2014-10-01 16:07:36

የብራዚል ብፁዓን ጳጳሳት በአገረ ቫቲካን ለሐዋርያዊ ጉብኝት


RealAudioMP3 የካቶሊክ ብፁዓን ጳጳሳት በያምስቱ ዓመት በአገረ ቫቲካን ሓዋርይዊ ጉብኝት ለማከናወንና ከመንበረ ጴጥሮስ ጋር ያላቸውን ትሥሥር ውህደት ለመመስከር ለማጽናት፡ ለቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ታዛዥነታቸውን አንድነታቸውን ለመመስከርና የቅዱሳት ጴጥሮስ ዎጳውሎስ ቅዱስ አጽም ለመሳለም ስለ ቤተክርስትያናቸው ወቅታዊና አንግብጋቢ ርእሶች አስደግፈው ከቅዱሱ ኣባታችን ጋር በመወያየት መሪ ቃል የሚያገኙበት መንፈሳዊ ጉብኝት ምክንያት የብራዚ ልብፁዓን ጳጳሳት አገረ ቫቲካን መግባታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
በአፓረሲዳ ሊቀ ጳጳሳት የብራዚል ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ራይሙንዶ ዳማሰኖ አሲዚ የተመሩት የብራዚል ብፁዓን ጳጳሳት በብራዚል የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታ ቤተ ክርስቲያኒቱ በብራዚል የምትከተውለው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ፣ የብራዚል ወቅታዊ ሁኔታ ርእስ ዙሪያ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጋር መወያየታቸው ከግኑኝነቱ ፍጻሜ በኋላ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት ብፁዕ ካርዲናል ራይሙንዶ ዳማሰኖ አሲዚ ገለጡ።
ብፁዕነታቸው ይላሉ፣ በየዓመስቱ ዓመት የአንድ አገር ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በአገረ ቫቲካን መደበኛ ሐዋርያዊ ጉብኝነት ማከናወን በቤተ ክርስቲያን ባህል የተለመደ ነው ሆኖም በተለምዶ ይከናወናል ማለት ሳይሆን ቤተ ክርስቲያን ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር ያላት ትሥሥር የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ኩላዊነት የሚመሰክር ተግባር ነው። የብራዚል ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ክንዋኔዎችና አገልግሎቱ እንዲሁም ቀጣዩ የብራዚል ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ልዩ ጉባኤ ዝክረ ነገር፣ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ወንጌላዊ ሃሴት በተሰየመው ሐዋርያዊ ምዕዳን መሠረት ያደረገው ሰነድ ለቅዱስነታቸው ምክር ቤቱ እንዳቀረበና የብራዚል የእርሻ ፖለቲካ ወቅታዊው ሁኔታ የሚዳስስ ልዩ ጥናታው ሰነድ በተጨማሪም የብራዚል ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ስለ ወንጌላዊ ልኡክነትና በቤተ ክርስቲያንና በኅብረተሰብ በተሰኘው ርእስ ሥር የተጠናቀረው የጥናት ሰነድ ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መሰጠቱ ገልጠው ሆነው እነዚህ የቀረቡት የጥናት ሰነዶች ቅዱስነታቸው በሚሰጡት ምዕዳን መሠረት የብራዚል ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ውይይት በማካሄድ የምክር ቤቱ ሰነድ ብሎ በይፋ እንደሚያቀርበው አስታውቀዋል።
ከዚህ በመቀጠልም በብራዚል እ.ኤ.አ. ጥቅምት 5 የሚካሄደው ብሔራዊ ምርጫ በተመለከተ ብሎም በብራዚል ያለው የሕብዛዊ ምርጫ ደንብ በተመለከተ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጥናት ያካሄዱበት ሰነድ ለቅዱስ አባታችን ማረከቡ የገለጡት ብፁዕ ካርዲናል ራይሙንዶ ዳማሰኖ አሲዚ አክለው የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በፖለቲካና በምርጫ ጉዳይ ጣልቃ ገብነት የሌለው መሆኑም አብራርተው ለምርጫው የሚቀርቡት እጩዎች ያሳተፈ ክፍት ውይይት ይካሄድ ዘንድ የብፁዓን ጳጳሳቱ ምክር ቤት በጠራው ዓውደ ጉባኤ ሁሉም እጩዎች መሳተፋቸው ገልጠው ስለ ተካሄደው ዓውደ ጉባኤ የሚያወሳ ልዩ የጥናት ሰነድ ጭምር ለቅዱስ አባታችን መረከቡ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.