2014-09-12 16:59:01

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ጠላትህን ማፍቀር ያስፈራናል፣ ነገር ግን ኢየሱስ የሚያቀርብልን ጥያቄ ነው


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሁሌ ማለዳ በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት የሚያቀርቡት መሥዋዕተ ቅዳሴ በመቀጠል እ.ኤ.አ. መስከረም 11 ቀን 2014 ዓ.ም. ምህረትን የሚያውቅና የሚምር ልብ ብቻ ነው ኢየሱስን መከተል የሚችለው የሚል ጥልቅ ሃሳብ ዙሪያ በላቲን ሥርዓት የዕለቱ ምንባብ ተንተርሰው ሥልጣናዊ አስተንትኖ መለገሳቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ክርስቲያናዊ ሕይወት በገዛ እራስ የሚጣቀስ ወይንም ገዛ እራሱ ዋቢ የሚያደርግ ሕይወት ሳይሆን ካለ ምንም ቁጠባና ራስ ወዳድነት ሙሉ በሙሉ እስከ መጨረሻ ጸጋ ነው። ስለዚህ እንዲህ ሲኮን ብቻ ነው ጌታ እንደሚጠይቀውም ጠላቶትን ለማፍቀር የሚቻለው። ጠላቶታችሁን አፍቅሩ የሚለው የዕለቱ የሉቃስ ወንጌል ምንባብ መሠረት በማድረግ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በዚህ ወንጌል አማካኝነት ጌታችን ያ ገደብና ድንበር አልቦ የሆነው የፍቅር ጉዞ በቃሉና በሕይወቱ ሲያመለክት፣ ክፉ ለሚያደርጉን ሁሉ እንድንጸልይ አሳስቦናል፣ አፍቅር መልካም አድርግ ባርክ ጸልይ ማንም አታግል፣ የተሰኙት በዚህ ምንባበ ወንጌል ጌታ የተጠቀመባቸውን ቃላቶችን አበክረው፣ ገዛ እርስ አሳልፎ መስጠት፣ ስለ እኛ መጥፎ ለሚመኙት ክፉ ለሚያደርጉን ሁሉ ለጠላቶቻችን ሁሉ ስለ እነርሱ ገዛ እራስ አሳልፎ መስጠት የሚለው ጥሪ ወንጌል ያመጣው አዲስትነት ሲሆን፣ መፈቀር የይገባኛል ጥያቄ አይደለም ማለትም ለሚያፈቅሩህ ማፍቀር ቀላል ነው። ኃጢአተኞች የሚያደርጉት ነውና። መልካም አድርግ ምንም ነገር ካለ መጠባበቅ መልካም አድርግ፣ አለ ምንም የግብረ መልስ ፍላጎት ማፍቀር፣፦ አይ አባቴ እኔ’ማ ይኽ ለማድረግ አይቻለኝም? አይቻለኝም ብሎ መናገሩ የገዛ እራስ ጉዳይ ነው። ወደድንም ጠላንም የክርስትናው ጉዞ ኢየሱስ ያመለከተው መንገድ ነው። በኢየሱስ መንገድ መጓዝ የኢየሱስ መንገድም ምህረት ነው። በሰማይ እንዳለው አባታችሁ መሃሪያን ሁኑ፣ በመሃሪ ልብ ብቻ ነው ኢየሱስ የሚመክረውን ለመከወን የሚችለው፣ የክርስትናው ሕይወት ርእሰ አጣቃሽ አይደለም፣ ከግዛ እርስ መውጣት ይኽም ስለ ሌሎች ገዛ እራስ ማሳለፍ የሚል ነው። ጸጋ ነው፣ ፍቅር ነው። ፍቅር በገዛ እራሱ ላይ አይዘጋም ራስ ወዳድ ለእኔ ባይ አይደለም” ያሉት ቅዱስ አባታችን ኢየሱስ መሃሪዎች የማይፈርዱ ሁኑ ብሎን እያለ እኛ ግን ብዙውን ጊዜ ፈራጆችና ዳኞች ሆነን እንገኛለን፣ ሁሉንም እንፈርዳለን፣ ነገር ግን ጌታ የሚለን አትፍረድ እንዳይፈረድብህ፣ አትኰንን እንዳትኰነን ነው፣ በመጨረሻ እኛ የበደሉንን ይቅር ስልን በደላችንን ሁሉ ይቅር ይባልልናል፣ ይቅር ካላልኩኝ ካልማርኩኝ እንዴት ደፍሬ አባትን ማረኝ ይቅር በለኝ ብየ የምለምነው የሚለው ጥልቅ ክርስቲያናዊ ሕይወት ሲያመለክቱ፦ “የክርስትናው ሕይወት እንዲህ ነው። ሆኖም ግን አይ አባ ይኽማ ሞኝነት ነው። አዎ ቅዱስ ጳውሎስ የክርስቶስ መስቀል ከዓለም ጥበብ ጋር ምንም አይነት ግኑኝነት የሌለው ሞኝነት መሆኑ ገልጦልናል። ታዲያ ክርስቲያን መሆን ሞኝ መሆን ማለት ነውን? በሌላው አነጋር አዎ እውነት ነው። ምክንያቱም ኢየሱስ የሚጠይቀን ሁሉ ለማድረግ የዓለም ብልሀተናኛነት እምቢ ማለትን ይጠይቃል፣ ይኽ ዓይነት ሕይወት ምናልባት በዚህ ዓለም ሚዛን ያየነው እንደሆነ ለእኛ የሚበጅ ላይመስለን ይችላል መክሰር ማለት ነው” ርህሩህ ለጋስ አለ ምንም ቁጠባ ገዛ እራስ መስጠት፣ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጥቶ ይኸንን እግብር ላይ አውሏል፣ ማረ እንጂ አልፈረደም ስለ ሌሎች ክፉ አልተናገረም፣ ፈርዶ አያውቅም ምህረትን እንጂ፣ ክርስትና ቀላል አይደለም፣ ክርስቲያን መሆን የሚቻለው በእግዚአብሔር ጸጋ ብቻ እንጂ በገዛ እራስ ኃይል አይኰንም፦ ስለዚህ ጌታ ሆይ መልካም ክርስቲያን እሆን ዘንድ ጸጋህን አድለኝ፣ እኔ ለብቻየ ልሆነው አይቻለኝምና፣ ክርስቲያን መሆን ምን ማለት መሆኑ ለመገዘብ ይቻለኝ ዘንድ ክርስቲያን ለመሆን እንድንችል ጌታ ጸጋውን እንለምነው፣ ለብቻችን የሚቻለ አይደለምና” በማለት ያስደመጡት ሥልጣናዊ አስተንትኖ እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.