2014-09-24 16:13:40

የብፁዕ ካርዲናል ሙለርና የብፁዕ አቡነ ፈላይ አንድነት ላይ ያነጠጠረ የጋራ ውይይት


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. መስከረም 23 ቀን 2014 ዓ.ም. በቅድስት መንበር ግዛት ክልል በሚገኘው የአንቀጸ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማሕበር ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጉባኤ በዚሁ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ገራርድ ሚዩለር በዋና ጸሓፊያቸው ብፁዕ አቡነ ልዊስ ላዳሪኣ እንዲሁት በታካይ ዋና ጸሓፊያቸው ብፁዕ አቡነ ጉይዶ ፖዞ ተሸኝተው ከፒዮስ አስረኛ ክህነታዊ ወድማማችነት ማኅበረብ ጠቅላይ አለቃ ብፁዕ አቡነ በርናርድ ፈለይ በረዳቶቻቸው ክብሩ ካህን ኒኮላስ ፍሉገርና በክቡር ካህን አላይን ማርክ ነለይ የተሸኝተው መካከል ወደ ምልኡ ውህደት በጋራ ለመድረስ በሚል መሪ ሃሳብ መሠረት የሦስት ሰዓት የጋራ ውይይት መካሄዱ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
የተካሄደው የጋራው ውይይት የወንድማማችነት መንፈስ የተካነው ልባዊ መቀራረብ የታየበት እንደነበር የአንቀጸ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ያስተላለፈው መግለጫ የጠቀሰው የቅድስት መንበር መግለጫ በማያያዝ በኵላዊት ቤተ ክርስቲያንና በፒዮስ አሥረኛ ክህነታዊ ወንድማማችነት ማኅበረሰብ መካከል የአንቀጸ እምነታዊና ሕገ ቀኖናዊ ልዩነት ያለ ቢሆንም ቅሉ በአሁኑ ወቅት ይኸንን ርእሰ ጉዳይ በማድረግ የሚካሄዱት የተለያዩ የጋራ ውይይቶች በሁለቱ ማኅበረሰብ እየተረጋገጠ ያለው መቀራረብ የሚመሰክርና ሙሉ ውህደት እንዲረጋገጥ በሁለቱ ተጋባእያን መካከል የተንጸባረቀ መንፈስ እንደነበር አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.