2014-09-26 17:13:05

ግብዝ ክርስትያኖች አያስፈልጉንም! እንደ የሳሙና አረፋ ናቸውና!


RealAudioMP3 ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍርናቸስኮስ ትናንትና በቅድስት ማርታ ቤተ ጸሎት ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ሁሉ ከንቱ ነው በሚለው የመጽሓፈ መክብብ ቃል ላይ በመመርኰዝ “ከከንቱነት እንጠንቀቅ ምክንያቱም ከእውነት ያርቀናል እንዲሁም እንደ የሳሙና አረፋ እንደምንመስል ያደርገናል፣ የዚህ ዓይነት ፈተና ያጠቃቸው ክርስትያኖች መልካም ነገር እንኳ ሲያደርጉ ለሰው እንዲታዩ ስለሚያደርጉት ግብዝነትና አስመሳይነት ያጠቃቸዋል፣ ክርስትያኖች ከዚህ ዓይነት ፈተና መራቅ አለባቸው” ሲሉ ተጨባጭ የሆነ ጥልቅ እምነት ከሌለን እኛም እንደ ሌሎቹ ነገሮች የከንቱ ከንቱ ሆነን እንደምንቀር አስገንዝበዋል፣
ቅዱስነታቸው አያይዘውም ኢየሱስ እንዲህ ዓይነት ሰዎች እጅግ እንደሚያወግዛቸው “ምጽዋት ስታደርግ፥ ግብዞች በሰው ዘንድ ሊከበሩ በምኩራብ በመንገድም እንደሚያደርጉ በፊትህ መለከት አታስነፋ፤
… ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ለሰው ይታዩ ዘንድ በምኩራብና በመንገድ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።” እያለም እንድሚነቅፋቸውና ሁሉንም እኛና ስውሩን የሚያይና የሚያውቅ ሰማያዊ ብቻ የምናውቀው ምሥጢር መሆን እንዳለበት ሰማያዊ አባታችን ካየና ካወቀ በቂ መሆኑን ገልጠዋል፣
“ነገር ግን ግብዙ ተመልከት ይህን ያህል ገንዘብ ለቤተ ክርስትያን ሰጠሁ በማለት የገንዘብ ቸኩን ያሳያል በሌላ በኩል ደግሞ ቤተ ክርስትያንን ይቀማል፣ ይህንን የሚያደርግበት ምክንያትም ግብዝ በመሆኑ ለመታየት ብቻ ስለሚፈልግ ነው፣ ጌታ በወንጌሉ ‘ስትጦሙም፥ እባካችሁ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ለሰዎች እንደ ጦመኛ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና፤ አንተ ግን ደስተኛ ሆነህ ጹም ተጋድሎና ንስሓ ስታደርግም በደስታ አድገው፣ በዚህም የሚያውቀው የለም’ ይላል፣ ሲሉ ከግብዝነት መራቅ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፣
በግብዝነት የሚኖሩ ክርስትያኖች እንደ ጣዎስ የሚባለው ወፍ ከፍ ከፍ ብለው እንዲታዩ ለከንቱነት ነው የሚኖሩት፣ እኔ እኮ ክርስትያን ነኛ እኔ የአባ እከሌ ወይም የአቡነ እከሌ ወይም የሲስተር እከሌ ዘመድ ነኝ ቤተሰቤ የክርስትያን ቤተሰብ ነው ብለው ይናገራሉ ነገር ግን ሕይወትህ ከጌታ እንዴት ናት ትጸልያለህ ወይ እንዴትስ ትጸልያለህ የምሕረት ሥራዎችህስ እንዴት ታከናውናለህ ሕመምተኞችን ትጐበኛለህ ወይ ተብለው ቢጠየቁ ግን እውነቱ ሌላ ይሆናል፣ ለዚህም ነው ጌታ ኢየሱስ ቤታችን በአለት ላይ እንጂ በአሸዋ መሥራት እንደሌለብን የሚያስጠነቅቀን፣ በአሸዋ ላይ የተሠራ ቤት መሠረት ስለሌለው ይወድቃል፣ መሠረት የሌለው ክርስትናም ፈተና በሚመጣበት ጊዜ ይንሸራተታል ይወድቃልም፣
“ስንት ክርስትያኖች በግብዝነት ይኖራሉ፣ የእነዚህ ክርስትያኖች ሕይወት የሳሙና አረፋን ይመስላል፣ የሳሙና አረፋ ስታዩት መልካም ነው ብዙ ኅብረቀለማት ይታይበታል ግን ከአንድ ሰከንድ በኋላ የለም፣ ይህ ብቻ አይደለም አንዳንድ የመቃብር ድንጋዮችን ስንመለከት ስንት ከንቱነት እንላለን ምክንያቱም የእግዚአብሔር አገልጋይ ር.ሊ.ጳ ጳውሎስ ስድስተኛ እንዳሉት እውነቱ ራቁታችን ወደመሬት መመለሳችን ስለሆነ፣ ስለዚህ ወደ ኅልናችን መለስ ብለን እኔስ በግብዝነት እመላለሳለሁ እዋሻለሁ ወይስ በእውነት እኖራለሁ፣ እውነት መልካም ሥራን እሠራለሁ ወይ እግዚአብሔርን እሻለሁ ወይ እጸልያለሁ ወይ ብለን እናስተንትን፣ ከንቱነት ውሸት ነው ያልሆነውን ለመሆን ስንጥር ገዛ ራሳችንን እናታልላለን፣ ይህንን ለመጀመርያ እንዳላውቅነው ልናስመስል እንችላለን ውሎ አድሮ ግን እውነቱ መገለጥ ስለማይቀረው መጋለጥ ነው፣ ሲሉ ስለከንተነት ከገለጡ በኋላ ወደ ቃለ ወንጌሉ መለስ በማለት ሄሮዱስ መጥምቁን ዮሓንስ ከገደለ በኋላ ስለኢየሱስ ዜና በሰማ ጊዜ አረ ማን ይሆን ብሎ ሲረበሽ ሰዎቹ አንዱ ከነቢያት ነው ኤልያስ ተመለሰ ዮሓንስ ከሙታን ተነሳ በማለት ስለኢየሱስ ተአምራቶች በሰማ ጊዜ ሊያየውና ሊሰማው ጉጕት አደረው፣ ይህ ጉጕት ግን ውሳጣዊ ሰላም የማጣትና የከንቱነት ጉጕት ነው፣ ይህ ዓይነት ሕይወት ልክ ፊታቸውን በቅባትና በተለያዩ ቀመማት በማቆንጀት ወደ ውጭ እንደሚወጡ ግን ዝናም እንዳይዘንም የሚፈሩ ዓይነት ሰዎች ነው ምክንያቱም ዝናም የዘነመ እንደሆነ ያ ተኳኵለውትና ተቀባብተውት የነበሩት ይረግፋልና እውነተኛ ገጽታቸው ስለሚገለጥ ነው፣ ከንቱነት ሰላም ሊሰጠን አይችልም፣ ሰላም የሚሰጠን እውነት ብቻ ነው፣ እውነትም ኢየሱስ ስለሆነ ሕይወታችን ለመመሥረት የምንችልበት እውነተኛ አለት ኢየሱስ ብቻ ነው፣ ስለከንቱነት ስናስብ ዲያብሎስ ለኢየሱስ ያቀረበለትን ፈተና እንመልከት ና ተከተለኝ ወደ ቤተ መቅደሱ እንውጣ አንተ ከዛው ተወርወር በዚህም ዝነኛ ትሆናለህ ብሎ እንደፈተነው እናውቃለን፣ እንደ ኢየሱስ ጠንቃቃዎችና በቃለ እግዚአብሔር የተካንን ያልሆንን እንደሆነ ከንቱነት እጅግ አደገኛ መንፈሳዊ ሕመም መሆኑን ለማወቅ ያዳግተናል፣
“የቀድመው ግብጻውያን አባቶቻችን በምድረበዳ መንኵሰው ሲኖሩ ከንቱነት መላው የሕይወት ዘመናችን መዋጋት ያለብን ፈተና ነው ምክንያቱም ሁሉ ያለችንን እውነት ሊነጥቀን በየዕለቱ ይመላለሳልና ብለው ያስተምሩ ነበር፣ ይህንን ለማስረዳት ደግሞ ከንቱነትን በሽንኵርት ምሳሌ ያቀርቡታል፣ ከንቱነትን ለማሸነፍ ከፈለግክ በየዕለቱ እየቀልጥ ሂድ በመጨረሻም ባዶ ትቀራለህ፣ እንዲህ በማድረግም ልታሸንፈው ይቻልል ብለው ያስተምሩ ነበር፣ ስለዚህ ጌታን ግብዞች እንዳንሆን ጸጋውን እንዲሰጠን በወንጌሉ እውነትም እንድንመራና እውነተኞች እንድንሆን እንዲረዳን እንለምነው ሲሉ ስብከታቸውን ደምድመዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.