2014-10-15 14:40:46

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ እምነት ከተጨባጭ የፍቅር ሥራ የተነጠለ መዋቢያ ኵል አይደለም


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 14 ቀን 2014 ዓ.ም. እንደ ተለመደው ማለዳ በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው እምነትና ፍቅር የማይነጣጠሉ መሆናቸው የሚያብራራ ሥልጣናዊ አስተንትኖ መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።
እምነት መሳይነት ሳይሆን መሆንን ነው የሚመለከተው። ይኽም በሁለመና በየትም ሥፍራ የሚኖር እንጂ በተመስሎ የሚኖር አይደለም፣ በአስመሳይነት የሚኖር ትህትና አክብሮት የተሞላህ ሆነህ ለመቅረብ ሳይሆን በገርነትና በንጽሕና የሚያፈቅር ልብ የሚገለጥበት መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በላቲን ሥርዓት የዕለቱ የሉቃስ ወንጌል ምዕ. 11፦ 37-41 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈሪሳውያንና የሙሴ ሕግ መምህራን ሲወቅስ የሚናገረው ቃል መሠረት በማድረግ ገልጠው፦ በማዕድ ከመቀመጥህ በፊት እጅህን አጥርተህ ታጠብ የሚለው ሕግ ባለ ማክበሩ ፈሪሳዊው ይገረማል፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሕግ ላይ የሚጸና ድህነት ሕግ ባፈረስክ ቁጥር ሕጉ በገዛ እራሱ የሚያወግዝህ መሆኑ በማስታወስም ሕግ ከማክበር የሚገኘውን ዓይነት እርግጠኛኘት ጌታችን ያወግዛል፦ “ኢየሱስ የዚህ ዓይነት አስመሳይ መንፈሳዊነት ያወግዛል፣ መልካም ደጋ ደጎች ሆነን ለመታየት ይቃጣናል፣ እውነትነቱ ግን ውስጥነት ነው። መልካም አግባብ ያላቸው ነገር ግን ክፉ ልማድ ያላቸውን ሁሉ ኢየሱስ ያወግዛቸዋል፣ እነዚያ በስውር በድብቅ ክፉ ልማዶችን የሚፈጸሙትን ያወግዛል፣ በርግጥ ውጫዊ መግለጫ አወንታዊ ነው፣ በአደባባይ መፈሳዊ ጸላይ ተመስሎ ሲጾሙ ፊታቸውን የከፋው አስመስለው የሚታዩት የሚያሳዩት ውጫዊነት ግን ከሕይወት ጋር የተቆራኘ ባለ መሆኑ አሉታዊ ነው፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለቱ ወንጌል የሚጠቀምባቸው ሁለት አመልካች ግሶች፦ ‘ቅምያና ክፋት’ በማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 23 ዘንድ እንደተመለከተው የዚህ የሉቃስ ወንጌል ተመሳሳዩ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈሪሳውያንና የሙሴ ሕግ መምህራን ሲወቅስ፦ “በኖራ የተለሰነ የሚያምሩ የመቃብር ግንቦች” በማለት ይገልጣቸዋል፣ በብሉይም በአዲስ ኪዳንም ስለ ምጽዋት ብዙ ተነግረዋል፣ ይክ ደግሞ ከፍትህ ጋር የተጣመረ ህሳብ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ገልጠው፣ ቅዱስ ጳውሎስ በዕለቱ በተነበበው ወደ ገላቲያ ሰዎች በጻፋት መልእክቱ ምዕ. 5፦ 1-6 ሕግ ለብቻው አያድንም” ይላል፣ አስፈላጊው እምነት ነው፣ በፍቅር ሥራ የሚገለጥ እምነት እንጂ ተአምኖተ እምነት መድገም ብቻ በቂ አይደለም። ሁላችን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ እናምናለ፣ አምናለሁ እንላለን፣ሁላችን እናምናለን፣ ሆኖም ግን ይኽ እምነት የማይንቀሳቀስ ባለበት የሚሄድ በግብር የማይሸኝ እምነት ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን የሚመነጨው ከእምነት የሚመነጭ ተግባር ነው። ማለትም በፍቅር ሥራ ከሚገለጥ እምነት የመነጨ ነው። ምጽዋት ከገንዘብ ሃብት አምባገነን ከገንዘብ ሃብት አምልኮ መላቀቅ ማለት ነው። ስስታምነት ከኢየሱስ ክርስቶስ ያርቀናል” ብለው በአንድ ወቅት የኢየሱሳውያን ማኅበር ጠቅላይ አለቃ በመሆን በ 1970 ዓመታት ያገለገሉት አባ አሩፐ ያጋጠማቸው እርሱም በጃፓን የኢየሱሳውያን ማኅበር ለሚያካሄደው ወንጌላዊ ተልእኮ ድጋፍ እንዲሆን አንዲት ሴት አባ አሩፐ በጋዜጠኞች ፊት መግለጫ እየሰጡ እያሉ ገንዘብ የታሸገበት ፖስት ትሰጣቸዋለች እስዋም በጋዜጠኞች ፊት የተፈጸመ ተግባር መሆን ደስ ሳይላት ነበር የቀረው፣ በኋላ ለብቻቸው ሆነው ፖስታው ሲከፍቱ በውስጥ አስር ዶላር ብቻ ያገኛሉ የተረፋት ሳይሆን ያላት ሁሉ ሰጠች” የሚለው የጌታ ቃል እንዳስታወሳቸውና በግብር የሚገለጥ እምነት እንደነበራት የሚያረጋግጥ የፍቅር ምልክት መሆኑ ነው በማለት ይገልጡታል፦ “ኢየሱስ የሚመክረን የነጋሪት ጥሩምባ አትንፉ፣ በሁለተኛው ደረጃ የተትረፈረፋችሁ አትስጡ፣ የነበራት ሁሉ ሰጠች ይኸንን እናስታውስ፣ ያላትን ሁሉ የሰጠቸው በመታበይ ሳይሆን ያላት ሁሉ ጥቂት በመሆን አፍራ ተደብቃ ነበር የሰጠቸው፣ ያሳፈራትም ያላት ጥቂት በመሆኑ ሳይሆን ከዚያ በላይ ለመስጠት ባለ መቻልዋ ነው፣ ብዙ ቢኖራት ኖርም ብዙውን በሰጠች ነበር” ብለው ከፍቅር ሥራ የተነጠለ እምነት የሞተ መሆኑ እናስታውስ በማለት የለገሱት ሥልጣናዊ አስተንትኖ እንዳጠቃለሉ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.