2014-10-15 14:48:13

ብፁዕ አቡነ ካኢጋማ፦ የሲኖዶስ ውሳኔ በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሚተረጎም ነው


RealAudioMP3 ካንድ ሚስት በላይ ማግባት የሚለው ባህላዊ ኃይማኖታዊ ጉዳይ ለቤተሰብ አቢይ ተጋርጦ መሆኑ በአገረ ቫቲካን በመካሄድ ላይ ያለው ሦስተኛው ልዩ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ያሰመረበት ሃሳብ በማስደገፍ በናይጀሪያ የጆስ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ኢግናዚዩስ ካይጋመ ከቫቲካን ርዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ከአፍሪቅ ባህል ጋር የተያያዘ ጉዳይ አለ መሆኑና በአፍሪቃ ባህል በጠቅላላ ሊባል ይቻላል ጋብቻ በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት የሚል ግንዛቤ ያለው ነው፣ ይኽ ደግሞ ለቤተሰብ መረጋጋት መሠረት ብቻ ሳይሆን ባለ መረጋጋት ለሚኖር ቤተሰብና አገር ጭምር ለመረጋጋት አቢይ ድጋፍና አብነትና መሆኑ ገልጠዋል።
በአንዳንድ የአፍሪቃ ባህሎች ከአንድ ሚስት በላይ ማግባት የተፈቀደ ሊሆን ይችላል፣ ሆኖም በአፍሪቃ ክልል የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጋብቻ በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት የሚለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት በማቅረብ ይኸንን ቲዮሎጊያዊ መሠረት ያለው ሃሳብ በተለያዩ የሥነ እውቀት ዘርፍ አማካኝነትም በማብራራት ከአንድ ሚስት በላይ ያላቸው የክርስትና እምነት ለመቀበል የሚመጡ አሉ፣ ስለዚህ ለእነዚህ ዜጎች መልስ የሚሰጥ ሲኖዶስ ይኸው እየተካሄደ ነው። ይኽም በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሚገለጥ መልስ እንደሚሆን አብራርተው፣ የቤተ ክርስቲያን ውሳኔ ምኅረትና ፍቅር ነው። በማንኛውም ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መንጸባረቅ ያለበት መሠረተ እምነትም እርሱ ነው። ከዚህ ቀደም አበይት የቲዮሎጊያ ሊቃውንት የሲኖዶስ አበው እንዳሉት የቤተ ክርስቲያን ሥርወ እምነት በትረ ፍርድ ሳይሆን የምህረት ቃል ነው። በመሆኑም ቤተ ክርስቲያን በዚህ በምንኖርበት ዓለም የሚታየው የቤተሰብ ተጋርጦ በሥነ እወቅት ዘርፍ ብቻ ሳይሆን ከሁሉም በላይ በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሚተረጎም መልስ ለመስጠት የሚችል ውይይት እያካሄደች ነው በማለት የሰጡት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.