2014-10-06 15:41:39

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ፦ ስፖርት ለያይ አጥርና ሌላውን የማግለል ባህል እንዲወገድ የሚያደርግ አገናኝ ባህል ነው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 4 ቀን 2014 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን ጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አድራሽ አካለ ስንኵላን ስፖርተስኞችን ተቀብለው ዓለም አቀፍ የአካለ ስንኵላን ስፖርት ውድድር ስፖርት ለያይ አጥርና ሌላውን የማግለል ባህል መሆን እንደሌለበት የሚያበቃ ተግባር የሚመሰክር ባህል የሚኖር ነው በሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ ያነጣጠረ መልእክት መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ አስታወቁ።
“ስፖርት ከተለያዩ ባህሎች ሃይማኖቶችና ጎሳዎች አገሮች የተወጣጡ የሚያገናኝ በሰዎች መካከል ግኑኝነት መቀራረብ እንዲኖር የሚያነቃቃ ካንተ የተለየውን በማስተናገድ አብሮ በመከባበርና በመቀባበል የሚለውን እሴት እንዲኖር የሚደገፍ አቢይ ሃብት ነው። ስለዚህ ስፖርት በሰዎች መካከል ግኑኝነት እንዲጸና በማድረግ ሌላውን ማግለልና በጥቅም አንጻር በመፍረድ ተጠቅሞ መጣል የሚለው ጸረ ሰብአዊ ባህል እንዲወገድ የሚደገፍ ነው” እንዳሉ ጂሶቲ አመለከቱ።
የሚያጋጥመው አካላዊ እንቅፋት እርሱም አከለ መሰንከል መልካም ከማድረግ የማያሰናክ በሰዎች መካከል የሚፈጠረው መለያየት ለማስወገድ የሚያበቃ እሴት የሚንጸባረቅ መሆኑ ያብራሩት ቅዱስ አባታችን የዚህ እሴት ኅያው ምስክርነትም ዓለም አቀፍ የኦሎምፒስ አካለ ስንኵላን ስፖርት ነው እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረድዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አክለው፦ “የእናንተ አካል አስንኵላን ስፖርተኞች ምስክርነት አቢይ የተስፋ ምስክርነት ነው። የሰው ልጅ ምንም’ኳ ያጋጠማችሁ አካላዊ ስንክልና ለብዙ ነገር እንቅፋት ተመስሎ ቢገለጥም በበእያንዳንዱ ሰው ልጅ ላለው እምቅ ኃይል ምስክሮች ናችሁ። የምታካሂዱት ስፖርትና የምትፈጽሙት ልምምድ ሁሉ የሰብአዊ ፍቅር መግለጫና ሁሉም አለ ምንም ልዩነት የሚኖርበት ዓለም ለመፍጠር አቢይ አስተዋጽኦ የሚስጡት እድሉንም የሚፈጥሩ ማመስገን ይገባል፣ ስፖርት እግዚአብሔርንና ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ለማፍቀር የሚያነቃቃ ኃይል ነው” በማለት ያስደመጡት ንግግር እንዳጠቃለሉ አስታወቁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.