2014-09-05 15:53:12

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ኃጢአታችን ከኢየሱስ ጋር የሚያገናኝ ምቹ ሥፍራ ነው


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. መስከረም 4 ቀን 2014 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እንደተለመደው በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት ጧት ባሰርጉት መስዋዕተ ቅዳሴ የክርስትና ሕይወት ኃይል በኃጢአታችንና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መካከል የሚከናወን ግኑኝነት ነው። ይኽ ግኑኝነት ሳይኖር ሲቀር አቢያተ ክርስቲያን ሕይወት የሌላቸው ፈራሽ ግንብና ወና ይሆናሉ፣ ክርስቲያኖችም ለብ ያሉ ይሆናሉ” በሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ ያተኰረ እስተንትኖ መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሰርጆ ቸንቶፋንቲ ገለጡ።
ጴጥሮስና ጳውሎስ ሁለት ነገሮችን ያሳስቡናል፣ እርሱም ስለ ኃጢአትና ስቅለተ ክርስቶስ ነው። ክርስቲያን በሁለት ነገሮች ብቻ ይመካል እርሱም የመጀመሪያ ምንባብ አንደኛይቱ የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ለቆሮንጦስ ስዎች ጥበበኞች ለመሆን ሞኞች መሆን ሲያስተምር፣ የዚህ ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ፊት ሞኝነት ነውና በመሆኑም፦ ልባችንና ዓለምን የሚለውጠው ድህነት የሚሰጠው የእግዚአብሔር ቃል ነው። መለወጥና ድህነት ሰብአዊ ጥበብ የሚያስገኘው አይደለም፣ መለወጥና መዳን ጣፋጭ ቃል አጣጥሞበ መናገር የሚነበነብ የቃል ጉዳይ ወይንም የላቀ ምሁር የሚያስብል ቃል በመጠቀም መናገር ማለት አይደለም፣ ይኽ አይነቱ አነጋገርማ ሞኝነት ነው። የእግዚአብሔር ቃል ኃይል፣ ሰብአዊ ጥበብ አይደለም፣ የእግዚአብሔር ቃል በሰባኪ ልብ አማካኝነት ይተላለፋል፣ ለዚህም ነው የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰብኩ ሞኞች የዋሆች መሆን የሚገባቸው፣ ማለትም በገዛ እራሳቸው ጥበብ በዓለም ጥበብ ላይ ጽናት እንዳይኖራቸው ለማለት ነው” ቅዱስ ጳውሎስ በሊቅነቱ ገዛ እራሱን ከፍ ከፍ አላደረገም በዚያን ጊዜ እጅግ ታዋቂ በነበሩት አስተማሪዎች የታነጸ ሰው ነበር ሆኖም ግን ሊቅ ሆኖ እያለ፦ “የምመካው ኃጢኣተኛ በመሆኔ ነው ያለው። ይኽንን የጳውሎስ አባባል እንቅፋት ይመስላል፣ በሌላው መልእክቱ ጳውሎስ ይላል እኔ የምመካው በክርስቶስ በመስቀል ነው በመስቀል ላይ በተሰቀለው ክርስቶስ ነው ይላል፣ ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል ኃይል በኃአቴና በሚያድነኝ በደመ ክርስቶስ መካከል የሚፈጸም ግኑኝነት ነው። ይኽ ግኑኝነት ሳይኖር ሲቀር በልብ ውስጥ ኃይል ይጐድላል፣ በሕይወታችን የተከናወነው የዚያ ዓይነቱ ግኑኝነት ስንዘነጋ የዓለም እንሆናለን። ስለ እግዚአብሔር ጉዳይ በዓለም ቃል የምንናገር ሆነው ንቀራለን፣ ይኽ አይጠቅምም ሕይወትም አይሰጥም” ካሉ በኋላ ቅዱስ ጴጥሮስ በወንጌል ስለ ተአምረኛው አሳ የማጥመዱ ተግባር ይናገራል፣ ይኽ ደግሞ ከኢየሱስ ጋር የሚፈጸም ግኑኝነት የሚገልጥ ነው። በኢየሱስና በኃጢኣተኛ መካከል የሚከናወን የግኑኝነት ገጠመኝ ያወሳል፣ ጴጥሮስ የኢየሱስ ኃይል እንዳየ ከገዛ እራሱ ጋር ይገናኛል፣ ጌታ ሆይ ኃጢአተኛ ነኝና ከእኔ ራቅ” በሚል እውነተኛ ግኑንኘት በሚያረጋግጥ ቃል በጌታ እግር ሥር ተደፍቶ ይናገራል፣ “በኃጢአቴና በኢየሱስ ክርስቶስ መካከል በሚከወነው ግኑኝነት ድህነት አለ” ብለው“ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለመገናኘት አመቺው ሥፍራ ኃጢአታችን ነው። አንድ ክርስቲያን ኃጢአተኛ መሆኑ ካልታመነና በደመ ክርስቶስ በመስቀለ ክርስቶስ እንደዳነ የማስተዋሉ ብቃት ሳይኖረው ሲቀር፣ ጐደሎ ክርስቲያን ነው። ለብ ያለ ክርስቲያን ነው። ወና ሆነው የቀሩት አቢያተ ክስቲያንና ቁምስናዎች መዋቅሮች እናስብ እነዚህ ሁሉ ወና ሆነው ስናይ አዎ በርግጥ ክርስቲያኖች የሚገኙበት ሥፍራ ነው፣ ነገር ግን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያልተገናኙ ክርስቲያን ናቸው፣ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የተከወነው ግኑንነት የዘነጉ ክርስቲያኖች የሚኖሩበት ሥፍራ ናቸው። የክርስቲያን ሕይወት ኃይልና የእግዚአብሔር ቃል ኃይል እኔ ኃጢአተኛው ከኢየሱስ ጋር የምገናኝበት ሁነት ነው። ኃይል ግኑኝነቱ ነው። ያ ሁሉን ነገር የሚለውጥ ለሌሎች ድህነትን ለማወጅ ኃይል የሚሰጥህ ከኢየሱስ ጋር መገናኘት ነው” እንዳሉ የገለጡት ልኡክ ጋዜጠኛ ቸንቶፋንቲ አክለው በቅዳሴው ሥነ ሥርዓት ለተሳተፉት ሁሉ ቅዱስ አባታችን ያቀረቡት አስተንትኖ፦ “እኔ ለጌታ ኃጢተኛ ነኝ ብየ ገዛ እራሴን ልገልጥለት ችሎታው አለኝ ወይ? በሓሳብ አይደለም በንሥሐ ሥራ መሆን አለበት። እርሱ በደሙ ከኃጢአቴ እንዳነጻኝ እንዳዳነኝ እምነቱ አለኝ ወይ? በእርሱ እታመናለሁ ወይ? አንድ ክርስቲያን የሚመካበት ነገር ምንድር ነው? እርሱም ኃጢአተኛነቱና መስቀለ ክርስቶስ ነው። እንዳሉ ቸንቶፋንቲ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.