2014-10-03 14:51:14

አገረ ቫቲካን፦ ስለ መካከለኛው ምሥራቅ ወቅታዊ ሁኔታ የሚመክር ጉባኤ: ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ የጦር መሣሪያ ንግድና ዝውውር አወገዙ


RealAudioMP3 በግብጽ በእስራኤል በኢየሩሳሌልም በፍልስጥኤም በዮርዳኖስ በኢራቅ በኢራን በሊባኖስ በሶሪያ በቱርክ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡካን፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኒው ዮርክ በሚገኘው ዋና መቀመጫውና በጀነቭ በተባበሩት መንግሥታት ማኅበራት በኤውሮጳ ኅብረት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢዎች፣ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የቅርብ ተባባሪዎች አበይት የሮማዊት ቤተ ክርስቲያን ባለ ሥልጣናት ብፁዓን ካርዲናሎችና ብፁዓን ጳጳሳት እነርሱም የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን፣ የቅድስት መንበር ተለዋጭ ምክትል ዋና ጸሓፊ፣ የቅድስት መንበር የውጭ ግኑኝነት ጉዳይ ተጠሪ፣ በቅርቡ በመካከለኛው ምስራቅ ሐዋርያዊ ጉብኝት አጠናቀው የተመለሱት ለአህዛብ አስፍሆተ ወንጌል ለሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ፊሎኒ፣ የምስራቅ አቢያተ ክርስቲያን የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ፣ ከተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር የሚካሄደው ውይይት የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት፣ የአቢያተ ክርስቲያን አንድነት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት፣ የፍትህና ሰላም ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት፣ የስደተኞችና ተጓዦች ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት፣ ጳጳሳዊ የውህድ ልብ ምክር ቤት ሊቀ መናብርት፣ በማሳተፍ ስለ መካከለኛው ምስራቅ እንዲወያይ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአገረ ቫቲካን እንዲካሄድ የጠሩት እ.ኤ.አ. እስከ ጥቅምት 4 ቀን 2014 ዓ.ም. የሚዘልቀው ዓውደ ጉባኤ ጥቅምት 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው ባሰሙት ንግግር በይፋ መጀመሩ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።
ይኽ በቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ንባብ በመካሄድ ላይ ያለው ዓውደ ጉባኤ በንግግር የከፈቱት ቅዱስ አባታችን፦ ጉባኤ የማኅበረ ክርስቲያን ህላዌ በመካከለኛው ምስራቅ የሚመለከት መሆኑ እንዳብራሩ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ተጠሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ለመረዳት ሲቻል፣ ቅዱስነታቸው ለዚያ ክልል ሕዝብ በጠቅላላ ቅርበታቸውን ለማረጋገጥና የክልሉ ቀውስ የሚዳስስና ሰላም ለማረጋገጥ የሚያግዘው መንገድ ለማፈላለግ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ባሰሙት ንግግር ገልጠው ጥሪው ተቀብለው በስብሰባው ለተገኙት አበይት የሮማዊት ቤተ ክርስቲያን አበይት አካላት ብፁዓን ካርዲናሎችና ብፁዓን ጳጳሳትን አመስግነው፣ በመካከከለኛው ምስራቅ ለሚገኙት ውሁዳን ሃይማኖት ምእመናን የክልሉ ሰላማዊ ሕዝብ ለከፋ አደጋ የሚያጋልጠው ሁከትና አለ መግባባት የሰው ልጅ ሕይወት ግምት የማይሰጥ መሆኑና ጦርነት ሽበራ የሚፈራረቅባቸው አገሮች የሚታየው ጸረ ሰብአዊ ተግባሮችን የሚደግፈው የጦር መሣሪያ ንግድና ዝውውር የጦር መሣሪያ አቅርቦት አውግዘው የክልሉ ሁኔታ እጅግ ለከፋ ሰብአዊ ስቃይ የሚዳርግ በመሆኑም ሕዝብ ቤቱንና ልብረቱን ጥሎ ለስደት መዳረጉንም አስታውሰው፣ ስለዚያ ክልል ሕዝብ እንዲጸለይ አደራ፣ ለዚያ ወንድም ለሆነው ህዝብ የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ቅርበት በማረጋገጥ ሁሉም የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ መልካም ፈቃድ ያላቸው ሰዎች ለሚሰቃየው ለዚያ ክልል ሕዝብ ትብብሩን ያቀርብ ዘንድ መማጠናችው አባ ሎምባርዲ ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል።
በመቀጠልም የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን የተጠራው ዓውደ ጉባኤ ትርጉምና ዓላማው ርእስ ዙሪያ ንግግር ሲያስደምጡ፣ የምስራቅ አቢያተ ክርስቲያን ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ሳንድሪ የክርስቲያኖች ሁኔታ በመካከለኛው ምስራቅ ምን ተመስሎው ርእስ ዙሪያ በመቀጠል ባስደመጡት ንግግር ተጋባእያኑ የሃሳብ ልውውጥ ማካሄዳቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ጉዳይ ተጠሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ገልጠው በማያያዝም፣ ከተካሄደው የሓሳብ ልውውጥ መርሃ ግብር ፍጻሜ በሶሪያ በኢራቅ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡካን በየተራ በሚያገለግሉበት አገር ያለው የማኅበረ ክርስቲያን ሁኔታና ስለ ንኡሳን ኅብረተሰብ ጉዳይ በሚመለከት ርእስ ሥር ንግግር አሰምተው እንዳበቁ ጳጳሳዊ የውሁድ ልብ ምክር ቤት ሊቀ መንበር የኩላዊት ቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማኅበራት በክልሉ ተከስቶ ያለው ሰብአዊ ችግር በመጋፈጥ ለሕዝቡ እርዳታ በማቅረብ እየሰጠው ስላለው አገልግሎትና የሚያጋጥመው እክል ርእስ ዙሪያ ንግግር አሰምተው ከተደመጡት ንግግሮች ቀጥሎ በተካሄደው የሃሳብ ልውውይ የግምሽ ቀን ስብሰባውን መጠናቀቁ አስታውቀዋል።
ከቀትር በኋላ ስብሰባው የተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር የሚካሄደው የጋራው ውይይት የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ዣን ልዊስ ታውራን ከምስልምና ሃይማኖት ጋር የሚደረገው የጋራው ውይይት ሂደቱና ያስጨበጠው ውጤት ከዛም በመቀጠል በቅርቡ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ውሳኔ መሠረት በኢራቅ ሐዋርያዊ ጉብኝት አካሂደው የተመለሱት የአህዛብ አስፍሆተ ወንጌል የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ፊሎኒ በኢራቅ ስላካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት ዘገባ አቅርበው እንዳበቁ ውይይት ከተካሄደበት በኋላ ተጋባእያኑ በጋራ ባሳረጉት ጸሎተ ዘሰርክ የመጀመሪያው የውይይት ቀን መዘጋቱ አባ ሎምባርዲ ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.