርሱት የነበረው መንፈሳዊ የግጥም ድርሰት ማንበብ ያስፈልጋል፣ የደረሱት መጽሓፍ ዓዋዲ መልእክት፣ ሓዋርያዊ መልእክት ማንበብ እሳቸው ይኖርት የነበረው የሰቂለ ህሊና ሕይወት ለመረዳት ይቻላል በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.