2014-08-21 18:31:28

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ፣


RealAudioMP3 ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን ኣደራችሁ!
ባለፉት ቀናት በኮርያ ሓዋርያዊ ጉዞ ኣደረግሁ፤ ዛሬ ደግሞ ከእናንተ ጋር ኣብሬ ለዚሁ ታላቅ ስጦታ ጌታን ኣመሰግናለሁ፣ በሰማዕታት ምስክርነት የተመሠረተችና በኣስፍሖተ ወንጌል ሕያው የሆነች የኤስያ ጥንታውያን ባህሎችና የቅዱስ ወንጌል ዘለዓለማዊ ህዳሴ በሚገናኙባት ኣገር ኣንዲት ወጣትና ታታሪ የሆነች ቤተ ክርስትያን ለመጎበኘት ችያለሁ፣
እጅግ የተወደዱ የኮርያ ወንድሞቼ ጳጳስትንና የረፓብሊኩ ፕረሲደትን እንዲሁም ለሁሉም ባለሥልጣኖችና ይህ ጉብኝት እንዲሳካ ኣበርክቶ ላደረጉ ሁሉ በድጋሚ ለማመስገን አወዳለሁ፣
የዚሁ ሓዋርያዊ ጉዞ ትርጉም በሶስት ቃላት ሊጨመቅ ይችላል፣ ዝክር ተስፋና ምስክርነት፣
የኮርያ ሪፓብሊክ ባጭር ግዜ ታላቅና ፈጣን ምጣኔ ሃብታዊ ግሥጋሴ ያሳየች ኣገር ናት፣ ነዋሪዎችዋ ትጉና ሥርዓት ያላቸው ሠራተኞች ሆነው በደንብ ሲኖሩ ይህም ከቅድመ ኣያቶቻቸው የወረሱት ነው፣
በዚህ ሁኔታ ቤተ ክርስትያን የታሪካቸው ዝክርና የተስፋ ጠባቂ ናት፣ ኣንዲት መንፈሳዊ ቤተሰብ ሆና ሽማግሌዎቹ ለወጣቱ ትውልድ ከታላቆቻቸው የወረሱት የእምነት ብርሃን ያስተላልፋሉ፣ በዚህም የጥንቱ የምስክርነት ዝክር ላለው ትውልድ ኣዲስ ምስክርነት ሆኖ ለሚመጣው ደግሞ ተስፋ ይሆናል፣ የዚህ ጉዞ ሁለቱ ዋና ፍጻሜዎች በዚህ ኣመለካከት ልናነባቸው እንችላለን፣ ከ30 ዓመታት በፊት በር.ሊ.ጳ ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ቅድስናቸው ለታወጀው ሰማዕታት ዛሬ እኛ ሌሎች 124 የኮርያ ሰማዕታት የብፅዕና ሥርዓታቸውን በማወጅ እንጨምራለን፣ ሁለተኛው ደግሞ በኤስያ 6ኛ ዓለም ኣቀፍ የወጣቶች ቀን ለተሰበሰቡት የመላው ኤስያ ወጣቶች ጋር መገናኘት ነበር፣
ወጣት ሁል ጊዜ የሕይወት ትርጉምን ለማግኘት በኣሰሳ የሚገኝ ሲሆን ሰማዕት ደግሞ የኣንድ ነገር መስካሪ በመሆን ለኣንድ ነገር ሕይወትን መስጠት ትርጉም እንዳለው የሚገልጥ ነው፣ ይህም ሁሌ የእግዚኣብሔር ፍቅር ሆኖ የእግዚኣብሔር ኣብ ምስክር በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ የለበሰ ፍቅር ነው፣ ከወጣቶቹ ጋር በተገናኘሁባቸው ሁለት ወቅቶች ከሙታን ተለይቶ የተነሣ የጌታ መንፈስ ወጣቶቹ ከተለያዩ ኣገሮች ባመጡት ደስታና ተስፋ ልቦቻችን ሞላልን፣ ይህም እጅግ መልካም ነበር፣
የኮርያ ቤተ ክርስትያን ምእመናን በቤተ ክርስትያን የነበራቸውን ዋነኛ ኣስተዋጽኦ ማለትም የእምነት ምንጭና ጠባቂ በመሆንም ይሁን ባካሄዱት ስብከተወንጌል ዝክር ይዛ ትገኛለች፣ በዚያች ምድር የክርስቲያን ማኅበረሰብ በሐዋሪያዊ አገልግሎት ልዑካን አልተቋቋመም ግን እ.ኤ.አቆ. በ1700 ዓ.ም. አጋማሽ አካባቢ የኮርያ ወጣቶች በአንዳንድ የክርስትና ጽሁፎች በጣም በመደነቅና በመሳብ ጠልቀው በማጥናት የራሳቸውን የሕይወት መመሪያ አድርገው ለመኖር መረጡ። ከነሱም ውስጥ አንዱ ወደ ቻይና ዋና ከተማ ፐኪኖ እንዲጠመቅ ሲጋበዝ እሱም በተራው ሌላ ግዋደኞቹን አጠመቀ። ከዛ ግዜ ጀምሮ ይሕ ሕብረት እያደገ ወደ ትልቅ ማህበረሰብ ሲስፋፋ ከመጀመሪያው ግዜ ጀምሮ ለዘመናት ለመቶ አመታት ያህል ብዙ አመጽና ስደት ሲደርስበት እንዲሁም በሺ የሚቆጠሩ ተገድለዋል ተሰውተዋል። ስለዚህ የኮርያ ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተችው በዕምነት በሐዋሪያዊ አገልግሎት ልዑካኖችና በምዕመናን መስዋዕትነት ነው።
የመጀመሪያ የኮርያ ክርስቲያኖች ለመኖር የወሰዱት ምሳሌ ያ በመጀመርያ ዘመን በእየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩ የመጀመርያ ክርስቲያኖች ያዘውትሩት የነበሩትን አንድነትና ኅብረትን በተጨባጭ እተግባር ላይ በማዋል የወንድሟሟችነትን ፍቅር በሕብረተሰቡ ያለውን መከፋፈልን በማሸነፍ ነበር፣ ስለዚህ የዘመናችንን ክርስቲያኖችን ከድሆችና ሕብረተሰቡ ከማይፈልጋቸው ወገኖች እንዲያካፍሉና እንዲለግሱ አበረታታሁኝ፣ በማቴዎስ ወንጌል ምዕ 25 ቁ.40 እንደተጻፈው በእውነት እላችኋለሁ ከእነሂህ ከወንድሞቼ አነስተኛ ለሆነው ለአንዱ እንኳን ብታደርጉት ለኔ እንዳደረጋችሁት ነው ሲል ይመልስላቸዋል፣
ውድ ወንድሞች የኮርያን እምነት ታሪክ ስንመለከት ክርስቶስ ባሕልን እንደማይተውና እንደማይሽር እንዲሁም ለዘመናት እውነትን ለሚፈልጉ የሕዝቡን ጉዞ የክርስቶስን ፍቅር ለነሱና ለሌሎችም በተግባር የሚያሳዩ ናቸው፣ ክርስቶስ መልካምን ነገር አይጥልም መልካሙን ነገር ወደ ፊት በመውሰድ ወደ ሙላትና ፍጽምና ላይ ያደርሳል፣ክርስቶስ የሚዋጋውና የሚያሸንፈው ጠላታችንን ነው፤ ጠላታችን ሃሜትን እየዘራ ሰው ከሰው ሕዝብ ከሕዝብ እያጋጨ ብቸኝነትን እየፈጠረ ሲያባርር የዚህም ምክንያት ገንዘብን ስለሚያመልኩ ነው፣ ገንዘብ በወጣቱ ልብ የሚዘራ መርዝ ነው፣ ይህ ነው ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የተዋጋው፤ ያሸነፈውም በፍቅር መስዋዕትነት ነው፣ እኛም ከእርሱ ጋር በመሆን በፍቅሩ የኖርን እንደሆነ፤ እንደ ሰማዕታት ለመኖር እንችላለን በዚህም የክርስቶስን ድል እንመሰክራለን፣ በዚህ እምነት ነው የጸለይነው አሁንም ለሁሉም የኮርያ ምድር ልጆች እንጸልያለን በጦርነቱ ምክንያት ተከፋፍለው ለሚሰቃዩ በሕብረት የወንድሟሟችነት ጉዞ የአንድነት እንዲሆን። ይህ ጉዞ እመቤታችን ድንግል ማሪያም ፍልሰታ ከሰማይ የተሰጠ ብርሃን ከላይ ከክርስቶስ ግዛት የቤተክርስቲያን እናት የእግዚብሔርን ልጆች ጉዞ በመምራት የደከሙትን በመደገፍ በችግርና በስቃይ የሚገኙትንም በተስፋ ታጽናናለች። በማያቋርጠው የእናት አማላጅነቷ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የኮርያን ሕዝብ ይባርክ ሰላምና በረኸትን ይስጠው በምድር የምትገኘውን ቤተክርስቲያኑንም ይባርክ ሁሉ ግዜ ፍሬን የምታፈራና በደስታ ወንጌልን የምትመሰክር ትሁን፣ እግዚአብሔር ይስጥልኝ፣







All the contents on this site are copyrighted ©.