2014-07-11 16:41:10

የቫቲካን ባንክ አዲስ ፕረዚዳንት ተሰየሙ ፡



የዮር የቫቲካን ባንክ ምክር ቤት ፕረሲደንት ጀርመናዊ ኤርንስት ፎን ፍረይበርግ
ተክተው የተሰየሙት የፈረንሳ ዜጋ ጃን ባፕቲስት ደ ፍራንሱ ሲመቱ በደስታ እንደቀበሉት በቫቲካን ራድዮ ከየ ፈረንሳ ቋንቃ ዝግጅት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ አስታውቀዋል።የቫቲካን ባንክ ምክር ቤት ፕረሲዳንት በመሆን ማገልገል ዓቢይ ሐላፊነት ነው ብዪ` አምናለሁ ይሁን እና የቀድሞ ፕረዚንት ኤርንስት ቮን ፍረይበርግ የጀመሩት ከባድ ሐላፊነት እና ስራ በመቀጠል እስራለሁ ብለዋል ጃን ባፕቲስት ደ ፍራንሱ ።
የቫቲካን ባንክ ሐላፊነት ወስዶ መስራት ትልቅ ትሕትና እና ብልልሃት ይጠይቃል የቅድስት መንበር የምህደራ ተቃማት እና ፋይናን እንዲሁም በዓለም ዙርያ ከሚገኙ የቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርትያን ድርጅቶች እና ሀገረ ስብከቶች ጋር ተባባሮ መስራት ስለሚጠበቅበት ብለዋል አዲሱ የቫቲካን ባንክ ፕረሲዳንት ።ሐላፊነቱ አንድ ተልእኮ መሆኑ እና በመልካም አግባብ ለመወጣት ከፍተኛ ተስፋ እንዳላቸውም አክለው አመልክተዋል።ከአሁን ቀደም የቅድስት መንበር የኤኮኖሚ ምኽር ቤት ባካሄደው የተለያዩ ጉብኤዎች ተሳታፊ ስለ ነበርኩኝ የሙያው ዘታ በመጠኑም ቢሆን የተረዳሁት ነገር አለ እና ይህ ጠቅሜታ ይኖረዋል ብለው ያሉት የቫቲካን ባንክ አዲስ ፕረሲዳንቱ የዮር የባንክ ቫቲካን ዋንኛ ዓላማ ቤተ ክርስትያን በዓለም ዙርያ ለሚታካሄደው ካቶሊካዊ እምነት ስርጭት ማለት ቅዱስ ወንጌል በማዳረስ ረገድ ያላትን ተልእኮ እና ድሆች ለመርዳት ያላትን ሂደት መተባበር ነው ብለዋል። ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ባንኩ ግልጽነት የሞላው እንዲሆን በጠየቁት መሰረትም የባንኩ አስራር የነጣ ከሀገራት አቀፍ የባንክ አስራር ዘይቤ የተስተካከለ ሆኖ አስራሩ ማክበር እንደሆነ እንደሆነም የቫቲካን ባንክ ፕረሲዳን ጃን ፓፕቲስት ደ ፍራንሱ ገልጠዋል።ፕረሲዳንት ፍራንሱ አያይዘው ሎ ዮር ማለት የቫቲካን ባንክ ባንክ ተብሎ ይጠራ እንጂ የፋይናንስ ተቋም መሆኑ መገንዘብ ያሻል ብለዋል።በየቅድስት መንበር ቁጥጥር ስር የሆነው ባንኩ ወይም የፋይናንስ ተቋሙ የቤተ ክርስትያንተቋሞችን የማገልገል ሐላፊነቱ በብቃት እንዲወጣ እንደሚፈልገም አመልክተዋል። የፋይናንስ ተቋሙ አስራር በየካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ግብረ ገብነት ላይ የተመሰረተ መሆኑ መታወቅ እንዳለበት እና ለካቶሊካውያን ድርጅቶች ሀገረ ስብከቶች እና የቅድስት መንበር ባለ ሙያዎች አገልግሎት የሚሰጥ እንደሆነም አብራርተዋል።
ሎ ዮር በግልፅነት ማነስ ወቀሳ ተሰንዝሮበት ባለፈው ወርሀ ሚያዝያ እንዲዘጋ የታሰበበት ግዜ መኖሩ እና ኃላ ግን ስር ነቀል ለውጥ እንዲደረግበት የፈለገበት ምክንያት ምን ይሆን ለሚለው ጥያቄ አዲስ ፕረሲዳንት ጃን ባፕቲስት ደ ፍራንሱ ሲመልሱ ከጥልቅ ጥናት እና መመካከር በኃላ የፋይናስ ተቋሙ ለቅድስት መንበር ተቋማት አስፈላጊ መሆኑ ተገኝተዋል ብለዋል። ለበርካታ ግዜ ሎ ዮር የቫቲካን ባንክ በየፋናንስ እና የኤኮኖሚ በሰሎች ባለ መመራቱ መጐሳቀሉም ፕረሲዳንት ደ ፍራንሱ ሳያስገነዝቡ አላለፉም ።
ይህ በዚህ እንዳለ ሆኖ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በዚሁ በተያነው ወርሀ ሐምለ 26 ቀን በደቡባዊ ጣልያን ካሰርታ ከተማ ላይ የግል ጉብኝት እንደሚያካሄዱ የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ መግለጫ ሰጠዋል። ጥብቅ እና የግል ጉብኝት መሆኑ ያሰመሩበት ቃል አቀባዩ ባለፈው ወርሀ የካቲት አንድየወንጌላዊት ቤተ ክርስትያን ቡድን ቫቲካን በጐበኘበት ግዜ ቅድስነታቸው ካሰርታ እንዲጐበኙ መጠየቁ አብራርተዋል ።








All the contents on this site are copyrighted ©.