2014-10-08 15:36:37

ሲኖዶስ፣ ብፁዕ ካርዲናል ፊሎኒ፦ የኢራቅ ቤተሰቦች


በኢራቅ ለተለያየ ችግር ለከፋና አደገኛ ስጋት ለጭፍጨፋ ለጅምላዊ ቅትለት አደጋ ተጋልጠው የሚገኙት ቤተሰቦች እምነታቸው ላለ መካድ ቤትና ንብረታቸውን እየጣሉ ተገደው ለስደትና ለመፈናቀል ምርጫ መዳረጋቸው በዚህ በመካሄድ ላይ ባለው ሲኖዶስ በመሳተፍ ላይ የሚገኙት በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ውሳኔ መሠረት በቅርቡ በኢራቅ የሁለት ሳምንት ሐዋርያዊ ጉብኝት አካሂደው የተመለሱት ለአሕዛብ አስፍሆተ ወንጌል የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ፈርናንዶ ፊሎኒ ከሲኖዶስ የሁለተኛው ቀን ውሎው ፍጻሜ በኋላ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠዋል።
በኢራቅ ያለው ዜጋ በሚከተለው ሃይማኖት ወይንም አባል በሆነበት ጎሳ አማካኝነት ውሁዳን የኅብረተሰቡ ክፍል ለመሆን የበቃው ዜጋ የገዛ እራሱ እምነት ክዶ የምስልምና እምነት እንዲቀበል የሚገደድ በመሆኑ፣ እምነቱን ከመካድ ስደት እየመረጠ መሆኑ ብፁዕ ካርዲናል ፊሎኒ ገልጠው፣ በኢራቅ ሐዋርያዊ ጉብኝት ባካሄዱበት ወቅት ቤተሰቦች በሚጋጥማቸው ችግርና መከራ አንድ በመሆን ሁሉንም በአንድነት በመጋፈጥ ከአደጋ ለማምለጥ ሲንቀሳቀሱም በህብረት ሳይለያዩ የሚኖሩት የክርስትያናዊ ኅብረት እንዳስደነቃቸው ገልጠው፣ የኢራቅ ክርስቲያን ቤተሰቦች በደስታ በችግር አብረው ሳይለያዩ ሳይነጣጠሉ የሚመሰክሩት ውህደትና አንድ ሆኖ የመኖር ጥሪ በእውነቱ ለብዙ ክርስቲያን ቤተሰብ አብነት ነው በተለይ ደግሞ ቤተሰብ ርእስ ዙሪያ ለሚመክረው ሲኖዶስ አቢይ ርእሰና ምስክርነትም ነው ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 5 ቀን 2014 ዓ.ም. ስለ ቤተሰብ የሚመክረው ሲኖዶስ በይፋ ለማስጀመር በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ መስዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው ባሰሙት ስብከት የኢየሱስ ክርስቶስ ባህርይና የኢየሱስ ምሥጢር ማእከል ይሁን ያሉትን ሃሳብ ብፁዕነታቸው አስታውሰው፣ በእውነቱ ኢየሱስ በሕይወቱ ያንን ወቅታዊ ብለን የምንገልጠው ሁኔታ ገና ከወዲሁ በመኖር መልስ ሰጥቶበታል፣ ስለዚህ ጉዳይ በዚህ በወቅታዊው ዓለም ለሚታየው ችግር ስቃይ አመጽ ኢየሱስ ምን መልስ በሰጠበት ነበር ሳይሆን፣ የሰጠው መልስ ምን እንደነበር መሻት ነው። ክርስትናም ይኽ ነው፣ የዮሓንስ መጥምቅ ሕይወት መመልከቱ ይበቃል፣ እምነቱን አቅቦ ለመኖር በመሻቱ ምክንያት መሥዋዕት ሆነ፣ ሄሮዶስ ከወንድሙ ሚስት ጋር መኖር ለመሳሰሉት ዓይነት ምርጫዎች ዮሓንስ መጥመቅ እንቅፋት ሆኖ ነው የተገኘው፣ የቤተ ክርስቲያን ተልእኮም የዮሓንስ መጥምቅ ተልእኮ ነው፣ ወደ ኢየሱስን በመቅረብ ላይ በማደግ ኢየሱስን ማሳወቅ። ኢየሱስ ለሳምራዊቷ ሴት እውነቱን ይነግራታል ስለ ማንነቷ ይገልጥላታል ከዚህ ከሚገልጠው እውነት ግን መኃሪነቱን አላገለለም፣ እውነትና ምህረት ተያይዘው የሚሄዱ ናቸው፣ ሆኖም አለ እውነት ምህረት የለም፣ በመካሄድ ላይ ያለው ሲኖዶስ እውነትና ምህረት በጥልቀት የሚያስተውል ነው ሲሉ ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.