2014-10-08 15:39:48

ሲኖዶስ፣ ብፁዕ ካርዲናል ስግረቻ፦ በቀጣይ ሕንጸት የሚያገኝ ቤተሰብ ጽናት ይኖረዋል


እ.ኤ.አ. ጥቅምት 7 ቀን 2014 ዓ.ም. የሲኖዶስ ውሎው በማስመለከት የጳጳሳዊ የሕይወት ተቋም ሊኂቅ ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ኤሊዮ ስግረቻ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ “የቤተሰብ ወንጌልና ባህርያዊ ሕግ” የተሰኙት ቀድሞ በተሰናዳው በሲኖዶስ የውይይት ማካሄጃ የዝክረ ነገር ሰነድ ዘንድ የተመለከተው ርእስ ዙሪያ መወያየቱ ገልጠው፣ ባህርያዊ ሕግ ማለት የተፈጥሮ ህግ በሚገባ ካለ መረዳትና ካለ ማስተዋል የሚከናወነው ጸረ የተፈጥሮ ሕግ ተግባር ወይንም የሕግና ፍትህ መመሪያዎች ውሳኔ እንዲነጻ የሚገፋፋ መሆኑ አስታውሰው፣ ስለዚህ ከዚህ አንጻር ቤተ ክርስቲያን የተፈጥሮ ሕግ በሚገባ በጥልቀት በማስተማር በአመክንዮ የተደገፈ ተስተውሎ እንዲያገኝ በማነጽ፣ የፍጥረት ሥርዓት የሰው ልጅ ሊገነዘበውና ሊያስተውለው እንደሚችል በማሳወቅ ተልእኮ ቤተ ክርስቲያን አቢይ ኃላፊነት አለባት፣ በመሆኑም በቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ቀጥተኛ ተሳታፊ የሆኑት ሁሉ የተፈጥሮ ባህርያዊ ሕግ ግዳይ ጥልቅ ግንዛቤ እውቀቱም ያላቸው ሊሆኑ ይገባል፣ በዓለም እየተስፋፋ ያለው ሥነ ምግባርና ትምህርት ኢሃይማኖታዊ መሠረት አለው የሚለው ባህል የተፈጥሮ ህግና ግብረ ገባዊ ሕግ ወድቅ ነው የሚለው በዚህ እየተስፋፋ ባለው ባህል አማካኝነት የዘፍጥረት ጥልቅ ትርጉም እንዳይስተዋል ተደርጎ በተለያየ መስክ ችግር እያስከተለ መሆኑ አብራርተው፣ የዘፍጥረት የኅልውና የተፈጥሮ ባህርያዊ ሕግ ትርጉምና ዓላማ ካልተስተዋለ ሕይወት ጭምር ትርጉም የሌለው ተመስሎ ነው የሚደቀነው፣ የሕይወት የተፈጥሮ ውበትና ውህበት በጥልቅ ለማስረዳት የእረኞች ቅድመ ዝግጅትና ሕንጸት በእውነቱ ጥልቅ ሊሆን ይገባዋል፣ ሰብአዊ ሕንጸት ወሳኝ ነው ሆኖም ግን በተለያዩ የሥነ ትምህርት ዘርፍ ጭምር የሰለጠነ መሆን አለበት። ወቅታዊው ዓለም የሚጠይቀው ጉዳይ ነው። መንፍሳዊ ሰብአዊ ስነ እውቀት (በሥነ ምርምር) ጭምር ያካተተ የተሟላ ሕንጸት ያገኝ ዘንድ ይጠበቅበታል፣ የሕግ ሊቅ የሥነ ልቦና ሊቅ የሥነ ሕክምና ሊቅ የሥነ ሕጽነት ሊቅ ወዘተ በተለያዩ የምርምር ሥነ እወቅት ዘርፍ የሰለጠኑ እረኞች አስፈላጊ ናቸው፣ ከዚህ አንጻር በዓለም በቤተሰብ ለሚከሰተው ችግር የተሟላ መልስ ለመስጠት ጥልቅና ሰፊ ቅድመ ዝግጅት ይጠይቃል፣ ለቤተሰብ ሕንጸት በሚገባ የታነጹ እረኞች ወሳኝ ነው ሲሉ ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.