2014-09-24 19:15:54

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ


RealAudioMP3 ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ!
በዛሬው ዕለት ባለፈው ዕለተ እሁድ በአልባንያ ስላደረግሁት ሓዋርያዊ ጉዞ ለመናገር እወዳለሁ፣ እንዲህ ማድረጌ ደግሞ ይህንን ጕብኝት የተሳካ እንዲሆን የረዳኝ፤ እንዲሁም በአካል ተጨባጭ በሆነ መንገድ ለዚሁ ሕዝብ የቤተ ክርስትያንና የእኔን ቅርበት ለመግለጽ ያበቃኝ እግዚአብሔርን ለማመስገን ነው፣ በሃገሪቱ በታላቅ ትጋት እያገለገሉ ላሉት ለአልባንያ ጳጳሳት ካህናትና ውሉደ ክህነት ወንድማዊ ምስጋየን እንደገና ለማቅረብ እወዳለሁ፣ እንዲሁም በታላቅ ክብር ለተቀበሉኝ እና ጉብኝቱ እውን እንዲሆን ለተባበሩት የአልባንያ መንግሥታዊ ባለሥልጣኖችንም ልባዊ ምስጋናየን አቀርባለሁ፣
ይህ ጕብኝት በአረመናዊና ኢሰብአዊ አገዛዝ ለረዥም ጊዜ የተጨቆነ አገር ነገር አሁን ሁሉ አልፎ በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል በሰላም የሚኖር አገር ለመጐበኘት ከነበረኝ ጉጕትና ፍላጎት የተወለደ ነው፣ ይህንን አገር ለማበረታትና ለጋራ በጎ ነገር የጀመሩትን ጉዞ እንዲቀጥሉና ያላቸውን መልካም ነገር ጠለቅ ባለ መንገድ እንዲያጠኑና እንዲቀሙበት መርዳት አስፈላጊ ሆኖ ታየኝ፣ የዚህ ጉዞ አንኳር የነበረው ከተለያዩ የሃማኖት ሰዎች ጋር መገናኘትና ያ በመካከላቸው ያለው የመተባበርና የመረዳዳት መንፈስ በቃል ከመስበክና መልካም ምኞት ከመግለጥ አልፎ በተጨባጭ እውን ሊሆን እንደሚችል የሚያሳይ ነው፣ እውነትም በተግባር ይኖሩታል፣ ገንቢ የሆነ ቍምነገረኛ ውይይት ከተዛማጅ አስተያየት ርቆ አንዱ የሌላውን ማንነት በማክበር ብዙ ፍሬ እያፈራ ነው፣ የሃይማኖቶች የተለያዩ አስተያየቶችን አንድ የሚያደርገው የሕይወት ጉዞ እና ማንንም ሳታባርርና ንቀትን አርቆ እርስ በእርስ በመከባበር አንዱ ለሌላው በጎ ነገር ለማድረግ መልካም ፍላጎት በማዘውተር ነው፣
ከካህናት እና ከውሉደ ክህነት እንዲሁም ከዘርአ ክህነት ተማሪዎችና ከመንፈሳውያን እንቅስቃሴዎች ጋር ያደረግኩት ግኑኝነት ያለፈውን ታሪክ በማስታወስ በተለይ ደግሞ የብዙ የእምነት ሰማዕታት ታሪክ በማስታወስ ጥልቅ ስሜት ውስጥ ከተተን፣ የስደቱ ስቃይን በአካል የተሳተፉ አንዳንድ ሽማግሌዎች በመካከላችን ስለነበሩ ክርስቶስን እስከ መጨረሻ በመከተላቸው የጀግንነት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፣ ለማንኛውም ሰማዕት እንደሚያጋጥመው እነኚህን ሰማዕታት ታላቅ ጽናት የሰጣቸው ከክርስቶስ ጋር የነበራቸው ጥልቅ የፍቅር ግኑንነት ነበር፣ ይህ ግኑኝነት እስከ ሰማዕትነት የሚያደርሱ አሰቃቂ ስቃዮችን በተእግሥት ለመቀበል ያስችላል፣ እንደ ባለፈው ዛሬም የቤተ ክርስትያን ኃይል ምንም እንኳ አስፈላጊ ቢሆኑም ከአቋቋምዋና ከመዋቅሮችዋ ሳይሆን ከክርስቶስ ፍቅር ነው፣ ይህ ከክርስቶስ ፍቅር የሚገኘው ኃይል በፈተና ጊዜ መጠጊያ ይሆነናል እንዲሁም የሓዋርያቱን ተግባር በልባችን በማስተንፈስ ሁሉን ለእግዚአብሔር እንድንሰዋና የእግዚአብሔር ይቅር ባይነትን ለመመስከር ሁሉንን ይቅር በማለት ለሁሉ ሰው መልካም ነገር ለማበርከት ይረዳናል፣
በአልባንያ ዋና ከተማ ቲራና ዋና መንገድ ከአየር ማረፍያ እስከ ቤተ መንግሥት በተጓዝኩበት ጊዜ በአምባገነኑ የኮሙኒስት ዘመን የተገደሉ የአርባ ካህናት ስ ዕሎችን አንድ ባንድ ተመልከትኩ፣ የብፅዕናቸው ጥናት እየተካሄደ ነው፣ እነኚህ ሰማዕታት በአገሪቱ ከተገደሉ ከተሰቃዩ ከታሰሩና ከአገር ከተባረሩ ብዙ የእስልምናና የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ጋር ይደመራሉ፣ የዚህ ሁሉ ችግር ምክንያት ደግሞ በእግዚአብሔር በማመናቸው ብቻ ነበር፣ እውነትም የጨለማ ዓመታት ነበሩ፣ ያኔ የሃይማኖት ነጻነትና በእግዚአብሔር ማመን በጥብቅ የተከለከለ ነበረ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ አብያተ ክርስትያናትና መስጊዶች ተደምስሰዋል፣ የቀሩም ለመጋዝዘን እና ለሲነማ አገልግሎት እንዲውሉ በማድረግ የኮሙኒዝም ር እዮተ ዓለም ያስፋፉ ነበር፣ የሃይማኖት መጻሕፍቶች ተቃጠሉ፣ ለወላጆች ለልጆቻቸው የአያቶቻቸው የሃይማኖት ስሞች እንዳይሰይምዋቸው ተከልክለው ነበር፣ ይህንን ድራማዊ ታሪክ እንደገና ማስታወስ ለአግሪትዋ ሕዝብ መጻኢ አስፈላጊ ነው፣ በታላቅ ጽናት እምነታቸውን የመሰከሩ ሰማዕታት ዝክርም ለአልባንያ ውሳኔዎች አስፈላጊ ነው፣ ደማቸው ለከንቱ አልፈሰሰም፤ ነገር ግን የሰላምና የወንድማማችነት አጋርነትን አፍርተዋል፣ ስለሆነም ዛሬ አልባንያ የዚሁ ምሳሌ ናት፣ አልባንያ የቤተ ክርስትያን ዳግመ ልደት ምሳሌ ብቻ ሳይሆን በሶስቱ ሃይማኖቶች መካከል በሰላም የመኖር ምሳሌም ናት፣ ስለሆነም ሰማዕታት የተሸነፉ ሳይሆን በዚሁ ጀግንነታዊ ምስክርነታቸው ሁሌ አዳዲስ የተስፋ መንገዶችና አድማሶች እየከፈቱ ሕዝቡን የሚያጽናና እግዚአብሔር ሁሉ ቻይነት በማንጸባረቅ ድል የነሱ ናቸው፣
በክርስቶስ እምነት እና ባለፈው ታሪካቸው የተመሠረተውን ይህንን የተስፋ መልእክት በየጐዳናዎቹ ደስ ብሎዋቸው ላየሁዋቸው ለመላው የአልባንያ ሕዝብ አስተላለፍኩ፣ ሁሌ ከሙታን ተለይቶ ከተነሣው ክርስቶስ አዲስ ኃይል እንዲያገኙና ለማኅበረሰቡ እርሾ በመሆን አገልግሎት በሚሰጥዋቸው ምግባረ ሠናይ ትምህርት በርትተው እንዲሠሩ ተማጠንኩ፣
በዚሁ ጉዞ በስቃይ ያልተበገረ ይህንን ብርታትና ኃይል ያገነባ ሕዝብ እንድጐበኝ በዚሁ ጉዞ ለረዳኝ ጌታን እንደገና አመሰግናለሁ፣ ለአልባንያውያን ወንድሞችና እኅቶችም መልካም ነገር ለማድረግና ያሁንዋንዋና መጻኢዋን ኤውሮጳ እንዲገነቡ ብርታት እንዲኖራቸው አደራ እላለሁ፣ በዚሁ የጉብኝቴ ፍሬ ሰማዕት የሆነው የዚሁ ሕዝብ ጉዞ እንድትመራቸው የመልካም ምክር እናት ለሆነችው የእስኩታሪ መካነ ንግደት ለእመቤታችን ድንግል ማርያም አማጥናለሁ፣ ያለፈው የፈተና ተመኵሮ ለወንድሞች ክፍት የመሆን ዝንባሌ በተለይ ደግሞ ለደካሞች በምግባረ ሰናይ ለመርዳት የሚያስችል ይሁን፣ በዚሁ አደባባይ የምንገኝ ሁላችን ለዚሁ ብርቱና ታታሪ የሆነና በሰላምም አንድነትን ለሚፈልግ የአልባንያ ሕዝብ ሰላምታ እናቅርብላቸው፣ ሲሉ ትምህርታቸውን ደምድመዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.