2014-08-29 16:14:51

የቅዱስ አባታችን ሐዋርያዊ ጉብኝት መርሃ ግብር


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. መስከረመ 13 ቀን 2014 ዓ.ም. አንደኛው የዓለም ጦርነት ዝክረ 100ኛው ዓመት ምክንያት በኢጣሊያ ጎሪዚያ ክፍለ ሃገር ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያካሂዱ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 28 ቀን 2014 ዓ.ም. የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ከተሰጠው መግለጫ ለመረዳት ሲቻል፣ ቅዱስነታቸው እ.ኤ.አ. መስከረም 13 ቀን 2014 ዓ.ም. በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከተጠዋቱ ሰባት ሰዓት ተኩል ከቅድስት መንበር በመኪና ሮማ ወደ ሚገኘው ቻምፒኖ ያየር ማረፊያ ተጉዘው ልክ ስምንት ሰዓት ላይ ሮንኪ ደይ ለጆናሪያ ያየር ማረፊያ እንደደረሱ ዘጠኝ ሰዓት ከሩብ ፎሊያኖ ዘ ረዲፑሊያ ወደ ሚገኘው የአውስትሪያ ሃንጋሪ መካነ መቃብር ዘንድ ተገንተው ጸሎት አሳርገው ጉንጉን አበባ አኑረው እንዳበቁም አስር ሰዓት በረዲፑሊያ በሚገኘው በሰማዕታት ሐወልት ፊት በሚገኘው አደባባይ መስዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው፣ በቅዳሴው ፍጻሜ በአንደኛው የዓለም ጦርነት የወደቁት የሞት አደጋ ያጋጠማቸውን የዚያኑ አሰቃቂው ጦርነት ሰለማ የሆኑትን በመዘከር ስለ እነርሱ ልዩ ጸሎት ደግመው እንዳበቁ ቅዱስነታቸው ለመከላከያ ኃይል አባላት መደበኛ የሐዋርያዊ አገልግሎት ጳጳስና መንፈሳዊ ረዳቶች በቅዳሴው ሥነ ሥርዓት ለተሳተፉት ብፁዓን ጳጳሳት ሁሉ በዚህ አንደኛው የዓለም ጦርነት ዝክረ 100ኛው ዓመት ምክንያት በሰበካዎቻቸው በይፋ በሚጀመርበት የመንፈሳዊ መርሃ ግብር ወቅት የሚያበሩት የኩራዝ መብራት ከሰጡ በኋላ ልክ እኩለ ቀን ወደ ሮማ የመልስ በረራ አድርገው ልክ ለአንድ ሰዓት 10 ጉዳይ ሮማ ቻምፒኖ የአየር ማረፊያ ደርሰው ወደ ሐዋርያዊ መንበራቸው እንደሚመለሱ የቅድስት መንበር የዜና ኅትመት ክፍል ከሰጠው መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.