2014-04-16 19:33:03

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ


ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ! RealAudioMP3
ይሁዳ ጌታን በመካድ ወደ አይሁድ የካህናት አለቆች በመሄድ መምህሩን አሳልፎ ለመስጠት የተዋዋለበት የሚያሳዝነውን የጌታ ታሪክ በምናስተነትንበት የሶሙነ ሕማማት ሥርዓት አጋማሽ ላይ እንገኛለን፣ ይሁዳ ለካህናት አለቆቹ ስንት ትሰጡኛላችሁ ብሎ ይጠይቃቸዋል፣ ከዚህ ግዜ በኋላ ጌታ ኢየሱስ አንድ ዋጋ ተወሰነበት፣ ይህ አሳዛኝ ፍጻሜ ጌታ በነጻ ፍላጎቱ የመረጠው መራራው ሕማማቱ የሚጀመርበት ጊዜ ነበር፣ ይህንን ራሱ ኢየሱስ በወንጌለ ዮሐንስ “ነፍሴን ደግሞ አነሣት ዘንድ አኖራለሁና ስለዚህ አብ ይወደኛል። እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም። ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ ይህችን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ።” (10፤17-18) በማለት ይገልጠዋል፣ እንዲህ ባለ መንገድም ያ ውርደትና ልብስ ማወልቅ በዚሁ ክህደት ይጀምራል፣ ኢየሱስ እንደ አንድ የንግድ ዕቃ በ30 ብር ይሸጣል፣ ኢየሱስም ይህንን የውርደትና የልብስ መገፈፍ ስቃይ እስከ መጨረሻ ይጓዘዋል፣ የውርደቱ ፍጹምነትን በመስቀል ላይ በመሞት ይቀበለዋል፣ ይህ የሞተ ቅጣት ያኔ ለባሮችና ለወንበዴዎች የሚሰጥ የከፋ ቅጣት ነበር፣ ኢየሱስ እንደነቢይ ይታይ ነበር ነገር ግን የአንድ ወረበላ ቅጣት በመቀበል በመስቀል ላይ ሞተ፣ ኢየሱስ ሲሰቃይ በምናይበት ጊዜ የመላው የሰው ልጅ ስቃይን እንደ በመስትዋት እናያለን በዚህም የሥቃይና የክፋት እንዲሁም የሞት ምሥጢር መለኮታዊ መልስ እናገኛለን፣ አብዛኛውን ጊዜ ከበውን ያሉትን የክፋትና የሥቃይ እሮሮን ባየን ጊዜ እንደነግጣለን “እግዚአብሔር ለምን ይህን ነገር ፈቀደ?” ብለንም እንጠይቃለን፣ ስቃይንና ሞትን በምናይበት ጊዜ በተለይ ደግሞ የንጹሓኑን እንዲሁም ሕጻናት ሲሰቃዩ በምናይበት ጊዜ ለልባችን ታላቅ ቁስል ሆኖ ይሰማናል፣ ይህ የክፋት ምሥጢር ነው ኢየሱስም ይህንን ይቀበለዋል መላው ስቃይን በገዛ ራሱ ይቀበለዋል፣ በዚሁ ሳምንት ሁላችን መስቀሉን በማትኰር የተመለከትንና የተሳለምነው እንደሆነ እንዲሁም የተቸነከሩትን ቍስሎቹ የተሳለምን እንደሆነ ጥሩ ነው፣ እርሱ የሰው ልጅ ስቃይን በሙሉው ወደ ገዛ ራሱ ወሰደው፣ እግዚአብሔር በከሃሌ ኵሉነቱ ኢፍትሓዊነትን ክፋትንና ኃጢአትን እንዲሁም ስቃይን አሸናፊ በሆነው መለኮታዊው ድል እንዲያስገኝልን እንጠባበቃለን፣ ነገር ግን እግዚአብሔር በሰው ልጅ አመለካከት ሽንፈት በሚመስለው የትሕትና አሸናፊነትን ያሳየናል፣ እንዲህ በመሆኑም የእግዚአብሔር ልጅ እንደተሸነፈ ሰው በክህነደትና በብዙ ስቃይ በመስቀል ላይ ተሰቀሎ ሞተ፣ ነገር ግን ኢየሱስ ይህ እንዲሆነ የፈቀደው አጠቃላዩን የሰው ልጅ ስቃይና ክፋት በገዛ ራሱ እንዲለብሰውና በመጨረሻም እንዲያሸንፈው ነው፣ ስቃዩና ሕማማቱ እንደአጋጣሚ የሆነ አይደለም ያች እርሱ የሞተባት ሞት ድሮ ተጽፋ ነበር፣ እንደእውነቱ ብዙ መግለጫ የለንም እጅግ አስደንጋጭ የሆነ ምሥጢር ነው፣ የእግዚአብሔር ታላቅ የትሕትና ምሥጢር ነገር ግን የዚህ ምሥጢር ትርጉም እናውቃለን የዚህ ታላቅ ትሕትና ምሥጢርም “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።” (ዮሐ 3፤16) በዚህች ሳምንት ስለ ኢየሱስ ስቃይ በደንብ በማስተንተን ገዛ ራሳችንን “ይህን ያደረገው ለኔ ነው፣ በዚህ ዓለም የሚኖር አንድያ ሰው እኔ ብሆንም ጌታ ለኔ ባደረገው ነበር፣ ይህንን ያደረገው ለኔው” ብለን እናስታውሰው፣ መስቀሉንም በመሳለም “ለኔ ነው ተመስገን ኢየሱስን ይህን ያደረግሀው ለኔ ነው” እንበል፣
የኢየሱስ ሕማማትና ሞት እንዲሁም የብዙ የሰው ልጆች ተስፋ መበታተን እጊዝብሔር ደህንነታችን እንዲፈጽም የተጠቀማቸው ዋነኛ መንገድ ናቸው፣ ይህ መንገድ በማንኛው የሰው ልጅ መመዘኛ ሊመዘን የማይቻል ነው፤ እንዲያው የተገላቢጦሽ ይሆናል፣ እኛ ሁላችን በኢየሱስ ቍስሎች ድነናል፣ (1ጴጥ 2፤24 ተመልከት) ሁሉ ነገር የጠፋ በሚመስልበት ጊዜ ሁላቸውም ስለሚሸሹ አንድም በማይቀርበት ጊዜ “እረኛውን እመታለሁ የመንጋውም በጎች ይበተናሉ የሚል ተጽፎአልና፤” (ማቴ 26፤31)፣ ያኔ ነው እግዚአብሔር በትንሣኤ ኃይል ጣልቃ የሚገባው፣ የኢየሱስ ትንሣኤ እንደ የአንድ ፊልም ደስ የሚያሰኝ ወይም የአንድ ደስ የሚያሰኝ ታሪክ ፍጻሜ አይደለም ነገር ግን እግዚአብሔር ጣልቃ ገብነት የሰው ልጅ ተስፋ በሚበንበት ጊዜ ተአምር ያደርጋል፣ ሁሉም የጠፋ በሚመስልበት ጊዜ ብርቱ ሥቃይ በሚያጋጥምበት ጊዜ ብዙ ሰዎችም ከመስቀል የመሸሽና የመውረድ ፈተና በሚያጋጥማቸው ጊዜ ለትንሣኤ ቅርብ መሆናቸውን ማወቅ አለባቸው፣ ሌሊቱ ሊነጋ ሲል ብርሃን ሊቀድ ሲል ጨለማው እጅግ ይከብዳል፣ እጅግ በጨለመ ጊዜም እግዚአብሔር ጣልቃ ይገባል፣ ከሙታን ለይቶ ያነሣል፣ በዚሁ ጐዳና ሊያልፍ የፈለገው ኢየሱስ እርሱ የተከተለውን የትሕትና ጉዞ እንድንከተል ይጠራናል፣ በኑሮ ዘመናችን አንዳንዴ ከችግሮቻችን ምንም መውጫ በምናጣበት ጊዜ፤ እጅግ ከባድ በሆነ ጨለማ በገባንበት ወቅት፤ የመዋረዳችንና የልብሳችን መገፈፍ ሰዓት መሆኑን ደካማዎችና ኃጢአተኞች መሆናችን የምናጣጥምበት ጊዜ ነው፣ ያኔ በዛች ጊዜ ነው ውድቀታችንን መሸፈን የሌለብን ነገር ግን ጌታ ኢየሱስ እንዳደረገው ሁሉ፤ በታላቅ መተማመን ልባችንን ለእግዚአብሔር ክፍት ማድረግ ያስፈልጋል፣ ውድ ወንድሞችና እኅቶች በዚሁ ሳምንት የጌታ መስቀልን በእጃችን ይዘን ደጋግመን እየሳምነው “ተመስገን ኢየሱስ ተመስገን ጌታዬ” እንበል አሜን፣








All the contents on this site are copyrighted ©.