2014-09-24 15:55:42

ዓለም አቀፍ የስደተኞችና ተፈናቃዮች ቀን


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም. ታስቦ ለሚውለው ዓለም አቀፍ የስደተኞችና ተፈናቃዮች ቀን ምክንያት ተቻችሎ መኖር ለብቻው በቂ አይደለም ስለዚህ ዓለማዊ መስተንግዶ የተካነ መንፈስ አስፈላጊ መሆኑ ያበከበረ መልእክት ከወዲሁ ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ይኽ ትላትና ቤተ ክርስትያን አለ ድንበር፣ የሁሉም እናት” በሚል መርሕ ቃል ሥር ለንባብ የበቃው መልእክት ቤተ ክርስቲያን ሁሉንም በተለይ ደግሞ ከባዱ የሕይወት ሁነትና የተለያዩ ሕይወትን ለአደጋ ከሚያጋልጠው ሁኔታ ሸሽተው ለሚሰደዱትና ለሚፈናቀሉት ለመቀበልና ለማስተናገድ እጆችዋን የምትዘረጋ መሆንዋ የሚያብራራ መልእክት ቤተ ክርስቲያን የማስተናገድና የትብብር ይኽም ማንም እርባና የሌለው እንደ ውዳቂ የማይታይበት ሰብአዊ ባህል በዓለም እንዲስፋፋ አቢይ ጥረት በምድረግ ይኸንን ባህል አጥብቃ እንደምትከላከል ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት መልእክት በማሳሰብ በዓለም የሚታየው ስደትና መፈናቀል ዓለማዊ ገጽታ ያለው በመሆኑም ዓለማዊነት ትሥሥር የተካነው መፍትሔ እንደሚያሻውና በዓለም አቀፍ ደረጃም የወንጀል ቡድኖች ሰዎችን በሕገ ወጥ ተግባር ከቦታ ቦታ ለተለያዩ ክብር ሰራዥ ለሆነው አዲስ ባርነት ለሚገለጠው ኢሰብአዊ ተግባር ለመደረግ ለሚያፈጽሙት ጥረት ዓለማዊ ትሥሥር ሂደት የተካነው ግብረ ሠናይና ትብብር በማስፋፋት በመቃወም የስደተኛውና የተፈናቃዮ ሁኔታ የመመልከቱ ሂደት ሰብአዊነት ለበስ ማድረግ ወሳኝ መሆኑ እንዳብራሩ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የወንጀል ቡድኖች ለሚያረማምዱት የአዲስ ባርህነት ባህል፣ የሰው ልጅ ሰብአዊ ክብርና ሁሉም የሰው ልጅ ማእከል ያደረገ ውጤታማና ትክክለኛ ግቡን የሚያስጨብጥ ዓለም አቀፍ ድራዊ ትብብር የተካነው ትግል አስፈላጊ መሆኑ የጠቀሱት ቅዱስ አባታችን የሁሉም አገሮች መንግሥታትና ዓለም አቀፍ የተለያዩ ማኅበራት የሰው ልጅ ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ እርሱም ጸዓትን ለማስተዳደርና ሥርዓት ባለው መንገድ እንዲመራ ለማድድረግ ተጨባጭና ስኬታማ ትብብር እንዲኖርና ሁሉም የሰው ልጅ ቤቱናን ንብረቱን የተወለደበት አገሩን ጥሎ ለመሰደድ የሚዳርጉት ሕዝቦችን ጦርነት እርሃብና ሌሎች ምክንያቶችን ጭርሶ ለማጥፋት የሚያግዘው ሁኔታ ለመፍጠር ሁሉም ኃይሉን በማጠናከር በማስተባበር ይረባረብ ዘንድ አደራ እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
በርግጥ ስደተኛ በሚገባበት አገር ከሚኖረው ከባለ አገሩ ዜጋ የተለየ በመሆኑ ችግርና መከራ አድልዎ ገፋፍቶት የተሰደደ ሆኖ እያለ ይኸንን ግምት ሳይሰጥበት መጠራጠርና እንደ ጠላት የማየት ሁኔታ ሊቀሰቅስ ይችላል ይሆናል፣ የዚህ ዓይነቱ መንፈስ በቤተ ክርስቲያን ጭምር ሊኖር እንደሚችልም ገልጠው፣ ነገር ግን የሚታየው መጠራጠርና ቅድመ ፍርድ ስደተኛው ማክበርና ማስተናገድ ከሚለው የመጽሓፍ ቅዱሳዊ ትእዛዝ ጋር የሚጻረር ነው። ከድኻው ከሚሰቃየው የአመጽ ሰለባ ከሚሆኑት ንጹሓን ከሚበዘበዘው ሰው ጋር ገዛ እራሱን ያመሳሰለው ኢየሱስ እኛም የሰው ልጅ ስቃይና መከራ አብሮ በመካፈል የፍቅር ትእዛዝ በቃልና በሕይወት እድንኖር ዘንድ ይጠይቀናል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።
“የእምነት የተስፋና የፍቅር ብርታት በሰዎች መካከል ያለውን መራራቅ ቀስ በቀስ እንዲጠፋ ለማድረግ የሚያበቃ ነው” የሚለውን ሃሳብ በመልእክታቸው ያበከሩት ቅዱስ አባታችን በስደተኛው በተፈናቃዩ ሕይወት አማካኝነት ኢየሱስ ገዛ እራሱን ዕለት በዕለት በመግለጥ ድሎትና ምቾት ወደ ጎና በማድረግ ከማባከን ርቀን በመቆጠብ ከሌለው ጋር ተካፍሎ ለመኖር ተግባር ይጠራናል” ብለው “በአሁኑ ወቅት በዓለም የሚታየው ኅብረ-ባህልና ኅብረ-ሃይማኖት በቤተ ክርስቲያን የምታከናውነው የትብብር፣ የሱታፌና ወንጌላዊ ልኡክነት በአዲስ መንፈስ ለሚያነቃቃ ኅዳሴ የሚያበረታታ ነው። ስለዚህ መቻቻል ተቻችሎ መኖር ብቻ በቂ አይሆንም ቤተ ክርስቲያን አርቃ ማዶ በመመልከትና በመኖር ከመከላከልና ከፍርሃት ጠባይ ተቆጥባ ከሌላው ጋር ለመገናኘት የሚያበቃ የግኑኝነት ባህል የሚያስተጋባ ጠባይ ትኑር” በሚል ሃሳብ መልእክቱን እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።







All the contents on this site are copyrighted ©.