2014-05-30 11:31:05

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ፣


ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ! RealAudioMP3
እንደምታውቁት ባለፉት ቀና በቅድስት መሬት መንፈሳዊ ንግደት ፈጽሜአለሁ፣ ለቤተ ክርስትያን ታላቅ ስጦታ ነበር፣ በዛችው የተባረከች መሬት አዎ የጌታ ኢየሱስ ታሪክን የመሰከረች እንዲሁም ለሶስቱም ታላላቅ እምነቶች ዕብራዊ ክርስትያናዊና እስላማዊ እምነቶች መሠረታውያን ነገሮች እውን የሆኑባት የተባረከች መሬት ናት፣ ለዚህም እግዚአብሔርን አመስግናለሁ፣ ለብፁዕነታቸው ፋውድ ጥዋል ለተለያዩ ሥር ዓቶች ጳጳሳት ካህናትና የቅድስት መሬት ጠባቂዎች ለሆኑ ፍራንቸስካውያን ልባዊ ምስጋናየን እንደገና ለማሳደስ እወዳለሁ፣ ለነገሩ እነኚህ ፍራቸስካውያን እጅግ ጐበዞች ናቸው የሚያደርጉት ያሉት ሥራቸው የጐበዞች ሥራ ነውና፣ ምስጋናየ ወደ ዮርዳኖስ እስራኤልና ፍልስጥ ኤም ባለሥልጣኖችንም ያጠቃልላል ምክንያቱም በታላቅ ክብር እንዲሁም በጓደኝነት ተቀበሉኝ፣ እንዲሁም ይህንን ሓዋርያዊ ጉዞ እውን እንዲሆን ለተባበሩት ሁሉ ልባዊ ምስጋናየን አቀርባለሁ፣
    የዚሁ መንፈሳዊ ንግደት ዋና ዓለማ በር.ሊ.ጳ ጳውሎስ ስድስተኛና በፓትርያርክ አተናጎራስ ለተካሄደው ታሪካዊ ግኑኝነት ሓምሳኛ ዓመት ለማክበር ነው፣ ያች ቀን የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ለመጀመርያ ጊዜ ቅድስት መሬትን የጎበኘበት ነበር፣ ጳውሎስ ስድስተኛ በሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤ ጊዜ የአርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት ጉዞ ከኢጣልያ ውጭ ይናገሩ ነበር፣ ያኔ በሮማዊው ጳጳስና በቍስጥንጥንያዊው ፓትርያርክ የተፈጸመው ትንቢታዊ ትእምርት ሁሉንም ክርስትያኖች ያሰቃይ የነበረው ልዩነት ተገርስሶ ይመኙት ለነበሩት አንድነት መሠረት ጣለ፣ እስከዛሬም ብዙ ተስፋ የሚሰጡ የአብያተ ክርስትያን አንድነት እርምጃዎች ተወስደዋል፣ ሆኖም ግን የእኔና እጅግ የተወደዱ በክርስቶስ ወንድሜ በርጠለሜዎስ የጉብኝቱ አንኳር በመያዝ የአንድነቱ ቅርበትን አብስረዋል፣ በኢየሱስ ባዶ መቃብር ላይ አብረን ጸልየናል ከኛ ጋር የኢየሩሳሌ ግሪካውያን ኦርቶዶክሶች ፓትርያርክ ብፁዕና ቅዱስ ተዮፊሎስ የአርመናውያን ሐዋርያዊ ፓትርያርክ በፁዕና ቅዱስ ኑርሃን እንዲሁም የሌሎች የተለያዩ አብያተ ክርስትያናትን ማኅበረ ክርስትያን ሊቃነ ጳጳሳት ጳጳሳት ባለሥልጣና ምእመናን አብረው ጸልየዋል፣ በዚሁ የጌታ ትንሣኤ የተበሰረበት ቦታ በክርስቶስ ተከታዮች መካከል ያሉ መከፋፈሎች የሚያስከትሉት ሥቃይና የዚሁ መራራነት ገልጠናል፣ ገና ተከፋፍለን መቀጠላችን እጅግ ያሳዝናል፣ ልብን ያሳምማል፣ በዛኛው ጌታ ከሙታን ተለይቶ መነሣት የታወጀበትና ጌታ ኢየሱስም ሕይወት የሰጠን ቦታ ገና መከፋፈል አለ ነገር ግን ያ ወንድማማነትና መከባበር የሞላበት ስለአንድነታችን ጸሎት ባሳረግንበት ወቅት አንድ የበጎቹ መንጋ ብቻ እንዲኖር የሚሻው መልካሙ እረኛ ድምጽ ኃያል ነበር፤ ገና ተከፍተው ያሉ ቍስሎቹን ለመፈወስና ለፍጹም አንድነት የምናደርገውን ጉዞ በጽናት እንድንቀጥል የሚጣራ ድምጽ ሰምተናል፣ ከእኔ በፊት የነበሩት አር እስተ ሊቃነ ጳጳሳት እንዳደረጉትም ለዚሁ መከፋፈል በእኛ በኩል ለተደረጉት ጉዳቶች ይቅሬታ በመጠየቅ መንፈስ ቅዱስ እንኚህን እኛ በሌሎች ወንድሞቻችን ያስከተልናቸው ቍስሎች ለመፈወስ እንዲረዳን እለምናለሁ፣ ሁላችን በክርስቶስ ወንድማሞች ነን ከፓትርያርክ በርጠለሜዎስም ጓደኞ ወንድሞች ስለሆንን አብረን ለመጓዝ ያለን ፍላጎትን ገልጠናል፤ ከዛሬ ጀምሮ ማድረግ የምንችለውን ሁሉ ለማድረግ አብሮ መጸለይም ይሁን ለሕዝበ እግዚአብሔር አብሮ መሥራት ሰላምን መፈለግ ተፈጥሮ መጠበቅና ብዙ የሚያስተባብሩን ነገሮች ለመፈጸም ተስማምተናል፣ እንደወንድሞችም አብረን ወደፊት መጓዝ አለብን ብለናል፣
    ሌላው የዚህ ንግደት ዓላማ ደግሞ በዚሁ ዞን ያለውን የእግዚአብሔር ስጦታና የሰው ልጆች ጥረትን የሚጠይቅ የሰላም ጉዞን ለማበራታታት ነበር፣ ይህንን በዮርዳኖስ በፍልስጥ ኤምና በእስራኤል አደረግሁት፣ ይህንን ሳደርግ ደግሞ እንደማንም መንፈሳዊ ተጓዥ የዚሁ ቦታ ሰዎች ለብዙ ጊዜ በውግያ ጋር ስለኖሩ የሰላም ዕለታትም ለማወቅ መብት እንዳላቸው በማሳሰብ በልቤ ውስጥ ታላቅ ርኅራኄ ይዤ በእግዚአብሔርና በዘመደ አዳም ስም ነው ያደርግሁት፣ ለዚህም በቦታው ለሚገኘው ክርስትያኖች ልቦቻቸው በመክፈትና ታዛዥ በማድረግ መንፈስ ቅዱስ እንዲቀባቸውና የትሕትና ወንድማማችነትና የእርቅ መንፈስ እንዲለብሱ አደራ አልኩ፣ በእምነትና በትህትና የቀረብነው እንደሆነ መንፈስ ቅዱስ ትሕትና ወንድማማችነት ይቅር ባይነት በዕለታዊ ሕይወታችን በመለገስ ከኛ የተለየ ባህልና እምነት ካላቸው ከሌሎች ሰዎች ጋር አብሮ ለመኖርና የሰላም ገንቢዎች ለመሆን ያስችለናል፣ ሰላም ትገነባለች ወይ ያልን እንደሆነ፣ ለሰላም የሚሆን ኢንዳስትሪ የለም፣ እላይ የጠቀስናቸው ዝንባሌዎችን በየዕለቱ በክፍት ልብ ያደረግን እንደሆነ እግዚአብሔር ሰላሙን ይሰጠናል፣ ለዚህም ነው በቦታው የሚገኙ ም እመናን ክርስትያኖችን በመንፈስ ቅዱስ እንዲቀቡ አደራ ያልክዋቸው፣

በዮርዳኖስ የመንግሥቱ ባለሥልጣናትንና መላው ሕዝቡ ከተለያዩ የውግያ ቦታዎች ለሚመጡ ስደተኞች በሚያደርጉት አቀባበልና እንክብካቤ አመሰገንክዋቸው፣ ይህ ታላቅ ሰብአዊ ሥራ ከባድ ስለሆነ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ቀጣይ ድጋፍ ማግኘት አለበት፣ የዮርዳኖስ በአከባቢው ካለው ውግያ ሸሽተው ለሚመጡ ስደትኞች ለመቀበልና ለመርዳት የሚያደርጉት ልግስና የሞላው ግብረሠናይ ልቤን ነካኝ፣ ለዚሁ ተግባር እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካቸው እላለሁ፣ እኛም እግዚአብሔር እነኚህ ሰዎች እንዲባርክ መጸለይና የዓለም አቀፉ የእርዳታ ተቅዋሞች ለዚህ ሕዝብ በሚያደርገው እንዲረድዋቸው መጠየቅ አለብን፣
በዚሁ ሐዋርያዊ ጉዞ በሌሎች ቦታዎችም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለሥልጣኖችን በመካከለኛ ምሥራቅ ያለውን ውጥረት ለማብረድ ከሁሉ በላይ ደግሞ በሲርያ ላለው ችግር እንዲሁም በእስራኤልና ፍልስጥኤም ያሉትን ውጥረቶች ሰላማዊ መፍትሔ እንዲያፈላልጉ የተቻላቸውን ያህል ለማበርከት ጥረት እንዲያደርጉ አሳስቤለሁ፣ ለዚህም የሰላም ሰዎችና ለሰላም የሚጥሩ የእስራኤሉ ፕረሲደንትና የፍልስጥኤም ፕረሲደንት ከሁለቱም ጋር አብረን ለሰላም እንድንጸልይ ቫቲካን እንዲመጡ ጥሬ አቅርቤለሁ፣ እናንተንም እባችሁ ብቻችን አትተውን ስለዚሁ ጉዳይ እንድትጸልዩ ይሁን፤ ጌታ ሰላሙን እንድሰጠን በተለይ ደግሞ ለዚችው የተባረከች መሬት፣ ጸሎቶቻችሁን እጠባበቃለሁ፣ በተለይ በዚሁ ጊዜ አበርትታችሁ እንድትጸልዩ ይሁን፣
    የዚሁ መንፈሳዊ ንግደት ሌላ ተጨማሪ ዓላማ ደግሞ በቦታው ለሚገኙ ማኅበረ ክርስትያኖችን ለማፅናት ነበር፣ በዚሁ ቦታ የሚገኙ ክርስትያኖች እጅግ እየተሰቃዩ ስለሆኑ ቤተ ክርስትያን ደግሞ በዚሁ ቦታና በመላው መካከለኛ ምሥራቅ ጸንተው በመቀጠላቸው ምስጋናዋን ለማቅረብ ነበር፣ እነኚህ ወንድሞቻችን የተስፋና የፍቅር ጽኑ ምስክሮች ናቸው፣ ለዚሁ መሬት ጨውና ብርሃን ናቸው፣ በእምነትና በጸሎት ሕይወታቸው እንዲሁም በሚያበረክቱት የትምህርትና የማኅበራዊ እርዳታ ለዕርቅና ለይቅር ባይነት እንደሚሰሩና ለጋራ በጎ ታላቅ አስተዋጽኦ እያደረጉ ናቸው፣

በዚሁ እውነትም የጌታ ስጦታ የሆነ ሐዋርያዊ ጉብኝት አንድ የተስፋ ቃል ለማስተላለፍ ነው የሄድኩት ነገር ግን እኔም በበኩሌ ይችን የተስፋ ቃል አገኘውሁ፣ ከገዛ መሬቶቻቸው በግጭት ምክንያት በመሰደድና በዘረኝነትና በእምነታቸው ምክንያት በሚያጋጥሙዋቸው ስደቶች በብርቱ ስቃዮች እየኖሩ ከሁሉ ተስፋ ጋር በመጻረር ካለው ሁኔታ እየተጋፈጡ ካሉ ወንድሞቼና እኅቶቼ አገኘኅዋት፣ ቅርበታችንን እንግለጽላቸው! ለእነዚህና ስለቅድስት መሬትና ስለመላው መካከለኛ ምሥራቅ ሰላም እንጸልይ፣ የመላዋ ቤተ ክርስትያን ጸሎት ለአብያተክርትያን አንድነት ለምናደርገው ጉዞም ይርዳን በዚህም ዓለም በመካከላችን በመምጣት ኢየሱስ ክርስቶስ ባበረከተልን በእግዚአብሔር ፍቅር ሊያምን ነው፣ አሁን በዚሁ አደባባይ ለምትገኙ ሁላችሁ ንግሥተ ሰላምና የክርስትያን አንድነት ንግሥት ለሆነችው የሁሉ ክርስትያኖች እና የመላው ዓለም እናት ለሆነችው ለእመቤታችን ድንግል ማርያም በዚሁ የአንድነት ጐዳና እንድትሸኘኝ አብረን ሰላም ላንቺ ኦ ማርያም እንድገም፣








All the contents on this site are copyrighted ©.