2014-09-19 15:59:58

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ሓጢአተኞች መሆናችን የማወቁ ብርታት ለኢየሱስ ርህራሄ ክፍት ያደርጋል


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት ማለዳ እ.ኤ.አ. መስከረም 18 ቀን 2014 ዓ.ም. ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ በላቲን ሥርዓት መሠረት ከሉቃስ ወንጌል ምዕ. 7፣ 36-50 የተነበበውን ጠቅሰው የኢየሱስ እግር በእንባዋ በጸጉርዋ በማበስም የሳመች ሓጢኣተኛ ሴት በተመለከ ያለውን ታሪክ ማእከል በማድረግ ኢየሱስ አንድ ፈሪሳዊ በባህል የላቀ የሕግ አዋቂ ጋር ይወያያል፣ ፈሪሳዊው ከኢየሱስ የእምነት ሕጎች ለመማር ወደ ቤት እንዲገባ ያደርጋል፣ ሆኖም ግን በሌሎች ላይ ለመፍረድ ፈጣን የዚያች ትሁት ሴት ተግባር ጨርሶ ለመረዳት የተሳነው፦ “አዎ ያ ፈሪሳዊው የዚያች ትሁት ሴት ተራ ተግባር ሁሉ ጨርሶ ለመረዳት ያልቻለ፣ ምናልባት ይኽ ሰው አንድ ሕፃን ዳብሶ የማባበሉ አንዲት ያዘነች ሴት የማጽናናቱ ተራው ምልክት ጨርሶ የረሳ ይመስላል፣ ነገር ግን ፈረሲሳውያንን የሚያማክር የሕግ አዋቂ ሰው ነው የነበረው ያንን ገና ስንወለድ ያጣጣምነው ተራው የሕይወት ምልክት የዘነጋ ነበር” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ኢየሱስ ያንን ፈሪሳዊው የምነግርህ ነገር አለኝ ሲል ትህትናውን ርህሩህነቱን ትዕግስቱን ፍቅሩን ሁሉን ለማዳን ያለው ፍጽም ፍላጎት የሚያበክር ቃል ያሰማዋል፣ ያች ኃጢአተኛ መሆንዋ በጥልቀት የተረዳች ሴት ያሳየቸው ተራው ምልክት ከፈረሲያዊው ያላየው ብቻ ሳይሆን ያ ፈሪሳዊው የዚያች ሴት ሁኔታ ተመልክቶ በኢየሱስ ላይ አይ ያ ሰው ነቢይ ቢሆን ኖሮ ይህች የምትዳስሰው ማን እንደሆነችና ምን ዓይነት ኃጢአተኛ እንደሆነች ባወቀ ነበር ሲሉ በልቡ ያስባል፣ ኢየሱስ ግን ለዚያች ሴት ‘ኃጢአትሽ ይቅር ተብሎልሻል፣ እምነትሽ አድኖሻልና በሰላም ሂጂ” በማለት ያሰናብታታትል እንጂ እንደ ፈሪሳዊው አልፈረደባትም። መዳንና እምነት የማይነጣጠሉ መሆናቸው የሚያስገነዝብ ቃል ነው፣ እዎ እምነትሽ አድኖሻል ያስባለውም በኃጢአትዋ ተጸጽታ በመናዘዝ በማንባቷ ነው። በዚያች ሴት ዙሪያ የነበረው ሕዝብ ከኃጢአት የራቀ ሆኖ የሚሰማውና በዚያ ሕዝብ ባህል ፊት ኃጢአተኞች ተብለው የሚነገርላቸው ቀራጮች አመንዝራዎች ናቸው። ኢየሱስ ግን እምነትሽ እምነትህ አድኖኻል ብሎ ነው የገለጣቸው፣ በልቡ ኃጢአተኛነቱ የሚታመን የሚናዘዝ የሚጸጸት ይድናል፣ መዳኑም አለው፣ መዳን ወደ እኛ የሚገባው በልባችንን በእውነት ኃጢአተኞች መሆናችን ስንታመን ነው” እንዳሉ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ ከኢየሱስ ጋር ለመገናኘት ምቹው ሥፍራ ኃጢአትን መታመን መሆኑና ቅዱስ ጳውሎስ እኔ የምመካው በሁለት ነገር ብቻ ነው፦ እርሱም በኃጢአቱና ከሞት በተነሳው ክርስቶስ መዳኔ ነው የሚለውን ቅዱስነታቸው አስታውሰው “ለዚህም ነው ኃጢአተኞች መሆናችንና ምስኪንነታችንን ስናውቅ ልባችን በኢየሱስ ለሚዳብሰው ለምህረቱ ለይቅር ባይነቱ ጸጋ ክፍት እናደርጋለን፣ እርሱም እምነትህ አድኖሃልና በሰላም ሂድ ይለናል፣ ልቡን ለኢየሱስ ክፍት የማድረግ ብርታት ያለው ብቻ ነው የሚድነው” ብለው ኢየሱስ ኃጢአተኛው ቀራጩ አመንዝራይቱ በእግዚአብሔር መንግሥት ይቀድሟችዋል ምክንያቱም ኃጢአታቸውን በመናዘዝ ልባቸውን ለማዳን ደሙን ላፈሰሰው ለእርሱ ክፍት በማድረግ ከኢየሱስ ጋር በመገናኘታቸውም መሆኑ ገልጠው ያስደመጡት ጥልቅ አስተንትኖ እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.