2014-04-15 09:39:35

በኢየሱስ ፊት ማርያም ነን የምንመስለው ወይስ ይሁዳን?


RealAudioMP3 በትናንትና ዕለት በዓለ ሆሳዕና በታላቅ ድምቀት የተከበረ ሲሆን ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በዚሁ ሶሙነ ሕማማት እያንዳንዱ ክርስትያን መመለስ ያለበት ሃይለኛ ጥያቄ አቅርበዋል፣ እያንዳንዱ ክርስትያን በዚሁ ሶሙነ ሕማማት ወደ ኅሊናው በመመለስ በኢየሱስ ፊት እኔ ማን ነኝ? እንደ ይሁዳ ነው የምኖረው ወይስ እንደጲላጦስ ወይስ እንደ ማርያም? እንደ ስም ዖን ቄረናዊ ወይስ ኢየሱስን እስከ መስቀል ሞት ላይ የተከተሉት እንደ ርኅሩሃኑ ሴቶች እከተለዋለሁ? ብለን ኅልናችንን እንድንመርምርና እንድናስተንትን ጥሪ አቅርበዋል፣ ትናንትና በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በተፈጸመው የሥር ዓተ ሆሳዕና መሥዋዕተ ቅዳሴና በዓል እንዲሁም እኩለ ቀን ላይ በተፈጸመው የመል አከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮና ጸሎት ከስልሳ ሺ በላይ ምእመናን እንደተሳተፉ ከቅድስት መንበር የወጣ ዜና አመልክተዋል፣ በዓለ ሆሳዕና የሃገረ ስብከት የወጣቶች ቀንም በመሆኑ ከጣልያን አገርና ከመላው ዓለም የተሰበሰቡ ብዙ ወጣቶችም በበዓሉ እንደተሳተፉ ሲገለጥ በተለይ ደግሞ ባለፈው ዓመት አለም አቀፍ የወጣቶች ቀንን ካከበረች ብራዚል ከርዮ ዲ ጃነሮ ወደፊት ለሚከበረው አለም አቀፍ የወጣቶች ለፖላንድ የክራኮቭያ ወጣቶች ከወጣቶቹ ጋር የሚጓዘውን ታላቅ የወጣቶች ዓለም አቀፍ ቀን መስቀል ሊያስረክቡ ከሁለቱም አገሮች ብዙ ወጣቶች ተገኝተው ነበር፣ ቅዱስነታቸው ለወጣቶቹ ሲናገሩ ለኤስያ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ቀን በደቡብ ኮርያ እፊታችን ወርኃ ነሓሴ እንደሚሄዱም አስታውሰዋል፣
እላይ የጠቀስናቸው ጥያቄዎች በተለይ ወደ ወጣቶች ያተኮሩ ስለነበር እያንዳንዱ ወጣት ከገጸ ባህርያቱ ማንን እመስላለሁ ብላችሁ ራስችሁን ጠይቁ በማለት ንግግራቸውን የጀመሩት ለዚሁ ታላቅ የእምነት ጥያቄ እያንዳንዱ በኅሊናው እንዲመልስ ለብዙ ሰኮንዶች በአደባባዩ ኃያል ጸጥታ ሰፈነ፣ አያይዘውም ዓይናቸውን በብርቱ ትኵረት ከተከሉበት በአደባባዩ ሞልተው በነበሩ ወጣቶ ሳያንቀሳቅሱ ረጋ ባለ ዝቅተኛ ድምጽ እንዲህ ሲሉ ጠይቀዋል፣ ማን ነኝ እኔ በጌታ ፊት ማን ነኝ?
“ወደ ኢየሩሳሌም በታላቅ በሚገባ በኢየሱስ ፊት ማን ነኝ እኔ? ደስታዬን ለመግለጥና ላክብረው እችላለሁን? ወይንስ ባለሁበት ቆሜ በሩቅ እመለከተዋለሁ? በሚሰቃየው ኢየሱስ ፊት እኔ ማን ነኝ? ሲሉ ከጠየቁ በኋላ በወንጌሉ ከተነበበው የጌታ ታሪክ የተለያዩ ገጸ ባህርያቶችን እየጠቀሱ ጌታን ለመግደል ከሚማከሩ ሊቃነ ካህናት ጀምረው በ30 ብር ጌታን እንደሸጠ ይሁዳ እሆን ወይስ ጌታ ከተያዘ በኋላ ከፍቁረ እግዚ እ ዮሐንስ በስተቀር የተበታተኑት ሐዋርያት እመስላልሁ ሲሉ የተለያዩ ሰዎችን ከጠቀሱ በኋላ ስለሓዋርያቱ ሁኔታ እንዲህ ብለዋል፣
“ስለሁኔታው ምንም ያልገባቸውና ግራ የተጋቡ ሓዋርያት ጌታ ሲሰቃይ ይተኙ ነበር፣ ሕይወቴ የእንቅልፍ ሕይወት ይሁን ወይስ ጌታን አሳልፎ መስጠት ምን መሆኑ እንዳልተረዳቸው ወይንም ያ ጌታን ሊከላከል ሰይፉን የመዘዘ እንደየትኛው እሆን? ወይንም የባሰው ጌታን እንደሚያፈቅር ለማስመሰል በመሳም አስላፎ የሰጠ ይሁዳ? ከሃዲው እኔ እሆን ወይስ እንደሊቃነ ካህናት ሁሉን በችኰላ ሸንጎ ጠርተው የውሸት ምስክሮች ለማቅረብ ይረዋወጡ እንደነበሩ እሆን? ወይንስ የሁኔታው መግቢያና መውጫ በጠፋበት ግዜ እጁን በውኃ እንደታጠበ ጲላጦስ ጌታን ጓደኞቼን ሲገድልዋቸው ዝም የምመለከት እሆን? ወይንስ በጌታ ላይ ያፌዙ እንደነበሩ እሆን?
“ሃይማኖታዊ ስብሰባ ወይንም ፍርድ ወይንም የመናፈሻ ሜዳ መሆኑን ሊለይ ያልቻለው በቦታው ተስብስቦ ኢየሱስን ይሰቅሉት ዘንድ የጮሀና ባርባንን ነጻ እንዲለቀቅ ከመረጠው ሕዝብ አንድ እሆን፣ ጌታን ማሳቃየት ደስ ያላቸው ወታደሮች አንዴ ሲደበድቡት አንዴ ፊቱ ላይ ሲተፉለት አንዴ ደግሞ ሲሰድቡትና ያዋርዱት እንድነበሩ እሆን?
“ከሥራ ወደ ቤቱ ይመለስ እንደነበረው ደክሞት የነበረ ነገር ግን የጌታን መስቀል ለመሸከም ፈቃደኛ እንደሆነ ቄረናዊው ስምዖን እሆን፧ ወይስ እንደ ጀግኖቹ ሴቶች ወይስ እንደ ኢየሱስ እናት በጸጥታ ትሰቃይ የነበረች እመቤታችን ድንግል ማርያም ወይስ በምሥጢር የኢየሱስ ተከታይ የነበረውና ጌታን የቀበረው ዮሴፍ ዘአርማትያስ ወይስ በኢየሱስ መቃብር ላይ ሲጸልዩና ሲያልቀሱ የነበሩ ሁለቱ ማርያሞች እሆን? ሲሉ የተለያዩ ጥያቄዎች ካቀረቡ በኋላ ሶሙነ ሕማማት በመጀመር ላይ ስለሆነን ልባችንን እንመርምር ዘንድ የሚከተለውን ጥያቄ በማቅረብ ስብከታቸውን ደምድመዋል፣
“ልቤ እምን ላይ ነው ያለው? የትስ አለ? እላይ ከዘረዘርናቸው ገጸ ባህርያት የትኞቹን ይመስላል? ለዚሁ ሶሙነ ሕማማት ይህንን እናስተንትን ብለዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.